FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

Archive for the day “July 9, 2015”

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙም ተፈታች (ኤዶም እና ማህሌትም ተፈተዋል)

Jul9,2015

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ትላንት የተጀመረው የመፈታት ዘመቻ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። በጋዜጠኛነት ሙያዋ የምትታወቀው ርዕዮት አለሙ ዛሬ ተፈታለች። ትላንት ያልተፈቱት ሁለቱ ሴት ጦማርያን ኤዶም እና ማህሌትም እንዲሁ ተፈተዋል። “አሸባሪዎች” ተብለው በሃሰት ክስ የተመሰረተባቸው ጋዜጠኞችን የመፍታቱ ዘመቻ ድንገተኛ እናአ ያልታሰበ በመሆኑ ብዙዎችን እያነጋገረ የሚገኝ ትኩስ ዜና ሆኗል።

ርዕዮት አለሙ ከእስር ከተፈታች በኋላ። ከእህቷ እስከዳር አለሙ እና ባለፈው ፖሊሶች ቀጥቅጠው እጁን ሰብረውት ከነበረው - ስለሺ ሃጎስ ጋር የተነሱት ፎቶ።

ይህ ፍቺ የተጀመረው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ከተገለጸ እና በተለይም ባለፈው ሳምንት  በኋይት ሃውስ ከፍትና የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ከተደረገ በኋላ መሆኑን ታዛቢዎች የራሳቸውን መላ ምት ይሰጣሉ። ሌሎች ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ የግንቦት 7 አርበኞች የጦርነት እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ በኋላ፤ መንግስት የህዝቡን ትኩረት ለማግኘት ያደረገው ነው” ሲሉ ይደመጣል። ሆኖም አሁንም ቢሆን በርካታ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያን የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች እና የፖለቲካ እስረኞች በእስር ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ያለምንም ጥፋታቸው የታሰሩ ዜጎች እስኪፈቱ ድረስ ግን፤ መዘናጋት አያስፈልግም።

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን መፈታት ምክንያት በማድረግ፤ ታናሽ እህቷ እስከዳር አለሙ ባስተላለፈችው መልዕክት እንዲህ ብላለች። “በጣም ደስ ብሎኛል !
ሁሌ ነገሪ የሆነች እህቴ ዛሬ አ|ጠገቤ አለች ለዚህም ደስ ብሎኛል ! ይህ ደስታ የኔ ብቻ አይደለም ስለ ሉልዬ ( ርዕዮት) የምትጨነቁ በሙሉ ነው፣ ልክ እንደ እህቴ እና ወንድሜ የምሳሳላቸው ማህሌት ፋንታሁን፣ ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ ዘላለም ክብረት፣ አስማማው ሀ/ጊዮርጊስ ከእስር ተፈተውልኛል፣ደስታዬም ይበልጥ ድርብ ሆኖልኛል ፣ ቀሪዎችም ከእስር እንደሚፈቱ እምኔቴ ፅኑ ነው፡፡ለሁሉ ነገር ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን .አሜን !!!”

ርዕዮት አለሙ ከእህቷ እስከዳር አለሙ ጋር - ከእስር ቤት መልስ።

ለተፈቱት ወገኖቻችን “እንኳን ደስ አላቹህ” እያልን ሌሎቹንም ለማስፈታት የሚደረገው ሰላማዊ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል – የሚለው ደግሞ የኛ መልዕክት ነው።

posted by Daniel tesfaye

Post Navigation