FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

Archive for the month “June, 2013”

በድጋሚ የወጣ የአቋም መግለጫ፤ ድምጼን ከፍ አድርጌ እደግመዋለሁ!

June30,2013

 

አቤ ቶኪቻው

በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራእኔ ኦሮሞ ነኝ፡፡ ኦሮሞነቴን የሰጡኝ አባቴ እና እናቴ ናቸው እንጂ ከሱፐር ማርኬት ገዝቼው አይደለም፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ከእናት እና ከአባቴ እንጂ አንዳች አካል እላዬ ላይ ለጥፎብኝ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያዊነቴ እንደምኮራው ሁሉ ኦሮሞነቴም ኩራቴ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተዟዙሪያለሁ፡፡ የዛን ጊዜ ከ”አካም ቡልተኒ” ውጪ ምንም ኦሮምኛ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን በየባላገሩ ያሉ ኦሮሞዎች የኔ አማርኛ ተናጋሪ መሆን፤ ወይም ኦሮምኛ ቋንቋ አለመቻል አንድም ቀን አሳስቧቸው አያውቅም፡፡ ሰው በመሆኔ ብቻ አክብረው እርጎ አቅርበውልኝ፣ እርጎ የሆነ ፈገግታ ለግሰውኝ፣ ለራቸው ከሚተኙበት የተሸለ መኝታ ሰጥውኝ በእንክብካቤ ነው የሚያስተናገዱኝ፡፡

አንዳንዶች፤ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አልመሆኑን ሊነገሩኝ ታሪክ እንዳነብ፣ አዋቂ እንድጠይቅ፣ ጸሎት እንዳደርግ ሁላ መክረውኛል፡፡ እኔ ግን ይሄንን ሁሉ ማድረግ ሳያስፈልገኝ ከኦሮሞ የሚፎካከር ኢትዮጵያዊ እንደሌለ አሁን በቅርቡ የዞርኩባቸው የኦሮሚያ ገበሪዎች አረጋግጠውልኛል፡፡ ይህንን ነገር እኔ ብቻ ሳልሆን በቅርብ የኦሮሞን ህዝብ ጠንቅቀው የሚያውቁት እነ ጀነራል ከማል ገልቹ አረጋግጠውታል፡፡ እነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳም መርቀውታል፡፡ ለዛም ነው ዛሬ የጀነራል ከማል ገልቹ ኦነግ በስፋት ተቀባይነት እያገኝ የመጣው፡፡ ለዛም ነው ዛሬ የኦሮሞ ልጆች በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያሸበረቀ የኦነግ አርማን  ከአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የሀገራቸው ባንዲራ ጋር ጎን ለጎን ይዘው በአደባባይ ስለ ኢትዮጵያ ልጆች የሚጮሁት!

ለብቻ መኖር የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ቢሆን ኖሮ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ጀግንነት እና ብዛት፤ ጮክ ብዬ እደግመዋለሁ እንደ ኦሮሞ ህዝብ ጀግነነት እና ብዛት፤  አርባ አመት ፈጅቶ አይኮላሽም ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ እየተበደለ እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ በርካታ ወዳጆቼ ኦሮምኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ብቻ ኦነግ ናችሁ ተብለው ከዩንቨርስቲ ወጥተው እስር ቤት ገብተዋል፡፡ ከስራቸው ተባረው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ ወዘተ ተደርገው ወዘተ ሆነዋል፡፡ ልክ እንደዛ ሁሉ ግን በደሉ ሌሎችም ዘንድ አለ፡፡ አማራውም ትግሬውም አዲሳቤውም ሁሉም ቁስል አለበት፡፡

አብሮ ታክሞ አብሮ መኖር ለሁሉም ይበጃል!!!

posted by Daniel tesfaye

13

 

 
 
 
 
 
 

አቤ ቶኪቻው

የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ

6dfc868ecccfc66f6592d0a6b7e266ba_XL
30 June 2013

ፍርድ ቤት ቀርበው በ25 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ፣ ተጠርጥረው በተከሰሱበት ከፍተኛ የማታለል ወንጀል ምክንያት ከአገር እንዳይወጡ ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. የእግድ ትዕዛዝ ተላለፈባቸው፡፡

ቀደም ባለው ቀጠሮ ሳይቀርቡ በመቅረታቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምስተኛ ወንጀል ችሎት ለሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ታስረው እንዲቀርቡ ባዘዘው መሠረት ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. የቀረቡ ሲሆን፣ በመጀመርያ ቀጠሮ ያልቀረቡበት ምክንያታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

በሕመም ምክንያት ሊቀርቡ አለመቻላቸውንና በዕለቱም በሕመም ላይ መሆናቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ተጠርጣሪዎቹ የተመሠረተባቸው ክስ ተሰምቶ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት ቢገባቸውም፣ ዓቃቤ ሕግ ከክሱ ጋር የሚያያይዘው ቀሪ ማስረጃ እንዳለው ገልጾ፣ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው በመጠየቁ ክሱ ሳይሰማ ቀርቷል፡፡

ሌላው ዓቃቤ ሕግ ለችሎቱ ያመለከተው ጉዳይ ተጠርጣሪዎቹ በአርበኞች ማኅበር ሠራተኞች ላይ ዛቻና ማስፈራራት እያደረሱ መሆኑን፣ ፕሬዚዳንቱ ቢሮ ባይገቡም ቤታቸው ውስጥ ሆነው እየሠሩ መሆናቸውን፣ በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ የማኅበሩ ንብረቶች አደጋ ላይ መሆናቸውን በማስረዳት፣ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆችም ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ማመልከቻ በማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ለችሎቱ በመግለጽ፣ የዓቃቤ ሕግ አቤቱታ ተዓማኒነት እንደሚጐድለው በማስረዳት አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄም በቤታቸው መሥራታቸው ለመታመማቸው ማስረጃ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው ስላሉት የማኅበሩ ሠራተኞችና የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን በሚመለከት ዓቃቤ ሕግ በማስረጃ የተደገፈ አቤቱታ በጽሕፈት ቤት በኩል እንዲያቀርብ በማሳሰብ፣ ፕሬዚዳንቱ በ25 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ አዟል፡፡ ክስ ለመስማትና የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለሐምሌ 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

source,,http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/2383-የአርበኞች-ማኅበር-ፕሬዚዳንት-ከአገር-እንዳይወጡ-ታገዱ

posted by Daniel tesfaye

ከፌዴራል መንግሥት በጀት በሕግ በተቀመጡ መመዘኛዎች መሠረት ከተመደበው 20 ሚሊዮን ብር ውስጥ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባት ሚሊዮን ብር ሕግን በመጣስ ኢሕአዴግ ለመረጣቸው ፓርቲዎች አከፋፍሏል በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ቀረበበት፡፡

ምርጫ ቦርድ ሕግ በመጣስ በኢሕአዴግ ለተመረጡ ፓርቲዎች ገንዘብ ሰጥቷል በሚል ጥያቄ ቀረበበት

ምርጫ ቦርድ ሕግ በመጣስ በኢሕአዴግ ለተመረጡ ፓርቲዎች ገንዘብ ሰጥቷል በሚል ጥያቄ ቀረበበ

“ፓርቲዎች ከዜጎች ገንዘብ እየተቀበሉ የቪዛ የድጋፍ ደብዳቤ ሲሰጡ ቦርዱ ችላ ብሏል” አቶ ግርማ ሰይፉ

“ሆደ ሰፊ የሆንነው ዴሞክራሲ እንዲጎለብት በማሰብ ነው” 

ፕሮፌሰር መርጋ በቃና

ከፌዴራል መንግሥት በጀት በሕግ በተቀመጡ መመዘኛዎች መሠረት ከተመደበው 20 ሚሊዮን ብር ውስጥ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባት ሚሊዮን ብር ሕግን በመጣስ ኢሕአዴግ ለመረጣቸው ፓርቲዎች አከፋፍሏል በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ቀረበበት፡፡

በምርጫ ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ሥራ ማስፈጸሚያና ለዕለት ተዕለት ተግባራት ማከናወኛ በጀት የማከፋፈል ሥልጣን የተሰጠው የምርጫ ቦርድ አመራሮች ለቀረበላቸው የሕግ ጥሰት ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡ አልፈውታል፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራሮች የ2005 ዓ.ም. አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ባለፈው ሐሙስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በተጠቀሰው የሕግ ጥሰትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በዓመቱ ውስጥ የተካሄዱት የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫዎች ዴሞክራሲያዊና ነፃ ሆነው መጠናቀቃቸውን፣ ለዚህም ውጤት ቦርዱ ያከናወናቸውን ዝርዝር ተግባራት በ14 ገጽ ሪፖርታቸው ጨምቀው አቅርበዋል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች መቀመጫ ላላቸው አሥር የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዕለት ከዕለት ተግባር ማከናወኛ በጀት 20 ሚሊዮን ብር ከመንግሥት በማስፈቀድ ባላቸው መቀመጫ ብዛት ተሰልቶ የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸውን ላሳወቁ ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማከፋፈሉን የቦርዱ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ ይሁን እንጂ ከተጠቀሰው 20 ሚሊዮን ብር የትኛው ፓርቲ ምን ያህል እንዳገኘ አልተካተተም፡፡

ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላ በምክር ቤቱ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ለፓርቲዎች የሚከፋፈል የመደበው 20 ሚሊዮን ብር በጀት ላይ ጠንከር ያለ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ከተጠቀሰው 20 ሚሊዮን ብር የትኛው ፓርቲ ምን ያህል ወሰደ የሚል ጥያቄ ማንሳት እንደማይፈልጉ፣ ምክንያቱ ደግሞ መመዘኛው በሕግ የተቀመጠና ቦርዱን የሚመለከት ባለመሆኑ እንደሆነ፣ ነገር ግን በመመዘኛው መሠረት ኢሕአዴግና አጋሮቹ አብዛኛውን እንደወሰዱት ግልጽ መሆኑን በመጠቆም ነበር አቶ ግርማ ወደ ጥያቄያቸው የገቡት፡፡

በመመዘኛው መሠረት ኢሕአዴግ ካገኘው ገንዘብ ውስጥ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚሆነውን በራሱ ፍላጎት ለመረጣቸው ፓርቲዎች እንዲከፋፈልለት በመጠየቅ ለቦርዱ መመለሱንና ቦርዱም በኢሕአዴግ ለተጠቆሙት ፓርቲዎች ማከፋፈሉን አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡ ጥያቄያቸውም ያጠነጠነው በዚህ ላይ ነው፡፡

“የተጠቀሰው ሰባት ሚሊዮን ብር በሕግ መሠረት ለተፈለገው ዓላማ ነው ወይ የዋለው?” በሚል ጠንከር ያለ ድምፀት ጥያቄያቸውን ያነሱት አቶ ግርማ፣ “በመጀመሪያ ደረጃ በምክር ቤት ወንበር ለሌላቸው ፓርቲዎች የመንግሥትን ገንዘብ የማደል ሥልጣን ለኢሕአዴግ ማን ሰጠው?” በማለት አክለዋል፡፡ በመቀጠልም ገንዘቡን ኢሕአዴግ ሳይሆን ያደለው ምርጫ ቦርድ መሆኑ እንዳስገረማቸው፣ “ኢሕአዴግ እገሌ እገሌ ለሚባሉት ፓርቲዎች ስጡልኝ ብሎ በጠየቀው መሠረት ገንዘቡን ለተባሉት ፓርቲዎች ያደለው ምርጫ ቦርድ ነው፤” ብለዋል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በወቅቱ የቦርዱን ሰብሳቢ በአካል አግኝተዋቸው እንዴት ይህንን ታደርጋላችሁ የሚል ጥያቄ አንስተው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ግርማ፣ ሰብሳቢው ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በወቅቱ ምን ክፋት አለው የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው በይፋ ተናግረዋል፡፡ “በእርግጥ በቅን ልቦና ስናስበው ምንም ክፋት የለውም፡፡ በሕግ ግን አይቻልም፡፡ በሕግ ላልተፈቀደላቸው ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ገንዘብ ማደል አልተፈቀደለትም፤” በማለት፣ “በየትኛው ሥልጣናችሁ ገንዘቡን እንዳደላችሁ ያስረዱን፤” ሲሉ ፕሮፌሰር በቃናን በምክር ቤቱ ፊት ጠይቀዋል፡፡

ባነሱት የሕግ ጥሰት ጉዳይ ላይ የበለጠ ማስረዳት የመረጡት አቶ ግርማ፣ “በምሳሌ ላስረዳዎት፤ መንገዶች ባለሥልጣን የተፈቀደለትን በጀት መጨረስ ስላልቻለ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስጠት አይችልም፤” ሲሉ የሕግ ጥሰቱን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡

ከተጠቀሰው በመንግሥት ለፓርቲዎች የተፈቀደ 20 ሚሊዮን ብር በጀት ውስጥ ኢሕአዴግ በአከራካሪዎቹ መስፈርቶች ያገኘው ገንዘብ ግዙፍ ስለሆነበት ለሌሎች ፓርቲዎች እንዲከፋፈልለት ማድረግ እንደማይችል ገንዘቡን የማይፈልገው ከሆነ በሕግ አግባብ ማድረግ የሚችለው ለምርጫ ቦርድ መመለስ ብቻ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡

“የእኔ ፓርቲ ከ20 ሚሊዮን ብር ውስጥ ለዓመት ሥራ ማስኬጃ የደረሰው ሦስት ሺሕ ብር ነው፡፡ እኛ ስለማይበቃን ገንዘቡን እንደመለስነው ኢሕአዴግም ይህንን ነበር ማድረግ ያለበት፤” ብለዋል፡፡ በማከልም ይህ ስህተት ሊታረም ይገባል ብለው፣ የሚታረመው ሌሎች ምክንያቶችን በመደርደር ሳይሆን ኢሕአዴግ ከሌላ የገንዘብ ምንጩ የተከፋፈለውን ገንዘብ ለምርጫ ቦርድ በመመለስ ብቻ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በተለየ ጉዳይ ጥያቄያቸውን ለምርጫ ቦርድ አመራሮች ማቅረባቸውን በመቀጠል፣ የመደራጀት መብት በአገሪቱ ስላለ ብቻ የፖለቲካ ፓርቲ እየመሠረቱ ነገር ግን ለፖለቲካ ተልዕኮ ሳይሆን ለሕገወጥ የገንዘብ መሰብሰቢያነት የሚጠቀሙ ፓርቲዎች መኖራቸው በግልጽ እየታወቀ፣ ቦርዱ ቸልተኝነትን መርጧል በማለት፣ “ሥራችሁ ምንድን ነው? ምንድን ነው የምታደርጉት?” ሲሉ አቶ ግርማ ጠይቀዋል፡፡ “በአሁኑ ወቅት ንግድ ፈቃድ ከማውጣት የፖለቲካ ፓርቲ ፈቃድ ማውጣት ይቀላል የተባለው እውነት እየሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ንግድ ፈቃድ ያወጡ ግለሰቦች ፈቃዱን ካልተጠቀሙበት ይሰረዛሉ፤” የሚሉት አቶ ግርማ፣ “ፓርቲዎች ምን ሲያደርጉ ነው እዚህ አገር የሚሰረዙት?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ለዚህ ጥያቄያቸው ራሳቸው የሰጡት ምላሽ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ከፖለቲካ ዓላማ ይልቅ ከዜጎች ገንዘብ እየተቀበሉ የውጭ አገር የቪዛ ማስመቻ ድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍ ዜጎችን ለስደት እየዳረጉ ነው የሚል ነው፡፡ “መንግሥት ለፓርቲዎች የሰጠውን የመንግሥት ቤት ለሌላ ሦስተኛ ወገን አከራይተው በጥቅም ሲጣሉ በሚዲያ እየተሰማ ቦርዱ ግን ዝምታን መርጧል፤” ሲሉ ተጨማሪ ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡

ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የጀመሩት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና፣ ለፓርቲዎች ተብሎ ከመንግሥት የሚመደበውን የድጎማ ገንዘብ ቦርዱ የሚያከፋፍለው ሕግን መሠረት አድርጎ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በሕጉ መሠረትም ፓርቲዎቹ በፌዴራልም ሆነ በክልል ምክር ቤቶች ውስጥ ያላቸው መቀመጫ ብዛት አንደኛው መስፈርት መሆኑን፣ የሌሎቹ ፓርቲዎች ለቅስቀሳ ዘመቻ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በገንዘብና በዓይነት የሚሸፈን እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዚህ መስፈርት መሠረት ተጠቃሚ መሆን የሚገባቸው አሥር ፓርቲዎች እንደነበሩ፣ ከእነዚህ ውስጥ ለስምንቱ መከፋፈሉን ሁለቱ ግን የገንዘቡ መጠን ስላነሰባቸው አለመቀበላቸውን ገልጸው፣ “ገንዘቡን የወሰዱ ፓርቲዎች በምን ላይ እንዳዋሉት ኦዲት አስደርገው ማቅረብ አለባቸው፤” ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ቦርዱ በኢሕአዴግ ጠቋሚነት በሕጉ መሠረት ለማይገባቸው ፓርቲዎች አከፋፍሏል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም፡፡

ፓርቲዎች ሕግን እንዲያከብሩ በተደጋጋሚ እየመከሩ መሆኑን የሚገልጹት ፕሮፌሰር መርጋ፣ “ሕጉ ሙሉ ለሙሉ ቢከበር ለቦርዱም ሥራ ቀለለለት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሆደ ሰፊነት ነው የምንሠራው፡፡ ምክንያቱም ለዴሞክራሲና ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት መጎልበት ሲባል፤” ብለዋል፡፡

ቦርዱ በዚሁ ሁኔታ ይቀጥላል ማለት እንዳልሆነ የጠቆሙት ሰብሳቢው ሕግን ማክበር በማይችሉ ላይ ዕርምጃ ይወስዳል ብለዋል፡፡ “ለምሳሌ አራት ፓርቲዎች ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ከቦርዱ ጋር ግንኙነት በማቋረጣቸውና በተደጋጋሚ በሚዲያ ጥሪ ቢተላለፍላቸውም ባለመገኘታቸው ተሰርዘዋል፤” የሚሉት ፕሮፌሰር መርጋ፣ በአሁኑ ወቅት ፈቃድ ካላቸው 76 ፓርቲዎች ውስጥ 22 የሚሆኑት ሕጉን ሙሉ ለሙሉ ያሟሉ መሆናቸውን፣ የተቀሩት ግን በከፊል ማሟላታቸውንና ከእነዚህ ጋር በቀጣይ ሕግ የማስከበር ሥራን በመወያየት እንደሚያከናውኑ አብራርተዋል፡፡

source,http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/2381-ምርጫ-ቦርድ-ሕግ-በመጣስ-በኢሕአዴግ-ለተመረጡ-ፓርቲዎች-ገንዘብ-ሰጥቷል-በሚል-ጥያቄ-ቀረበበት

posted by Daniel tesfaye

ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል። ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ ከስልጣን ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት ስልጣኑ በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም – በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ ከመሆኑ በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን መሆኑን ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር ረቀቅ ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ የእንቅስቃሴው ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም ለመንግስት ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። በዚህም ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም የሚያውቁት እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ – መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና ማሳያ መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል። በመጨረሻም፥ የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ ንግድ መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።

source,,,: http://www.zehabesha.com/

posted by Daniel tesfaye

 

አንድነት ፓርቲ በጎንደር ቅስቀሳ እያደረገ ነው

576820_643438789017118_1777115518_n
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሰኔ 30 ቀን በጎንደር ከተማ አደባባይ ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ በከተማዋና በዙሪያ ወረዳዎች የጥሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ እንደሚገኝ የሰሜን ኢትዮጵያ አደራጅ እና የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አእምሮ አወቀ ለኢሳት ገልጸዋል።

በምእራብ አርማጭሆ በአብራሀ ጅራ ከተማ አለልኝ አባይ፣ እንግዳው ዋኘው፣ አብርሀም ልጃለም እና አንጋው ተገኘ የተባሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ወረቀቶችን ሲበትኑ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰአት አካባቢ በደህንነቶች ታስረው መወሰዳቸውን አቶ አእምሮ ተናግረዋል

የሰላማዊ ሰልፉ ማሳወቂያ ደብዳቤ አልቀበልም ብሎ ለነበረው የጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ደብዳቤውን በፖስታ መላካቸውንና መድረሱን ማረጋገጣቸውን ተወካዩ ገልጸዋል።

በመጪው ሰኔ 30 በሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በርካታ ህዝብ ይገኛል ብለው እንደሚጠብቁ አቶ አእምሮ ተናግረዋል።

የጎንደር ከተማ የቀበሌ 6 እና 7 ነዋሪዎች በቅርቡ በራሳቸው ተነሳሽነት የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

posted by Daniel tesfaye

ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

“ግብረሰዶማዊነት ወደፊት!”

obama in senegal

J
በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡

ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር አድርገዋል፡፡

አፍሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ኦባማ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት የግብረሰዶማውያንን መብት ሊያስከብር የሚችል ውሳኔ ማስተላለፉ እንዳስደሰታቸው በጉብኝታቸው ወቅት ጠቁመዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ ለጋብቻ መጠበቅ ከለላ የሚያደርገውን Defense of Marriage Act (DOMA) የተባለው ሕግ ለወንድና ሴት ተጋቢዎች ብቻ በማለት ያስቀመጠው ከለላ የግብረሰዶማውያንን መብት ይጻረራል በማለት ነበር፡፡ ስለሆነም በፍርድቤቱ ውሳኔ መሠረት  በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል የተፈጸመ “ጋብቻ” ከፌዴራል መንግሥት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞችን ሊያስከለክል አይገባም በማለት ወንድ ሚስትም ሆነ ሴት ባል ያላቸው ሁሉ የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ ፈቅዶላቸዋል፡፡ እንዲሁም በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት የሰዶማውያን ጋብቻ እንዲቀጥል ፈቃድ የሚሰጥ ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድቤቱ አስተላልፏል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ግብረሰዶማዊነት በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በበኩላቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይከሰሱ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናግረዋል፡፡ “በጣም በመቻቻል” የምንኖር ነን ያሉት የሴኔጋሉ መሪ አገራት ውስብስብ የሆኑ ሕጎችን በራሳቸው ጊዜ በተግባር ላይ እንደሚያውሉ በመጥቀስ የኦባማን ሃሳብ ተግሳጽ በተሞላበት ምላሽ አስተናግደውታል፡፡

በመቀጠልም አገራቸው ሴኔጋል ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት ያቆመች መሆኗን በመናገር አሜሪካ ግን ይህንን እስካሁን ተግባራዊ አለማድረጓን በመጥቀስ ኦባማን ተሳልቀውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ወንጀለኞችን በሞት የመቅጣት ህግ ከ30 በላይ ግዛቶች ውስጥ ተግባራዊ ሲሆን በተለይም በቴክሳስ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት እንደገና ከተጀመረ ከ1974ዓም በኋላ የቴክሳስ ጠቅላይግዛት 500ኛዋን ወንጀለኛ ሰሞኑን በመግደል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡

“ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

በፈረንሣይ አብዮት አካባቢ ህዝቡ መራቡን በተለይም የፈረንሣይ ጭሰኞች መቸገራቸውና በረሃብ እየተንገላቱ መሆናቸውን የተነገራት ልዕልት ማሪ አንቷኔ (“Qu’ils mangent de la brioche”) “ከራባቸው ኬክ ይብሉ” ብላ መልሳለች እየተባለ ለዘመናት ሲዘበትባት ኖሯል፡፡ ልዕልቲቱ ይህንን ለማለትዋ የተረጋገጠ ነገር ባይሆንም ነጻነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ … ለጠማው የአፍሪካ ሕዝብ ባራክ ኦባማ “የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር ይገባል” በማለት መሠረታዊውን የህዝብ ጥያቄ ችላ ማለታቸው “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” የማለት ያህል እንደሆነለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ጠቁመዋል፡፡

በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት “ለውጥ” እና “ተስፋ” ቀዳሚ ዓላማቸው አድርገው የበርካታዎችን ቀልብ የሳቡት ባራክ ኦባማ፤ ለአፍሪካ መሠረታዊ ችግር እስካሁን ጆሮ አለመስጠታቸው ብዙ የተባለበት ነው፡፡ ሰሞኑን በአሜሪካ ምክርቤት“ኢትዮጵያ፤ ድኅረ መለስ” በሚል ርዕስ በተደረገው ምክክር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የተናገሩትን በድጋሚ ያስታወሱም አሉ፡፡ በወቅቱ አቶ ኦባንግ ያሉት “ኦባማ ለምርጫ በተወዳደረ ጊዜ ጥቂት ደመወዝ የሚከፈላቸው ኢትዮጵያውያን የምርጫ ዘመቻውን ደግፈው ነበር፤ እስካሁን ከኦባማ የሰሙት ነገር የለም”በማለት ነበር፡፡

ከምዕራባውያን የሚመነጨውን ማንኛውንም ነገር – ከፖለቲካ እስከ ማኅበራዊ አመለካከት – ትክክለኛ አድርገው ለሚቀበሉ ግብረሰዶማዊነት ሥልጣኔ ይመስላቸዋል በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ የሃይማኖትና የማኅበረሰብ ሳይንስ ጉዳዮች ምሁር “ጋብቻ” የሚለውን ቃል ለሁለት ወንዶች መጠቀም እርስበራሱ የሚጋጭ ጉዳይ ነው በማለት ተመሳሳይ ጾታ ብሎ ጋብቻ ማለት የተሳከረ አነጋገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “ይህ የሰዶማውያን መብት ይከበር የሚለው ጉዳይ በሕግ እየጸደቀ ሲሄድ ድርጊቱን ከሃይማኖታቸው አኳያ የሚቃወሙ ሰባኪያን የሃይማኖት ትምህርታቸውን በሚያስተምሩበት ቤ/ክ ይሁን መስጊድ ወይም ምኩራብ ግብረሰዶማዊነትን እየተቃወሙ ሰበካ ማድረግ በህግ የሚያስጠይቃቸው ይሆናል” በማለት ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን የማኅበረሰብ ቀውስ ጠቁመዋል፡፡

bush in africaበሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ዳግም የመመረጥ ፈተና የሌለባቸው የአሜሪካ መሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን የአፍሪካን የዱር እንስሳት እየጎበኙ ወደፊት ለሚሠሩት ፕሬዚዳንታዊ ቤተመጻህፍት (ፋውንዴሽን) ፎቶ እንደሚሰበስቡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ የባራክ ኦባማም ጉብኝት ከዚህ የተለየ አለመሆኑ ግልጽ ሲሆን “የአፍሪካ ልጅ” እየተባሉ ሲሞካሹ የኖሩት ፕሬዚዳንት ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ሲገቡ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ገጥሟቸዋል፡፡ ቅዳሜ የክብር ዶክትሬት በሚቀበሉበት የዮሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል፡፡

ዛሬ ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ደቡብ አፍሪካውያን “ይቻላል” (Yes! We can!) ለሚለው የኦባማ የምርጫ መፈክር “አትችልም!” (“No, You Can’t Obama,”) የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ “ኦባማ የመጣው አፍሪካንና ደቡብ አፍሪካን ለመዝረፍ ነው” በማለት ጠንካራ ተቃውሞውን የገለጸው አንዱ ተሰላፊ “አፍሪካውያን በብዙ መልኩ እየተሰቃዩ እያለ እርሱ ግን የአፍሪካን ሐብት፤ ወርቅ፣ አልማዝ፣ … ለመዝረፍ ነው የመጣው” ብሏል፡፡obama s africa

የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ፣ … ዕጦት ላንገላታውና በአምባገነኖች መዳፍ ሥር ለሚሰቃየው የአፍሪካ ሕዝብ በቃላት እንኳን ድጋፋቸውን ከመስጠት እስካሁን የተቆጠቡት ኦባማ አሜሪካ በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አገሮች ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ፍላጎቱ እንደሌላት በማያወላውል መልኩ ያረጋገጠ መሆኑ የብዙዎች ግንዛቤ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ኃይል ጥያቄ ውስጥ የሚጥልም ነው፡፡

በአውሮጳ የፖለቲካ ምጣኔሃብት ተመራማሪ የሆኑ እንደሚሉት “አሜሪካኖች እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዓይነቱን አምባገነናዊ አገዛዝ እስኪያስመልሰው ድረስ በዕርዳታ ገንዘብ ካሽሞነሞኑ በኋላ “ኢህአዴግን ምን እናድርገው” በማለት “ምክር ስጡን” እያሉ በሕዝብ ሰቆቃ ላይ ያላግጣሉ፡፡ ሲሻቸውም ደግሞ አፍሪካ ድረስ በመሄድ “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” በማለት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን ችግር ያልሆነውን የግብረሰዶማውያን መብት መከበር ይሰብኩናል፡፡ ታዲያ ለዚህ ልግጫ መልሳችን መሆን የሚገባው “ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ነጻነታችንን አንለምንም፤ አሜሪካ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት እንድትሆንብን አንፈልግም” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ምክርቤት በተካሄደው ምክክር የተናገሩትን ዓይነት ቁርጠኝነት ነው በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡

obama africa trip100ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በአሁኑ ጊዜ በበጀት ቀውስ ምክንያት በርካታ ሠራተኞች ደመወዛቸው እየተቆረጠ ባለባት አሜሪካ አነጋጋሪ መሆኑን ዋሺንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡ የደኅንነት ሰዎችን እንዲሁም 14ሊሞዚን፣ 56 ጥይት የማይበሳቸው ድጋፍ ሰጪ  መኪናዎች፣ ሙሉ የህክምና ባለሙያዎችን የያዘና ጀቶችን የጫነ መርከብ … ለፕሬዚዳንቱና ለቤተሰባቸው ጥበቃ በማድረግ ሥራ ላይ እንደሚውሉ ጋዜጣው ያብራራል፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ በደቡብ አፍሪካ የሁለት ቀን ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰኞ ወደ ታንዛኒያ ያመራሉ፡፡ የአባታቸው የትውልድ አገር ነው የሚባለውን ኬኒያ ሳይረግጡ በዚያው ወደ አገራቸው እንደሚያቀኑ የጉዞ መርሃግብራቸው ያስረዳል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

posted by Daniel tesfaye

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?

_1_~1
June 29, 2013
ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?

ባለፈው ጊዜ አንድ ወዳጄ ጋር አዲሳባ ስልክ ደውዬ ሳናግረው በአካባቢው ከእርሱ ድምጽ ጎልቶ የሚሰማ የመኪና ጥሩንባ ሰማሁና ይሄ ሁሉ የመኪና ጥሩምባ ምንድነው… ብዬ ጠየኩት፡፡

ሃይለማሪያም ደሳለኝ እየገቡ ወይም እየወጡ ነው መሰለኝ መንገድ ተዘጋግቷል፡፡ አለኝ፡፡

ወዲያውም ቀጠል አድርጎ፤ እንደ ሀቁ ቢሆን ኖሮ መንገድ መዘጋጋት የነበረበት ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ሳይሆን ለተመስገን ደሳለኝ ነበር… አለኝና በቁጭት፤ ይሄው የሚያጅቡትን አያቀውቁምና… እልኩ እያታዘብኩ ነው…! ሲል አወጋኝ!

ተመስገን ደሳለኝ ገዢውም ተገዢውም ፓርቲ ሊያመሰግነው የሚገባ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ነገር ግን ገዢዎቻችን ማመስገን የሚቆጥር ይመስል ሰውን ማመስገን አይወዱም፡፡ ስለዚህ ተሜንም በማመስገን ፈንታ ከሰሱት፡፡ ጎሽ በማለት ፈንታ እንደ ጎሽ ሊወጉት ቀንዳቸውን አሾሉበት፡፡ እሰይ በማለት ምትክ ሰይ ባንከረባብት ብለው ለሁለቱም አሰቡት፡፡ (ለማሰርም ለማሰደድም) (ሰይ ባንከረባብት በልጅነታችን ብይ ጨዋታ ላይ ተወርዋሪዋ ብይ ጉድጓዳ ውስጥ ብትገባም የተቃራኒውን ብይ ብትመታም ነጥቡ እንዲያዝልን ውል የምንገባባት ቃል ነበረች፡፡)

ተመስገን ደሳለኝ እንዲሰደድ መንግስት ከፀሎት ጀምሮ ሁሉንም አይነት የትግል ስልቶችን እንደተጠቀመበት ትዝ ይለኛል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ጊዜ ምንም የቀጠሮ ወረቀት ወይም መጥሪያ ሳይሰጠው በራዲዮን፤ “ተመስገን ደሳለኝ በሌለበት የፍርድ ሂደቱ ታየ ለሚቀጥለው ጊዜ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርበው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል!” የሚል አይነት ዜና በሰላም ቁጭ ብሎ ሻይ በሚጠጣበት ካፌ ውስጥ ሰማ፤ (እናጋን ካልን ደግሞ ዜናውን እንደውም ያነበቡት ተሜ ልክ ዜና ሲሰማ አይተው ነው…! ማለት እንችላለን…) የዚህ ዜና አላማ ግልፅ ነበር፡፡ ተሜ ደንግጦ ፖሊስ ሳይዘው በፊት መንገዱን እንዲያያዘው ማድረግ ነበር፡፡ ወዳጃችን ግን፤ ብታስሩኝ ባለ ጊዜም ባለ ብረትም ናችሁና እግሬ እምቢ ማለት አይቻለውም፡፡ ለመሰደድ ግን እሺ የሚል እግር የለኝም፡፡ ብሎ እንቅጩን ነገራቸው እና የመጣው ምጣ ብሎ ቁጭ አለ…

በነገራችን ላይ ተመስገን እስከ አሁን ድረስ በመንግስት የተሰነዘረበት ክስ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ እንደው የሪከርድ መዝጋቢ መስሪያ ቤቶች የሚያስታውሳቸው አጥተው እንጂ ከዚህ ሁሉ ክስ ጋር አብሮ መኖር የቻለ ጋዜጠኛ ብለው ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሚያሰፍሩት ሁሉ ይመስለኛል፡፡ መንግስታችን በክስ ላይ ክስ ሲደራርብ ሲደራርብ ክሱ ተቆልሎ አለመናዱም የእግዜር ተዓምር ነው፡፡ አንዱ ሳይቋጭ አንዱን አንዱ ሳይቋጭ አንዱ ክስ ሲመጣ በአሁኑ ሰዓት ተመስገን ደሳለኝ ከሃምሳ በላይ ክሶች ጋር ተመስገን ብሎ እየኖረ ነው፡፡

የተሜ እና የእኛ ፍትህ ጋዜጣ “መለስ ሞቱ” በማለቷ እኛ ሳንል ምን ሲደረግ እንዲህ ትያለሽ ተብላ ከሳላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ተደረገች፡፡ (የመለስ አምልኮ ይሎዎታል ተመስገን…!) አንዱ ሲዘጋ በአንዱ እንከሰታለን በምትለው ስትራቴጂ መሰረት፤ አዲስ ታይምስ ተተካች፡፡ አዲስ ታይምስ ደግሞ “ብር ከየት አምጥታችሁ ነው…” ተብላ ህትመቷ ተከለከለ፡፡ መንግስታችን እንደሆነ ኮሚክ ነው ጮክ ብለን በያይነቱ ስናዝ ራሱ “ብር ከየት አምጥተው ነው” ብሎ ይጨንቀዋል፡፡ በእርሱ ቤት እርሱ አበል ያልሰጠው ሰው፤ ወይም ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ያልተበደረ ሰው ምንም ገንዘብ የለውም…!

ተመስገን እና ጓደኞቹ እጅ መስጠት ብሎ ነገር አያውቁም ነበር፤ እና ከየትም ከየትም ብለው ድጋሚ ልዕልና ጋዜጣን አበረከቱልን፡፡ መንግስት መንግስት ሆኖ እንጂ… በብስጭት ካቲካላ ይጠጣ ነበር፡፡ ግን ሳይጠጣም ሞቅ አለው፡፡ ሰከረም፡፡ እናም ልዕልናንም ጥርቅም አድርጎ ዘጋት፡፡ (ይህ ውሳኔ የሞቅታ ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም)

ተመስገን ደሳለኝ ሲናገር ሰዎቻችን ደስ አይላቸውም፡፡ እናም በተቻለ አቅም ዝም ማሰኘት ይፈልጋሉ፡፡ ልጁ ግን በቀላሉ ዝም ብሎ የሚያስደስታቸው አልነበረም፤ በማህበራዊ ድረገፆች የሚተነፍሰውን ይተነፍስ ጀመር፡፡

ኢህአዴግ ሰው እንደማትንቅ ያወኩት እኔ ምስኪኑን ሳይቀር ለመከታተል የደህንነት ሰው የመደበች ዕለት ነው፡፡ ለተመስገን ደሳለኝማ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት ነው የተጠቀመችበት፡፡ በእውነቱ ከሆነ፤ ለአንድ ግለሰብ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት መጠቀም ትልቅ የሀይል ብክነት ነው፡፡ ፍጹም ተመጣጣኝ ያልሆነ ርምጃ፤ ጎጆ ቤትን በሚሳኤል እንደ መደብደብ በሉት…

ተሜ በኢህአዴግ ክሶች ብዛት፤ በኢህአዴግ ሚዲያዎች ማስፈራራት፣ በኢህአዴግ የደህንነት ሰዎች ከበባ፣ በኢህአዴግ ማተሚያ ቤቶች አድማ አበሳውን አየ፡፡

“አንበሳው” መንግስታችን ተመስገን ግለሰብ ነው ብሎ አልናቀውም፡፡ ያለውን አቅም ሁሉ ተጠቅሞ ሊገድበው ተንቀሳቅሷል፡፡ እርሱን ለመገደብ ያላደረገው ነገር ቢኖር ቦንድ ግዙ ብቻ አላለንም፡፡ ለአባይ የምንገዛው ቦንድ ብዙ ነገር ይገድባልና!

አሁን ተመስገን ደሳለኝ ከሜዳው ላይ ጠፍቷል፡፡ ከመንግስታችን ሃይል የተሞላበት አጨዋወት አንጻር እስከዛሬም በቃሬዛ አለመውጣቱ የሚገርም ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ ችሎ ሜዳው ላይ ስናየው እኛ ደስ ይለን ነበር፡፡ አሁን ታድያ ሲጠፋብን ጊዜ በአዲስ መስመር ላይ ጮክ ብለን እንጮሃለን እንጂ እንደምን ዝም እንላለን…

ተመስገን ደሳለኝ ሆይ ማን ደስ ይበለው ብለህ ጠፋህ…!
http://www.abetokichaw.com/2013/06/29

posted by Daniel tesfaye

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው

June 28, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ “አላማና ግብ” አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ “በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ።” ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..« አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።sebehat nega one of the founders of TPLF

ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ። አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..

አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።

posted by Daniel tesfaye

አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡

C76B7AE3-8C3B-441E-A763-5A2C1034660C_w640_s
ዓርብ, ጁን 28, 2013
አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡
አሜሪካ ውስጥ ያለ ሕጋዊ ፍቃድና ሰነዶች የሚኖሩ ከአሥራ አንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ወደ ዜግነት ሊወስድ እንደሚችል የታመነበት የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሕግ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አለፈ፡፡

በምክር ቤቱ ውስጥ ዛሬ በተሰጠው ድምፅ 68 ሴናተሮች የድጋፍ ድምፃቸውን ሲሰጡ 32 ሴናተሮች ደግሞ ተቃውመውታል፡፡

ይህ ሕግ አያይዞም ዩናይትድ ስቴትስ የተጠናከረ የወሰን ጥበቃ እንዲኖራት የሚያዝዝ ሲሆን ከሜክሲኮ ጋር ባላት ድንበር ላይ ሃያ ሺህ ተጨማሪ የወሰን ቃፊሮች እንዲሠማሩ እና የአንድ ሺህ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አዲስ አጥር እንዲሠራ ይፈቅዳል፡፡

የተበላሸውን የሃገሪቱን የኢሚግሬሽን ሥርዓት ለመጠገን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ነው ሲሉ የሕጉ ደጋፊ የሆኑት በአፍሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለዛሬው የሴኔቱ ውሣኔ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሕጉ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለተወካዮች ምክር ቤቱ የሕግ መምሪያው እንደራሴዎች ለድምፅ ይቀርባል፡፡

ሕግ ለጣሱ ምህረት የሚሰጥ ነው የሚሉትን ማንኛውንም እርምጃ እንደሚቃወሙ ወግ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች ይናገራሉ፡፡

source,,http://amharic.voanews.com/content/us-senate-passes-immigration-reform/1690849.html

posted by Daniel tesfaye

ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት

ECADF_Ethiopian_News
June 28, 2013
ይነጋል በላቸው
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የ…
የሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡

…በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንበርና በነሲብ ነበር እስትንፋሷ ውሎ እሚያድረው፡፡ ሰውዬው የሚፈልገው ሁሉ እዛው ባለበት እየቀረበለትና እንደአንበሣ በብረት አጥር ውስጥ እየኖረ በስልክና በደብዳቤ ሲገዛንና ሲሸጠን ኖረ፤ ፈጣሪ በወደደው ሰዓት ያን የእፉኝት ልጅ ወሰደ፡፡ ጦስ ጥንቡሱ ግን አሁንም እንደገነነ አለ፤ መቃብር ውስጥ ሆኖ በመግዛት መለስ አንደኛ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ይቺ ራዕይ የሚሏት ሀገርን የማጥፋት ተልእኮ በየወያኔው ጭንቅላት ውስጥ ሠርፃ ገብታ እነሱንም እኛንም ዕረፍት ነስታለች፡፡ አዳሜ እየተነሣ “ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት!” ይላል፡፡ “ራዕያቸው ምን ነበር?”ተብሎ ሲጠየቅ በቅጡ የሚመልስ የለም፡፡ የፈረደበት የአባይ የሚሌኒየም ይሁን የሕዳሴ ግድብ አለ፡፡ እሱው መሰለኝ ትልቁ ራዕይ፡፡ በሌሎች ሀገሮች እዚህና እዚያ የተትረፈረፈ የወንዝና የኩሬ ግድብ እኛ ሀገር ሲደርስ ብርቅ ሆኖ ሰውን በመዋጮና በተስፋ ቁንጣን እየገደለ ነው፡፡ ራዕዩ ይሄው ነው፡፡ በተረፈ በሚሊዮኖች ላብና ደም ጥቂት ቅንጡ ሀብታሞችን የመፍጠር ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለብዙ አሠርት ዓመታት ተከፍሎ በማያልቅ ብድር መንገድና ሕንጻ መሥራት ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ይበልጡን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚመስል መልኩ የሀገርን ሀብት ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በማዋል በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና በኮብል ስቶን ሥራ አደራጅቶ ዜጎችን በጥቅም መከፋፈል ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዕይታ ሳይቀር የሚዘገንን የኔቢጤ (ለማኝ)፣ ወፈፌና ሰካራም፣ ብስጩና ግልፍተኛ፣ በረንዳ አዳሪና የዐዋቂና ሕጻናት ሴተኛ አዳሪዎችን በየዋና ዋና ከተሞች በብዛትና በስፋት ማምረት በልዩ ራዕይነት ካልተመዘገበ በስተቀር የመለስ ራዕይ ብሎ ነገር የሚጨበጥ ነገር አላየሁም – በዋና ራዕይነት እንዲመዘገብለት ከተፈለገ ዋናው የመለስ ራዕይ የተከፋፈለችና የደከመች፣ ለኤርትራ በምንም መንገድ የማታሰጋ ጥንጥዬ ኢትዮጵያን በሂደት መፍጠር ነው – ይሄ የሚታየው ብልጭልጭ ነገርና የዕድገት እመርታ የሚመስል የፎቅና የአስፋልት ወይም ሌላ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሁሉ መለስ ሳይወድ በግዱ በሥሩ ባሉ ጥቂት ሀገር ወዳድ ወያኔዎች አማካይነት የተከሠተ – ‹ከሬዲቱ› ለርሱ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን ለማለት ነው- በመለስ የጥፋት ራዕይና በአፈጻጸሙ መካከል እንደሳይድ ኢፌክ ሊቆጠር የሚችል አጋጣሚ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው – መለስ ኢትዮጵያን በማጥፋት ሂደት ተጠምዶ ሳለ ያን ሂደት ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ መስሎ መታየት ወይም ማታለል ስላለበት ለዚያም ሲባል አንዳንድ የሚታዩና የሚጨበጡ ነገሮችን ማድረግ ስለነበረበት በኢትዮጵያዊ ስብዕና ዓለም አቀፍ አመኔታን ለማግኘት ሲል ባልጠበቀው ሁኔታ ከእጁ ሾልከው ክፉ ገጽታውን በጥሩ ቅባት ያዋዙለት አጋጣሚዎች ነበሩ ወይም ናቸው(ለዚህም ይመስላል ብዙ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰው ‹ምትሃት› ተወናብደው የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮ እንዳያውቁ የተደረገውና ዐይናቸው በወያኔ ጥፋት ላይ እንዳያማትር እንዲያውም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የርሱ ነገረ ፈጅ እስከመሆን እንዲደርሱ የተሞከረውና አሁን አሁን ደግሞ እየቆጫቸው መምጣቱን እየተገነዘብን ያለነው…) ፡- በሕክምና አነጋገር ለጉበት የወሰድከው መድሓኒት ኩላሊትህን ሊጎዳ ይችላል – ኔጌቲቭ ሳይድ ኢፌክት፡፡ ለራስ ምታት የወሰድከው መድሓኒት ከጨጓራ ህመምህ ሊፈውስህ ይችላል – ፖዚቲቭ ሳይድኢፌክት፡፡ የመለስም የአባይ ግድብና ሌላው ግርግር ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ እውነት ያለፈ አይደለም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ፍቅርና የሀገር መውደድ ስሜት ቢኖረው ኖሮ… ታውቁት የለ – ምን ወደዚያ ውስጥ ከተተኝ … ፡፡ ይቅርታ – በዋናው የሃሳብ መስመሬ ላይ እንደአረብ ጣቢያ ጣልቃ እየገባ ኳርት የሚለዋውጥብኝና እንድዘባርቅ የሚያደርገኝ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግር በመሆኑ ታገሱኝ፡፡

ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው? የት ተቀምጦ? በስምና በአካል ይታወቃል ወይ? ብለን እንጠይቅ፡፡
እኔ በ
ግል እንደምታዘበው ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደራት የሚገኘው ሰው አይመስለኝም፤ መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ ግማሹ ቅዱስ ነው፤ ግማሹ ደግሞ እርኩስ ነው – አሁንም በኔ ዕይታ፤ ዕይታየ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የኔ ጉዳይና የናንተ የኅሊና ፍርድ ነው፡፡

ቅዱስ ያልኩት በተከመሩብን ሁለንተናዊ የፖለቲካና ማኅረሰብአዊ ችግሮች የተነሣ እርስ በርስ ተበላልተን እንዳናልቅ እየረዳን ያለ አንዳች ኃይል መኖሩን ከመገመት ባለፈ ስለማምን ነው፡፡ ይህ ኃይል ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ እንደሚታየው ጭቆናና የኑሮ ውድነት አንድም ሰው በአንጻራዊ ሰላም ከቤት ወጥቶ ወደቤት በሰላም ባልገባ ነበር – እውነቴን ነው የምለው ይህን ዓይነት ደግ መንፈስ ባይጠብቀን ኖሮ ተበላልተን ለማለቅ የሚፈጅብን ጊዜ ሰዓታትን ብቻ በወሰደ ነበር(ሦርያንና ሊቢያን… ያዬ ይፍረድ – ሊያውም ከኛ በእጅጉ ያነሰ ጭቆናና እንግልት ደርሶባቸው!) ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው በረንዳ አዳሪ፣ ሥራ አጥና ቤት አልባውም በ”ሰላም” ካደረበት ከየቱቦውና ከየላስቲክ ቤቱ ወጥቶ በቀጣዩ ቀን በየአደባባዩ ባላየነው ነበር፡፡ ካለአንዳች አለሁህ ባይ የመንግሥት መዋቅር በራሱ ኃይልና እንዲሁ በኪነ ጥበቡ ርሀብና ችግሩን ችሎ የሚኖር ሕዝብ ማየት የሚገርምም የሚሰቀጥጥም በድንቃ ድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውም የሚሌኒየሙ ተዓምር ነው፡፡ አንድም ሥራና አንድም ደመወዝ የሌለው በሚሊየን የሚገመት ዜጋ ቀኑን አለበቂ ምክንያት እዚህና እዚያ ሲንከራተትና ሲንገላወድ ውሎ አሁንም ልድገመውና በየሥርቻውና በየሥርጓጉጡ በ”ሰላም” አድሮ የቀጣይዋን ዕለት ጀምበር ለማየት እባቡር መንገዱ ላይ ተሰጥቶ መታየቱ የትንግርትን እንጂ የመንግሥትን ኅልውና አያመላክትም፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገራችንን በትረ ሥልጣን ከያዙ ሥውር ኃይሎች ውስጥ የተወሰነውን ‹የፓርላማ ወንበር› የተቆናጠጠው አንዳች የተቀደሰ ነገር መሆን አለበት ብዬ አምለሁ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ማን እየተዘባነነ ማንስ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በርሀብና በጥም እየተሰቃዬ ይኖር ነበር? ሀሰት ነው?

በሌላ በኩል የሚታየውን መቋጫ የሌለው የግፍ አገዛዝና የዘረኝነት ቱማታ ስንቃኝ ከነዚህም ጋር የሚቆራኘውን አጠቃላይ የድቀት ሕይወት ስንታዘብ በተለይ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ አመራር ረገድ የእርኩሱ መንፈስ ምን ያህል የበረታ እንደሆነ መረዳት አይቸግርም፡፡ ስለዚያም ምክንያት ይመስለኛል ይህ በመለስ የሙት መንፈስ የሚነዳ የአጋንንት መንጋ አንዳች ሥፍራ ተደብቆ ደህና ሰው ወደ አመራር ዝር እንዳይል እነአዜብንና በረከትን እየተመሰለ በላያችን ላይ የሚያንዣብብብን፡፡ እንደሚወራው አዜብ ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሆና አይደለም ጽዳትና ዘበኛም ሆና ብትመጣ እንኳን ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት፡፡ በሌላ ቦታ እያለች የማዘጋጃ ቤት ሹሞችን በስልክ እያስፈራራችና በአካል እያስጠራች ስንትና ስንት ግፍና በደል መፈጸሟ እየታወቀ አንድያውን በዚያ ቢሮ ስትገኝማ ከተማዋን ብቻ ሣይሆን እኛን ነዋሪዎቹን በጅምላና በችርቻሮ ባወጣንበት ዋጋ ቸብችባ በጥቂት ወራት ውስጥ ትጨርሰናለች፡፡ አዜብ – ዮዲት ጉዲት – እንኳንስ ማዘጋጃ ቤት ገብታ በሩቅ እያለችም – ለብልግናየ ይቅርታና – ለውሽማዋም ይሁን ለምትፈልገው ማንኛውም ሰው ቦታ ለማሰጠት፣ መብራት ለማሰጠት፣ የንግድ ፈቃድ ለማሰጠት፣ (እንዳስፈላጊነቱ ተመላሽ ሊደረግ ወይ ላይደረግ የሚችል) የባንክ ብድር ለማሰጠት፣ በመንግሥት ወጪ ረጃጅም የስልክና የውኃ መስመር ለማዘርጋት፣ የፈለገችውን ለማሾም ወይም ለማሻር፣ ንጹሕን ሰው ካለበደልና ጥፋቱ ዘብጥያ ለማስወረድ፣ በጥፋቱ የታሠረን በቅጽበታዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት በሕግ ሽፋን ለማዘረፍና ለራሷ ካምፓኒዎች ወይም ለመሰላት ለማሰጠት፣ በነባርና አዳዲስ የአክሲዮን ካምፓኒዎች ራሷን በአባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ለማስገባት፣ ወዘተ. ታደርገው የነበረውና አሁንም ከማድረግ የማትመለሰው አቅል ያጣ ሩጫ በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ሴትዮዋ ለገንዘብና ለእንትን ሲሏት ገደል እንደምትገባ የሚያውቋት ይመሰክራሉ – አጉል ተፈጥሮ፤ ከምን ዓይነት ሥጋና ደም ተፈጥራ ይሆን ወገኖቼ? በዚህ ዓይነቱ ለከት የሌለው የገንዘብና የሀብት ፍቅሯ ነው እንግዲህ ሰውዬውን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንደውሻ አሥራ በርሱ ስምና በርሷ ድፍረት ባጠራቀመችው ንዋይ ከዓለም መሪዎች መለስን በሀብት የሚበልጠው እንዳይገኝ ከፍተኛ ጥረት ላይ የነበረችው – በየባንኩ ብዙ ገንዘብ ታቁር የነበረችው፣ በየዓለም ማዕዘናት ብዙ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ትመሠርት የነበረችው፣ በፍቅረ ንዋይ መታወሯ እንዳንዳች እያደረጋት እንዲያ ዐይን ባወጣ መንገድ ትዝብት ላይ ወድቃ የነበረችው፡፡ ይህች በገንዘብና በእንትን ፍቅር ያበደች የድብቁ ቢግ ብራዘር ተወዳዳሪ ሴት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብትገባ ምን ተዓምር ልትሠራ እንደምትችል ገምቱ – የምን መገመት ነው – ፍንትው ብሎ እየታዬ! የስንቱን ቤት እንደምታፈናቅልና ባወጣ እንደምትሸጥ፣ ስንቱን የኪስ ቦታ እንደምትቸበችብ፣ እንደ አንደኛው ባሏ ‹የዐይናችሁ ቀለም አስጠላኝ› እያለች ስንቱን ምሥኪን ሰው ከሥራና ከደመወዝ እንደምታግድ፣ እንደምታሳስርና ደብዛ እንደምታስጠፋ፣ ስንትና ስንት የሀገር ማፈሪያ ወንጀልና የቁጭ በሉ አሣፋሪ ድርጊቶችን እንደምትሠራ፣ ስንቱን ኮበሌ ካልተኛኸኝ እያለች ከትዳሩና ከጤናማ ኑሮው እንደምታፈናቅል (“አሮጊት ለምኔ! ገንዘብና ሥልጣን ባፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ አሻፈረኝ የሚልን መቀመቅ እንደምታወርድ)፣ … በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል – እባካችሁን ‹ህልም እልም› ብለን ሁላችን እናማትብበት፡፡ አዜብ ብሎ ከንቲባ? ወያኔ ይህን ካደረገ በርግጥም ራሱን ለማጥፋት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህችን የአጋንንት ውላጅ የባንዳ ልጅ ማሳረፍ ይገባል – በሰላም፡፡ በቃ – በመለስ ቀብር እንዳለችው ልጆቿን በማሳደግ ፈተና ላይ ብቻ ታተኩርና በዚያው ትታይ፡፡

አዜብ በሌብነቷ አይደለም ሹም አትሁን እያልኩ የምከራከረው፤ በሌብነቷ ከሆነ መብቷ ነው፡፡ ዓለማችን በሌቦችና አጭበርባሪዎች የተሞላች በመሆኗ የርሷ ሌባ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም – በአመራርም ሆነ በተራ ዜጋነት ሌባና አጭበርባሪ ሀገር ምድሩን ሞልቶታል፡፡ አዜብ በተፈጥሯዊ ደመ ሞቃትነቷና ያንንም ተከትሎ በጉልህ ስለሚንጸባረቅባት የሴሰኝነት ጠባይዋ አይደለም ሹም እንዳትሆን የምመኘው፡፡ ያም መብቷ ነው – ካልሰለቻት እንኳንስ ነባር ታጋዮችን አዳዲሶቹንና እምቦቀቅላ ታጋዮችንም ታነባብራቸው፡፡ አዜብም ሆነች ቤቲ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መብት እስከፑንት (ላንድ) ቢጠቀሙበት የነሱ ጉዳይ እንጂ የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡ እኔን ክፉኛ የሚያሳስበኝ ድንበር የማያውቀው ውሸቷ ነው፡፡ በተራ ቃል ‹ውሸታም› መባል በፍጹም አይመጥናትም፡፡

በባህር ዳሩ የወያኔ ስብሰባ የተናገረችው ውሸት ስለሷ ባሰብኩ ቁጥር ስለእውነት በጣም ያመኛል፡፡ በዚያ ስብሰባ ‹መለስ ከዓለም መሪዎች በደመወዙ ብቻ ቤተሰቡን እያሰቃየ የኖረ ብቸኛው መሪ ነው፤ ከስድስት ሺ ብር ደመወዝ ለኢሕአዲግ ተቆርጣ በምትደርሰው አራት ሺህ ምናምን ብር ወርን ከወር እየጣጣፍን በመከራ ሲያኖረን የነበረና አእምሮውን ብቻ ይዞ የተወለደ… ይህ ሊሠመርበት ይገባል ፤ ሰው የሚለው አይደለም – እርሱ በዚያች ትንሽ ደመወዝ ብቻ ኖሮ ያለፈ የተለዬ መሪ ነው…› እያለች የቀላመደች ዕለት ስለርሷ ጨረስኩ፡፡ ስለርሷ ብቻም አይደለም፡- ስለወያኔ/ኢሕአዴግም ያኔውን ጨረስኩ፡፡ አንድ አንጋፋ ድርጅት ያን የመሰለ በሬ ወለደ ዓይነት ነጭ ውሸት ሰምቶ እርምጃ አለመውሰዱ ገርሞኛል – የዚያን ድርጅት የለዬለት ባዶነትም አረጋግጫለሁ፤ የሴትዮዋ ንግግር እውነትነት ቢኖረውም እንኳን የሀገርንና የድርጅትን ምስል በማጠየም ረገድ ቀልማዲት ያደረገችው ነገር እጅግ ሰቅጣጭ በመሆኑ በሕይወት የመኖርን መብት ሳይጨምር ከብዙ ነገር ልትታገድ በተገባት ነበር፡፡ ሕዝብ በሆነ ምክንያት በይሁንታ አፉን ቢለጉም እውነት እንዳይመስላቸው፡፡ ሕዝቡ በዕውቀት ከነሱ ስለሚበልጥ በዚያን ሰሞን ይህን የአዜብን የድህነት ወሬ የቡና ማጣጣሚያ ነው ያደረገው – ሳይጠማን እየጠጣን ብዙ ቡና ፈጅተንበታል – ጊዜው ሲደርስ ይህንን ኪሣራችንንም ታወራርዳለች፡፡ የዚህች ቀልማዳ ሴት ንግግር በአሣፋሪነቱና አጸያፊነቱ በሺዎች ዓመታት አንዴ እንደሚያጋጥም እጅግ ነውረኛ አነጋገር ሊወሰድ ይችላል፡፡ የርሷ ስህተት እንደግለሰባዊ ስህተት ተቆጥሮ በዝምታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ የወያኔው ድርጅት በፍርሀት ይሁን በሌለው ይሉኝታ እርሷን በዝምታ ማለፉ ግን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ህፀፅ ነው፡፡ ለነገሩ አሁንም ብዙም አልረፈደምና የሴትዮዋን ተፈጥሮ የምታውቁ ወያኔዎች እባካችሁን አንድ ነገር አድርጉ – ለናንተው ስትሉ፡፡ እኛ ሁሉንም ለምደነዋልና ስለኛ ብላችሁ እንደማትጨነቁ እናውቃለን፡፡ ሀፍረቱ ይበልጡን ለእናንተው ስለሆነ አዜብን ግዴላችሁም ተዋት፡፡

ቁጭ ብዬ በእርጋታ ሳስበው ሕዝብንና የታሪክ ፍርድን ንቆ ይህችን ሴት ባለሥልጣን ማድረግ የኋላ ኋላ ኢሕአዴግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስለኛል፡፡ እናም ኢሕአዴግ ለክብሩ ሲል – ክብር ካለው ነው ለዚያውም – አለበለዚያም ውርደቱን ቅጥየለሽ ላለማድረግ ሲል ይህችን ሴት ከማዘጋጃ ቤት ሹምነት የዕጩ መዝገብ ይፋቃት፡፡ እኔ ውርድ ከራስ ብያለሁ፡፡ ሰውን መናቅ ፈጣሪን መናቅ እንደሆነ ለሃይማኖት የለሹ ወያኔ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – በአምባገነኖች ዘንድ ማይምንና እንደጤናማ ሰው ማሰብ የማይችልን አጋሰስ መሾም የተለመደ ነው፡፡ ሲበዛ ግን ያንገሸግሻል፡፡ ሕዝብ ስቆ ቢያልፈው የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ፣ አይደለም ይህችን በሰው ቋንቋ ከመናገሯ ውጪ ከውሻ ብዙም የማትለየው ሴት ትቅርና ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አምባገነኖችን አይቀጡ ቅጣት አከናንቦ በጭቁኖች መሃል አዋርዷቸዋል፡፡

ይህች መናኛ ሴትም ከወያኔ ጋር የምትዋረድበት ዘመን እየመጣ ቢሆንም ማምሻም ዕድሜ ነውና ማሰብ ያልተሳናችሁ በጣት የምትቆጠሩ ወያኔዎች ካላችሁ የዛሬን ማሩን፤ ቀድሜ እንደገለጽኩት ውርደቱ የጋራችን ነው፡፡ ይበልጡን ግን – ልድገምላችሁ – የእናንተው ነው፡፡ ሴትዮዋን መሾማችሁ የግድ ከሆነ ብትፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓት፡፡ ያ ቦታ ከሕዝብ የራቀ በመሆኑ አንገናኝምና እንደፍጥርጥራችሁ፡፡ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ግን ሺዎችን በየቀኑ የሚያስተናግድ የሕዝብ መናኸሪያ በመሆኑ ባለሥልጣናቱ የሕዝብን ቀልብ እንደነገሩም ቢሆን የሚስቡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህች ሴት እኮ አርከበ ዕቁባይ ለሕዝብ ጥሩ ሠራ በመባሉና ሕዝብም በተወሰነ ደረጃና በግል አበርክቶው ስለወደደው በዚያ ቀንታበት ኤች አይ ቪ ሲመረመር የሚያሳየውን ቢልቦርድ በተሰቀለ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲወገድና ከዕይታ እንዲሠወር አድርጋለች፡፡ የባል ተብዬው የመለስና የሚስት ተብዬዋ የአዜብ የክፋት ደረጃ እንግዲህ እስከዚህ የወረደና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ ነው – ለቅጣት መምጣታቸውን በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ተራ ዜጋ ምቀኛና ቀናተኛ ቢሆን ምንም አይደለም፡፡ የአንድን ሀገር በትረ ሥልጣን የጨበጠ ቁንጮ ያገር መሪና ሚስቱ ግን እንዲህ ያለ በራሱ በመለስ ወራዳ የቋንቋ አጠቃቀም ለመግለጽ እንዲህ ያለ ወራዳና ልክስክስ ጠባይ ሲያሳዩ የሀገርን አጠቃላይ ውድቀት ነው በጉልህ የሚያስረዳን፡፡ ያልዘሩት መቼም አይበቅልም፡፡ የዘራነውን እያጨድን ነን፡፡

ለማንኛውም አዜብን በከንቲባነት መሾም – ምክትልም ሆነች ዋና ለውጥ የለውም – የሚያስከትለው አደጋና ውርደት ታስቦበት በጊዜ አንድ ነገር እንዲደረግ የዜግነት ጥሪየን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡

በሌላም በኩል ይሄ ለይምሰል ያህል በብሔረሰብ ተዋጽዖ አንጻር የሚደረገው ሹመት ይቁም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ማንም አያምንም – ይህን ያረጀ ያፈጀ ሥልት አንቀልባ ውስጥ ያለ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቀዋልና፡፡ እኔ ለምሳሌ በደመቀ መኮንን መሾም ምክንያት አልተደሰትኩም፡፡ አንደኛውና ትልቁ ነገር እንደውሻ አጥንትና ደም አላነፈንፍም፡፡

በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም የሚኒስትር ካቢኔ ከኮንሶና ከሙርሲ ቢሆን ሃሳቡ አይበላኝም፤ ወያኔንም የጠላሁት በመጥፎ ድርጊቱ እንጂ በተሹዋሚዎች የዘር ሐረግ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሁለተኛ የደመቀ መሾም ስሜትን በማይነካ የቃላት አጠቃቀም ለየዋሃን አማሮች ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ የፈጠጠውን ኢትዮጵያዊ እውነት ለሚረዳ ሰው ‹አማራ ተሾመልኝ!› በሚል የሚያስፈነጥዝ አይደለም፡፡ ራሱን ከጥቃት የማያድን አማራ፣ የራሱ ናቸው የተባሉ ወገኖችን ጥቃትና እንግልት ለማስቆም አንዳችም ተሰሚነት የሌለው በድንና ገልቱ ሰውዬ ተሾመልኝ ብዬ ጮቤ የምረግጥ ሞኝና ተላላ መስዬ ከታየኋቸው – አዝናለሁ – ሞኞቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ደመቀን መሣይ ከረፈፍ ሆዳሞች በሥርዓቱ ውስጥ ወይነው ገብተው ሀገሪቱን ምን ያህል እየጎዱ እንደሆነ ማስታወስም ተገቢ ነው፡፡ በጣም የምወደው ኦባንግ ሜቶ ቅድም ሲናገር እንደሰማሁት ሁልጊዜም እኔ ራሴ እንደምለው ወያኔ ማለት በዘርና በቋንቋ ተወስኖ ወይም ተቀንብቦ የተቀመጠ አለመሆኑንም መረዳት ይገባል፡፡ መነሻውና አስኳል አመራሩ ከትግራይ ይሁን እንጂ ለዚህ የወያኔ ሥርዓት ማበብና ማፍራት ዋና ተባባሪዎቹ ትግሬ ያልሆኑ የተጋቦት ወያኔዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ግን ግን “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ዞረ” እንዲሉ ሆኖብን አንዴ የፈረደበትን የትግራይ ሕዝብ ብዙዎቻችን እንወርድበታለን፡፡ በበኩሌ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ የእያንዳንዳችን ልብ ሳይሰበር ነገ ይቅርታ እንደምንባባልና አብሮነታችን ካለሣንካ እንደሚቀጥል በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ንዴትና ብስጭት የማይፈጥረው አእምሮኣዊ ምስል ባለመኖሩ ደመናው ሲጠራና እውነት ስታሸንፍ አሁን ችግር የሚመስሉን ብዙ ነገሮች ከላያችን ላይ ተገፍፈው ይጠፋሉ፤ ያለ ነገር ነው – በዚህን መሰሉ ጊዜ የሚያጋጥም ብዙ ነገር አለ፡፡ መምሰልና መሆን ስለሚለያዩ የደፈረሰው ሲጠራና የሰላም አየር በሀገራችን ሰማይ ሲያረብብ የግጭትና የሁከት እርኩሳን መናፍስት ተጠራርገው ይወገዳሉና ስለነገው ከመጠን በላይ አንጨነቅ፡፡ የወቅት ንፋስ የሚፈጥራቸው ብዙ አላፊ ክስተቶች አሉ – በኛ ብቻ ሳይሆን በየሀገሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳትና ለዚያ በርትቶ መታገል እንደሚገባ ተረድተን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ተባብረን ይህን የለያየንን ቆሻሻ ሥርዓት ለማስወገድ አብረን መታል ብቻ ነው የሚያዋታን፡፡ አለጥርጥር ሥርዓቱ ይወድቃል – ችግሩ በጣም ብዙ ምናልባትም ከእስካሁኑ የከፋ ቨስጠሊታ የታሪክ ጠባሳ ሳይተው የሚወድቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም ምክክር፣ ትብብርና ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ምን ጊዜም ከእውነት መንገድ ለማትወጣው ነገር በመለያየት አዲስ ግን በወያኔያዊ ትልምና ዐቅድ የተለወሰና በፀረ-ኢትዮጵያነት የተመረዘ ታሪክ ለማስመዝገብ የምንቻኮል ሰዎች ካለን ቆም ብለን እንድናስብ በእገረ መንገድ ጠቆም ባደርግ ደስ ይለኛል – ከወያኔ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ የሕዝቡ ችግረና ፍላጎት ይግባን፡፡ ‹ሕዝቡ ምን ይላል? ምንስ ይፈልጋል ?› ብለን እንራመድ እንጂ በየግል ፍላጎታችን የተጓዝን ተሳስተን አናሳስት፤ ታሪክም ይቅር አይለንም፡፡ መደማመጥ ለመልካም የጋራ ስኬት ጠቃሚ መሆኑን እየዘነጋን ለየህልማችን እውን መሆን በተናጠል ስንሮጥ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ፡፡

ማንዴላ እጅ ሆነዋል፡፡ ምናልባትም ይህች ጽሑፍ በአንዱ ድረ ገፅ ከመለጠፏ በፊት አንዳች ነገር ሊከሰት ይችላል፤ ወይም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ዜና ዕረፍታቸውን እንሰማ ይሆናል – ለነገሩ ‹እግረ ቀጭን እያለ እግረ ወፍራም ይሞታል› እንዲሉ ከማንዴላ በፊት ለምሳሌ እኔ ራሴ ልቀድም እችላለሁ፡፡ የወደፊቱን ያለማወቃችን ምሥጢር ነው ሕይወትን ትርጉም ያላት እንድትሆን ያደረጋት፡፡ ተስፋ ባትኖር ሁሉም በቁም እንደሞተ ያህል ነው – ጧት ከቤቱ በሰላም የወጣ ሰው ማታ ሬሣው ወደቤቱ ሊመለስ እንደሚችል ቢያውቅ ማንም የመኖር ጉጉት አያድርበትም – የእግዜሩም እንበለው የተፈጥሮ ጥበብ መገለጫም ይሄው ነው – ስለወደፊቱ አለማወቅ፡፡ በዚህም አለ በዚያ በማንዴላ ሁኔታ ዓለም በጭንቀት ላይ የምትገኝ ትመስላለች፡፡ ጭንቀቷ ግን ለማንዴላ ለራሱ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምሥጢሩ ወዲህ ነው፡፡(በነገራችን ላይ ‹ድኅረ ገፅ› የምንል ሰዎች ‹ድረ ገፅ› ማለትን ብንለምድ ደስ ይለኛል፡፡ ‹ድኅረ› ማለት ‹በኋላ›(post) ማለት እንደሆነና ‹ድረ› የሚለው ቃል ግን ‹ድር› ከሚለው የአማርኛ ቃል ተወስዶና ከ‹ገፅ› ጋር ተጋምዶ ‹website› የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እንዲተካ መደረጉን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ዕውቀት አይናቅምና በተለይ ድረ-ገፆች እባካችሁን ይቺን ነጥብ አትናቋት፡፡ መናደድ ሲያምረኝ ከምናደድባቸው ነገሮች አንደኛዋ ይህች ነች፡፡ )

የዓለም ሕዝብ አንድ አባሉ ከ94 ዓመታት በላይ በመሬት ላይ እየኖረ እንዲሰቃይ የሚፈልግ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰዎች እስከዘላለሙ እንዲኖሩ የሚፈለግበት ምኞት – ከልብ ስለመሆኑ ማወቅ ቢያስቸግርም – በብዛት የሚታየው በኛይቷ ሀገር በኢትዮጵያ ነው፡፡ የመቶ ሃያ ዓመት ሽማግሌ ሲሞት ፊት የሚነጨው በሌላ ሀገር አይደለም – በኢትዮጵያ ነው – ሊያውም ይበልጡን በአማራው አካባቢ፡፡ ባህላችን ከኛ ወቅታዊ ግንዛቤ በልጦ የሚገኝበትን ሁኔታዎች አንዳንዴ እንታዘባለን፤ ከአንዳንዴም በላይ እንዲያውም፡፡ ለዚህም ነው በዛሬዋ ውሎየ እንኳ ሁለት ተቃራኒ ጸሎቶችን የታዘብኩት – አንድ ከኢትዮጵያውያን፣ አንድ ከደቡብ አፍሪካውያን፡፡ መቼም እኛ ከነሱ በልጠን እግዜሩ ለማንዴላ የማቱሳላን ዕድሜ እንዲሰጥልን ልንጸልይ እንደማንችል ቢያንስ ኅሊናችን ያውቃል – እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፡፡ ይህ ምን ያሳያል? ፊት ለፊት የሚታየው ባህላችን ለሰው መጥፎ የማይመኝ መሆኑንና በብዙ ነገር ከሌሎች የምንለይ ሕዝብ መሆናችንን ነው ለዓለም እያስመሰከርን የምንገኘው – ምነው እውነተኛና በምንም ዓይነት ማዕበል የማይናወጥ አቋም ባደረገልን!

ማንዴላ እንዳይሞት የምንፈልግበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ዓለማችን በሰው እጦት ምች ስለተመታች ጥሩ ሰው ስናገኝ እንደብርቅ እናየዋለን፤ ሞት እንዳይነጥቀንም እንሳሳለታለን፤ እስከወዲያውም አብሮን እንዲኖር እንመኛለን – ትውልድ ቢያልፍም ከቀጣዩ ትውልድ ጋር፡፡ ብዙ ደጋግ ሰዎች ቢኖሩን ኖሮ የዓለም ሕዝቦች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት ያለቪዛና የትራንስፖርት ወጪ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ፕሪቶሪያ ሆስፒታል ዙሪያ ባልከተመ ነበር፡፡ ጥሩ ሰው ብርቅ በሆነበት ዘመን መፈጠር እንዴት መታደል ነው! መለስም እንዲያ የተንጫጫንለት እኮ የርሱን አእምሮ ይዞ የሚወለድ – እንደአዜብ አነጋገር በዓለም የአንጎል ገበያ ተመራጭ ጭንቅላት ይዞ በሺዎች ዓመታት አንዴ የሚወለድ ዐዋቂና ታዋቂ በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ለመለስ የነጨሁት ፊት እስካሁን አላገገመም፤ የምለብሰውም ማቅ ከላየ ላይ አልወረደም፡፡ እርግጥ ነው – ይበልጡን ለክፋት ቢጠቀምበትም መለስን በዕውቀቱ መቀጣጠብ አይቻልም፤ ሰይጣን ለዘዴው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባል መለስም የነበረው ሁለገብ ዕውቀትና ብልጣብልጥ ተፈጥሮ ከብዙዎች መሪዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የኔነህ ሳይለኝ ቢሞትም የኔነው ማለት ወጪ የለውምና ሳልወድ በግዴ የኔነው ብዬ ብቀበለው ከሚኮሰኩሰው ኢትዮጵያዊነቱ አንጻር ብቻም ሳይሆን ከአጠቃላይ ስብዕናው የሚፈልቁ ብዙ የሚደነቁ ሰብኣዊ ተሰጥዖዎች እንደነበሩት አልክድም – አጭበርባሪው፣ አስመሳዩና መልቲው መለስ ዜናዊ፡፡ ግን ተሰጥዖዎቹን ለተንኮልና እንደሥራየ ቤት ነገርን በመጠምዘዝ ሕይወቱን ጨርሶ ዕውቀቱን ሳይጠቀምበት ሞተና ዐርፎ ዐሣረፈን፡፡ በሚስቱ ሲንገበገብ የነበረ አንድ ፈላስፋ መቃብሯ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሯል አሉ፡- My wife lies here; let her rest in peace, so do I.

አትታዘቡኝ፡፡ በበኩሌ ማንዴላ እንዲያርፍ እጸልያለሁ – በሰላም ማረፍ ለኔ አይገባኝም – ሰው እየሞተ ምን ሰላም አለና፤ ማንዴላ በ‹ሰላም› እንዲያርፍም በ‹ሰላም› እንዲድንም ከጸሎት ጀምሮ ሁሉም ነገር ቢደረግም እስከዚች ሰዓት ድረስ አልዳነም ወይም አላረፈም፤ የዚህን ደብዳቤ የመጀመሪያ ረቂቅ ስጽፍ – አሁን ሰዓቱ ከሌሊቱ ስምንት ገደማ መሆኑን ልብ ይሏል – የማንዴላ የጤና ሁኔታ እንደሰሞኑ ሁሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ፤ ከአሳሳቢነቱም የተነሣ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ሊያደርጉት የነበረውን የሀገር ውጪ ጉዞ እስከመሠረዝ ደርሰዋል፡፡ ዕንቁ ልጃችን – ብርቅዬ የአፍሪካ ብቻ ሣይሆን የዓለማችን ልጅ ማዲባ ሲያርፍ ደግሞ ነፍሱ በማኅተመ ጋንዲና በእማሆይ ተሬዛ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ እንድትቀመጥ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆን ዘንድ የሁላችንንም ጸሎት እኔም በበኩሌ እጸልያለሁ፡፡ ይቅርታችሁን – ቀደም ብዬ ማዲባን በአንቱታ የጠራሁት ብዙ ሰው ያለው እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ከሰው ለመመሳሰል ነው፤ ስጨርስ በአንተ የጠራሁት የሕዝብ ሰው አንቱ እንደማይባል ስለምረዳ የአንጀቴን ነው – የሕዝብ ሰው ማለት ደግሞ የሚፈቀርና የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አብንና ወልድን ማን አንቱ ይላል? ቅድስት ማርያምንስ? ኧረ መለስ ዜናዊንስ ማን በአንቱታ ጠርቶት ያውቃል? የሕዝብ ሰው ማለት እንዲህ ነው – ቺንዋ አቼቤ A man of the people የሚል ርዕስ ለአንድኛው መጽሐፉ የሰጠው እኮ ለነማንዴላ ዓይነቱ መላ ሕይወታቸውን ለራሳቸው ጥቅም መስዋዕት ላደረጉ ሣይሆን ለነመለስ ዜናዊ ዓይነቱ ለቤት ቀጋዎች ለውጭ አልጋዎች ነው፡፡ ዓለም ግን ምን ዓይነት የዕንቆቅልሽ ምድር ናት ጎበዝ?!

ውድ ማንዴላ ሆይ! ሁልጊዜ ከኅሊናችን አትጠፋም – በአካል ብትለየን በመንፈስ ምንጊዜም አብረኸን አለህ – ከአሁኑም ከወደፊቱም ትውልዶች ጋር፤ ፈጣሪ አንተን እንደወሰደ በምትክህ ለዓለም ሰላም የሚተጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን አሳቢ ዜጎችን እንዲልክልን ስትሄድ አሳስብልን፡፡ አፈሩን ገለባ ያድርግልህ፡፡ የሁለት ወር ሀገርህን ኢትዮጵያንም በፈጣሪ ፊት አስባት፡፡ ስቃይና ጣር ሳይበዛብህ በቶሎ ሂድልን፡፡ በዚህች አንተን ሳይቀር ለ27 ዓመታት በእሥር ባንላታች የእርጉማን ምድር ከአሁን በኋላ ለሴከንድም መቆየቱ መከራና ስቃይ መጨመር እንጂ ጤናውም ጤና አይሆንህም፡፡ ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፤ ‹ቆይልን› የምንልህ በአንተ ስቃይ የኛን ‹ኢጎ› ለማስደሰት እንጂ አንተ አልጋ ላይ ውለህ የመከራ ቀናትንና ሌሊቶችን በእዬዬ ማሳለፍህ፣ በድጋፍ ሰጪ የሕክምና ቴክኖሎጂ እየታገዝክ ካለ እንቅልፍ መቆየትህ አንዳችም ነገር አይፈይድልንም – ለአንተም ለእኛም፡፡ በሀገሬ ሰው ይሙት ተብሎ እንደማይጸለይ አውቃለሁ ማዲባየ – ግን ‹ይህን አለ› ተብዬ ኩነኔ መግባቱን እመርጣለሁ እንጂ ስትሰቃይ ለማየት ከእንግዲህ ቆይልን አልልህም፡፡ በቃ፡፡ በሰላም ሂድልን፡፡ ስትመጣ እንደምትሄድ ይታወቅ ነበር፡፡ እኛም በሕይወት አለን የምንል ወገኖችህም ወረፋችንን ጠብቀን እንከተልሃለን፡፡ ዱሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ይብላኝ ለኛ ግና፡፡ በጅቦችና በእሪያዎች መካከል እንደተጣልን ተለይተኸን ለምትሄደው ለኛ ይብላኝ እንጂ አንተማ ከፋም ለማም 95 የሚጠጉ ክረምቶችን ለሕዝብህ ስትል ከአፓርታይድና ከመጥፎ ግላዊ ገጠመኞችህ ጋር ስትፋለም ኖረህ አሁን በመጨረሻው ሥጋዊ ሽንፈትህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል፡፡ በዚያች በደቡብ አፍሪካዊቷ አዜብ እንኳን ያየኸውን አበሳ ማን ይረሳዋል? ብቻ ሆድ ይፍጀው ማዲባየ፡፡ እዚያው እስክንገናኝ ደህና ሰንብትልኝ፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ፤ በዚህ ዓለም አቀፍ ሀዘን መጽናናት ለሚያስፈልገው ሁሉ ፈጣሪ እንዲያጽናናው እመኝለታለሁ፡፡

posted by Daniel tesfaye

Post Navigation