FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

Archive for the month “September, 2013”

ግንቦት7 በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መስመሩን እየዘረጋ መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ

379902_189182111178517_478402269_n
መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው።

የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል።

በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት ሰዎች በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ አንዳርጋቸው ፣ በመከላከያ ሰራዊት በእግረና፣ በአየር ሃይልና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሊደርሱበት በማይችሉበት መንገድ መስመር እየዘረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

በውጭ አገራት ተመሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለማድረግ እቅድ አላችሁ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ ህዝባዊ ሀይሉ ከተግባር ጋር በተዛመደ መልኩ የገቢ መሰባሰብ ዝግጅት መርሀ ግብሩን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በህዝባዊ ሀይሉ ወይም በግለሰቦች ስም ምንም አይነት የገቢ መሰባሰቢያ ዝግጅት መደረግ እንደሌለበት ገልጸዋል

በሌላ ዜና ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው በስቶክሆልም እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ውይይት አድርገዋል። አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን ዓላማዎች፡ተልዕኮዎች እና ራዕይ በማስተዋወቅ ህዝባዊ ሃይሉ ከምስረታ ጀምሮ አሁን ያለበትን ደረጃ በምስልና በጽሁፍ የተደገፈ ገለጻ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።

እሳቸው እና ሌሎች የአመራር አካላት እንዲሁም አባላት የተገኙበት የውትድርና ስልጠና አንዱ የበታች አንዱ የበላይ እንዳልሆነ በማስገንዘብ ይህ ህዝባዊ ሃይል ቤተሰባቸውን፡ስራቸውን፡ ገንዘባቸውን፡ እና የተደላደለ ኑሯቸውን በመተው ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን የተዋቀረ እንደሆነ ገልጸዋል።

የግንቦት ሰባት ዓላማ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ብቻ ሳይሆን ባለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያውያን የተገፈፉትን ክብራቸውን ማስመለስ ጭምር መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው አስምረውበታል ሲል ቴዎድሮስ አረጋ ከስዊድን ዘግቧል።

posted by Daniel tesfaye

Advertisements

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ተመስገን ደሳለኝ)

September 29th, 2013107521ee73facb2e1377756991
ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

እንደ መግቢያ

ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በምርጫ 2002ቱ ማግስትም ድርጅቱ አቦይን ‹‹በክብር›› እንዲሸኝ ሲደረግ፣ ፀጋዬ በርሄን ደግሞ ‹‹አማካሪ›› በሚል ሽፋን ከመቀሌ ወደ ቤተ-መንግስት (ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ) አዛውሮ በቅርብ እይታ ስር በማዋሉ ሁለቱንም ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል፡፡ በግልባጩ አዜብ መስፍንና ‹የመለስ ታማኞች› የሚባሉት እነአባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስ የፖሊት ቢሮውን ተቀላቅለዋል፡፡ ሁነቱም ከእነአቦይ ጋር በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩ ባለስልጣናትን በማስከፋቱ በድርጅቱ ውስጥ ብቻ የሚታወቅ (አደባባይ ያልወጣ) ልዩነት ፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል (በነገራችን ላይ ኦህዴድ የማዳከሙ ሴራ ሰለባ ነው፡፡ ይህ ሁናቴ ከመለስ ህልፈትም በኋላ ቀጥሏል፤ ለምሳሌ ባለፈው ዓመት የግንባሩ አባል ድርጅቶች፣ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ብአዴን በ‹ክብር› ካሰናበተው ሁለት ዓመት ያለፈውን መሪውን አዲሱ ለገሰን ወደ ቦታው መልሶ ራሱን ሲያጠናክር፣ በተቃራኒው ኦህዴድ አንጋፋ አመራሮቹን፡- አባዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳና ግርማ ብሩን ከስራ አስፈፃሚነታቸው እንዲያነሳ ተገድዷል፡፡ ይህንን ነው መተካካት የሚሉትም፡፡

ህወሓት

የመለስን ህልፈት ተከትሎ በውስጡ ያደፈጠው ቅራኔ ፈንቅሎ በመውጣቱ ህወሓትን የ‹መቀሌው› እና የ‹አዲስ አበባው› በሚል ለሁለት ከፍሎት ነበር፤ ይህ ግን የመቀሌው-በአዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባው-በመቀሌ ደጋፊ አልነበረውም እንደማለት አይደለም (የመቀሌውን አዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሀጎስ… መርተውታል፤ የአዲስ አበባውን ደግሞ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃዬ፣ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ ታጋዮች ዘውረውታል)፡፡ ይህ አጋጣሚም ከእነ አዜብ ቡድን ጋር ትብብር የፈጠረውን ብአዴንን ለጊዜያዊ ድል አብቅቶት ነበር (በ93ቱ ክፍፍልም የብአዴን ድጋፍ መለስ በአሸናፊነት እንዲወጣ ጉልህ ድርሻ ማበርከቱ ይታወሳል)፡፡ አቦይ ስብሃት ነጋ በትግርኛ ቋንቋ በሚታተመው ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ ‹‹ህዝቢ ትግራይ ዘቃልሶ ኣቃሊሱ ዝጠቕሞ ወያናይ ውድብ ይግብኦ›› (የትግራይ ህዝብ የሚያታግለው፣ ታግሎም የሚጠቅመው ወያኔያዊ ድርጅት ይገባዋል) በሚል ርዕስ በፃፉት ፅሁፍ ችግሩን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡-

‹‹አባይ ወልዱም ባለፈው የህወሓት ጉባኤ ላይ በተደጋጋሚ ‹ህወሓት ውስጥ ማጠለሻሸትና (የሥልጣን) ሽኩቻ በስፋት እየተስተዋለ ነው› በማለት ሁኔታውን ገልፆታል፡፡ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ ደግሞ የለም፡፡ እንዲህ ያለ በኃይል አሰላለፍ ደረጃ ሊታይ የሚችል የአንድን የፖለቲካ ድርጅት አቅም ከማዳከምና መርሀ-ግብሩን ከማሰናከል አልፎ ተርፎም ድርጅቱን ለአስከፊ ውድቀት ሊጥል ከሚችል አደገኛ ሁኔታ የበለጠ አደጋ ያለ አይመስለኝም፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሐሴ 2005 ዓ.ም)

ከኃይለማርያም ጀርባ

ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንባሩ ሊቀ-መንበር በመሆኑ ጉዳይ ላይ ብአዴንም ሆነ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ቅሬታ አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እርሱም ሆነ ‹ደቡብን እወክላለሁ› የሚለው ድርጅቱ ለአሸናፊ ኃይል ከማገልገል አልፈው የፖለቲካ አመፅ ሊያስነሱ እንደማይችሉ ይታወቃልና፡፡ ይሁንና በወቅቱ ኃይለማርያም ሰልፉን በ‹መለስ ባርኔጣ› ከሚንቀሳቀሰው ከመቀሌው ህወሓትና ብአዴን ጋር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝበማስተካከሉ የኃይል ሚዛኑ በአንፃራዊነት ወደእነርሱ እንዲያጋድል አድርጓል፡፡ በግልባጩ ለእነ አቦይ እና ደጋፊዎቻቸው የመሸነፍ መገለጫ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ እንግዲህ እስከ ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ድረስ ‹መልከ-ኢህአዴግ› በዚህ መልኩ ነበር የቀጠለው፡፡

‹መፈንቅለ-ህወሓት›

ብአዴኖች፣ ከመቀሌው ህወሓት ጋር የፈጠሩትን ግንባር፣ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ካገኙት ድጋፍ ጋር በማዋሀድ፡- የአዲስ አበባውን ህወሓት የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ፣ የደህንነት ሀላፊው ጌታቸው አሰፋን እና አንጋፋ የህወሓት ታማኝ ጄነራሎችን ከመንግስታዊውም ሆነ ከፓርቲው ኃላፊነታቸው በማንሳት በአሸናፊነት ለመወጣት ስልታዊ እንቅስቃሴ አድርገው እንደነበር ለድርጅቱ ቅርብ ከሆነ ሰው አረጋግጫለሁ፡፡ በባህርዳሩ ጉባኤ ላይም መላኩ ፈንቴ ‹አላሰራ አሉኝ› ብሎ በአደባባይ እንዲያጋልጣቸው ከተደረጉት የንግድ ደርጅቶችና ሀብታም ነጋዴዎች አብዛኞቹ ከአዲስ አበባው ህወሓት ጋር የተሳሰሩ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ኩነቶችም ነው ‹መፈንቅለ-ህወሓት› ለማለት የተገደድኩት፡፡ ሴራው የከሸፈው በሁለት ምክንያቶች ይመስለኛል፤ የመጀመሪያው በሰውየው ህልፈት ማግስት (ተተኪው ጠቅላይ ሚንስትር ገና ባልተመረጠበት) እነአባይ ፀሀዬ ሶስት ሜጀር ጄነራል እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎች (አብዛኞቹ የህወሓት ሰዎች ናቸው) መሾማቸው ኃይላቸውን ሲያጠናክርላቸው፣ በአንፃሩ የመቀሌውን ህወሓትና ብአዴንን በሠራዊቱ ውስጥ የነበራቸውን ተፅእኖ ከማዳከሙም በላይ ኃይል የማሰባሰብ ሩጫቸውንም ገትቶታል፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በደህንነት
መስሪያ ቤቱ አቀናባሪነት በ‹ፀረ ሙስና› ሽፋን የተከፈተው ዘመቻ ነው፤ እነበረከትንም ስልታቸውን መልሰው እንዲያጤኑ ያስገደዳቸው ይህ አይነቱ አስደንጋጭ እርምጃ ይመስለኛል፡፡

የህወሓት ‹ቆሌ›

የኢትዮጵያን ልማዳዊ ፖለቲካ ከነሴራው ጠንቅቀው ከተረዱት ጥቂት ሰዎች መሀል አቦይ ስብሃት ነጋ አንዱ መሆናቸው ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ አቦይ ህወሓትን ጠፍጥፎ በመስራቱም ሆነ በስልጣን ለማቆየት የመለስን ያህል (ሊበልጥም ይችላል) ለፍተዋል፡፡ ዛሬም ተፈጥሮ ላመጣባቸው እርጅና እጅ ሳይሰጡ በህወሓት ላይ የሚሴረውን-ለመበጣጠስና ለተቀናቃኞቻቸው-ጉድጓድ ለመቆፈር እንደማይሳናቸው አሳይተዋል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው ‹የህወሓት ቆሌ› የሚል ቅጥያ ያሰጣቸው፡፡

ከመለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው ጥብቅ የመተባበር መንፈስም ከጓዳዊነትም በላይ እንደነበር የቅርብ ሰዎቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ ግና ይህ የጦፈ ፍቅራቸው ከ2000 ዓ.ም ወዲህ መደብዘዝ ጀምሮ ነበር፤ ልዩነታቸውም ቅስ በቀስ እየሰፋ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ አንዱ መለስ፣ ለአዜብ መስፍን እየሰጠ የነበረውን የፖለቲካ ጉልበት፣ አቦይ ‹ህወሓትን በሴት ቀሚስ እንደማሳደር› አድርገው መውሰዳቸው ነበር፡፡ ሌላው የሴቲቱ ኃይለኝነት የአቦይን የተሰሚነት ክልል ከመፈታተን አልፎ በአደባባይ ክብራቸውን እስከ መዳፈር መድረሱ ይመስለኛል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም ከመለስ ጋር ተገናኝተው መነጋገር አልቻሉም፤ ለህወሓት ቅርብ የሆኑ ወዳጄ እንደነገሩኝ መለስ ህይወቱ ሲያልፍ አቦይን ካገኛቸው ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፤ ምክንያቱ ደግሞ እርሱ ማግኘት ባለመፈለጉ ነበር፤ ይህም ሆኖ አቦይ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም በልዩ ረዳቱ አማካኝነት ‹አስቸኳይ ጉዳይ ላይ ነው› እያስባለ መልሷቸዋል፤ በስራ አጋጣሚ ከቢሮ ውጪ ሲገናኙም ‹አጣዳፊ ስራ ስለተደራረበብኝ ነው፤ እኔ ራሴ አስጠራሀለሁ› እያለ ለሁለት ዓመት ያህል ሲርቃቸው ከቆየ በኋላ ነበር ድንገት ህይወቱ ያለፈው፡፡

አቦይ ወደ ህወሓት ተመልሰው በንቃት መሳተፍ የጀመሩት የመለስን ጤንነት ሲከታተሉ የነበሩ ሐኪሞች ‹ተስፋ የለውም› ባሉበት ማግስት ነበር፤ እንደምክንያት ያስቀመጡት ህወሓት ከድህረ-መለስ በኋላ፣ የብአዴንን የትከሻ ግፊያ መቋቋም አይችልም የሚል ስጋትን ነው፡፡ የሰውየው መጨረሻ ከታወቀ በኋላም የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ የታየው የኃይል ሚዛን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ በወቅቱም አቦይ ‹መፍትሄ› ብለው ያቀረቡት ‹ብአዴንና ከጎኑ የተሰለፉትን የህወሓት የአመራር አባላትን ማሸነፍ ስለማንችል፣ አንጃው (የእነ ስዬ ተወልደ ቡድን) ተመልሶ ያጠናክረን› የሚል ነበር፤ በስማቸውም ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ በፃፉት (ርዕሱ ከላይ በተጠቀሰው) ፅሁፍ ጉዳዩን እንዲህ በማለት ገልፀውት ነበር፡-

‹‹…ሁላችንም ህወሓት ውስጥ እያለን እኮ አንጃው ድርጅቱን ተቆጣጥሮት በትረ-መንግስቱንም ሊጨብጥ ተቃርቦ ነበር፡፡ በአንጃው የመዋጥ አደጋ ጊዜ ሁላችንም ተኝተን ነበር፡፡ እነዚያ የተሰናበቱት ሰዎች በማዕከላዊ ኮሚቴው ውስጥ ቢቆዩ ኖሮ ይተኙ ነበር ማለት ግን አይደለም፡፡ አሁን ላለው አመራር ይደግፉት ነበር ይሆን ማለቴ ነው እንጂ፡፡ …ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የወጣ ሁሉ እንደአዲስ ተደራጅቶ አሁን ላለው ማ/ኮሚቴ እገዛ የሚያደርግበትን መንገድ ማፈላለግ አለበት፡፡…›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሀሴ 2005 ዓ.ም)

ሆኖም አባይ ፀሀዬ፣ አርከበ እቁባይ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋን የመሳሰሉት ‹በጭራሽ አይሆንም! የእነርሱ መመለስ ያውከናል› የሚል አቋም በመያዛቸው ሃሳቡ ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

ከዚህ በኋላ የእነ አቦይና አባይ ቡድን ‹ህወሓትን ማዳኛ› ያለውን ሁለት ወሳኝ እርምጃ ወስዷል፤ ከህግ ውጪ ሶስት ሜጀር እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎችን ሲሾም፣ በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበረውን ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከየትኛውም አይነት ‹ኦፕሬሽን› እንዲገለል አደረገው፤ ቀጥሎ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከሀላፊነቱ አነስቶታል፡፡ በዚህ በኩል ያገኙትን የፖለቲካ ጉልበት በመመንዘር ከህገ-መንግስቱም ሆነ ከተለምዶአዊው አሰራር በማፈንገጥ ተጨማሪ ሁለት ም/ጠቅላይ ሚንስትሮች እንዲሾሙ ጫና ፈጥረው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ኃ/ማርያም ደሳለኝን በቅርብ ርቀት እንዲከተል አድርገዋል (በነገራችን ላይ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በመረጠበት ወቅት ወልደስላሴ ሲጠቆም፣ ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቦ እንዳይመርጡት ያነሳሳበት የደህንነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋ ሲሆን፣ በአንፃሩ ጌታቸው የተጠቆመ ጊዜ ወልደስላሴ እና ገብረሃዋድ ተቃውሞውን ቢያስተባብሩም ታናሽ ወንድሙ በላይ አሰፋን ጨምሮ ከመመረጥ ማደናቀፍ አልቻሉም፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወልደስለሴና ገብረሃውድ በሙስና ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ)፡፡

ሌላኛው የህወሓት ‹ጠባቂ መልአክ› አባይ ፀሀዬ ነው (በ2005 ዓ.ም ወርሃ ጥቅምት በታተመችው ‹አዲስ ታይምስ› መፅሄት ላይ አባይ፣ መለስ ያደረገውን ማድረግ የሚችል /ከንግግር ችሎታ በቀር/ አደገኛ ሰው መሆኑን መግለፄ ይታወሳል) ዘግይቶም ቢሆን ቡድኑን የበላይ ባደረገው የ‹ፖለቲካ ጨዋታ› እርሱም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ታይቷል፡፡ ደብረፅዮንም ቢሆን ከህወሓት ጋር ባሳለፈው ዘመን ‹ትጉህ ደቀ-መዝሙር› ስለነበር ያካበተው ልምድ ህወሓትን በታደገው ንቅናቄ ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ እነ አባይ ከባህርዳሩ ጉባኤ በኋላ ነው ‹ከመከላከል ወደ ማጥቃት› ተሸጋግረው ብአዴንንና የመቀሌውን ህወሓት በ‹ሙስና› ስም ሰለባ ያደረጉት፡፡ ይህንን እውነታም የሚያጠናክርልን አቦይ ስብሃት ‹‹ውራይና›› መፅሄት ስለ ጉዳዩ ጠይቋቸው የሰጡት ምላሽ ነው፡-

‹‹አሁን በእስር የሚገኙት [እነመላኩ ፈንቴን ማለታቸው ነው] ሙሰኞች ብቻ አልነበሩም፡፡ የፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፍንም ሲለውጡ የነበሩ ናቸው፤ ያስፈራሩም ነበር፤ ‹የስልጣን ሹዋሚም ሻሪም እኛ ነን› አስከማለትም ደርሰው ነበር፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 2 ሠኔ 2005 ዓ.ም)

የብአዴን የአመራር አባል የሆነ አንድ ሚንስትር ለእስር ሲዳረግ፣ ሌላ ሚንስትር ደግሞ ከኃላፊነቱ መነሳቱ ይታወቃል፡፡

አዲሱ ግንባር

ብአዴን የአዲስ አበባው ህወሓት ክንደ-ብርቱ እየሆነ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብን ቡድን አውላላ ሜዳ ላይ ትቶ አብሮ ለመስራት ተደራድሯል፡፡ እነ አባይም ‹ከብአዴን ተሻርኮ ሊያስበላን ነበር› ያሉትን የመቀሌውን የህወሓት ኃይል ከሞላ ጎደል ሲያስገብሩት፣ የቡድኑ መሪን አዜብ መስፍንን ደግሞ ከኤፈርት ከማሰናበታቸውም በላይ የፓርላማ ወንበሯን የሰዋችለትን የአዲስ አበባ የከንቲባነት ምኞቷን አጨልመው፣ በመለስ ፋውንዴሽን ገድበዋታል (የመለስ ሙት ዓመት በተከበረበት ወቅት የትግሉን ዘመንና የመለስን ገድል በኢቲቪ ሲተርኩልን የነበሩት የታሪኩ ዋና ተዋንያን አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ሳሞራ የኑስ…ሲሆኑ፣ በህልፈቱ ሰሞን ግን መድረኩን ተቆጣጥረውት የነበሩት ብአዴኖች፣ እነኩማ ደመቅሳ እና ትግሉን በመፅሀፍትና በቴሌቪዥን የሚያውቁት እነ ሬድዋን ሁሴን መሆናቸውን ስናስታውስ የእነ አባይ ፀሀዬ ህወሓት ምን ያህል ተገፍቶ እንደነበረ እንረዳለን፡፡)

በአናቱም ብአዴን የበላይነቱን በጨበጠበት ወቅት እንደ ስጋት ቆጥሮት ‹ሊፐውዘው› አስቦ የነበረውን መከላከያም፣ ከድርድሩ በኋላ በሁለቱ ኃይሎች ስምምነት ለአምስት ቀናት ኪራይ ሰብሳቢነትን እና ሙሰናን በተመለከተ ብቻ ተገማግሞ እንዲታለፍ ተደርጓል፡፡ ከኃላፊነታቸው ለማንሳት የታሰቡት ጄነራሎች ጉዳይም ‹ያልታሰበ አደጋ ሊያመጣ ይችላል› በሚል ለጊዜው ተዘሏል፡፡ ይሁንና ኤታማዦር ሹሙን ጄነራል ሳሞራ የኑስን በዚሁ ዓመት መጨረሻ በ‹ክብር› ሸኝቶ፣ ጄነራል አበባው ታደሰን የመተካት ዕቅድ መኖሩን ምንጮች ጠቁመዋል (ከዚህ በኋላ በጡረታ የሚሰናበቱ ጄነራሎች ‹መከላከያ ቴክኖሎጂ› /መቴክ/ በሚመራውና ወደፊት በሚያቋቁማቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በስራ-አስኪያጅነት ወይም በቦርድ አባልነት እንደሚመደቡ ቃል ተገብቶላቸዋል)

ከኃ/ማርያም ጀርባ ያደፈጠ-ስውር እጅ

በሁለቱም ቡድን ካሉ ምንጮቼ ‹‹ኃ/ማርያም ስራው ከብዶታል›› የሚል ቅሬታ እንደነበራቸው ሰምቻለሁ፤ ይሁንና መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደው በረከት ስምዖንን የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር› አማካሪ በሚል ሹመት በጽ/ቤቱ ማስቀመጥን ነው፤ እርሱሁሉንም ነገር ከጀርባ ሆኖ እንዲያከናውን ወስነዋል፡፡ በረከት የተመረጠው ‹ከመለስ ጋር በቅርብ ስርቷል፣ መለስ ያነበበውን አንባቧል፣ የመለስን የዕለት ተዕለት ሥራ በቅርብ ተከታትሏልና መንገድ ይመራል› በሚል እንደሆነ ምንጮቼ ነግረውኛል (በነገራችን ላይ መለስ ሞት ባይቀድመው ኖሮ የወደፊት ዕቅዱ ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ጀምሮት የነበረውን ግንባታ አጠናቅቆ፣ ከ2007ቱ ምርጫ በኋላ ስልጣኑን፣ ከአሻንጉሊቶቹ ለአንዱ አስረክቦ፣ መኖሪያውንም ወደ አዲሱ ህንፃ አዛውሮ፣ በለቀቀው ቤት ውስጥ የሚያስገባውን ጠቅላይ ሚንስትር ከጀርባ ሆኖ መዘወር ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ህልፈቱን ተከትሎ ግንባታውም የተቋረጠው፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ግንባታው ሊቀጥል እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ በረከት ስምዖን እንዲገባበት ታስቦ ይሆን? …አባይ ፀሀዬም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹አማክሪ› ሆኖ እንደሚሾም ‹ፎርቹን› ጋዜጣ በ‹ጎሲፕ› አምዱ አትቷል፡፡ መቼም ኃ/ማርያም ‹‹ሰርክ ‹እኔም አንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልለት› እያልኩ እዘምርለታለሁ›› ያለን አምላኩ ካልታደገው በቀር፣ ከእነዚህ ጉልበታም ሰዎች በጤና መውጣቱን እንጃ!)

ህወሓትና ብአዴን ልዩነታቸው መፈታቱን ለማሳየት፣ በረከት ስምዖን ከአዲሱ ሹመት በኋላ በሃያ ሁለት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ አድርጎት የማያውቀውን መንግስትን ወክሎ (በግሉ ሄዶ ሊሆን ይችላል) በትግራይ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የስራ ጉብኝት አካሄዷል፡፡ ‹ድምፀ ወያኔ› የተባለው የክልሉ ሬዲዮ ጣቢያም ጉብኝቱን ሳምንት ሙሉ ሳይታክት ደጋግሞ አስተላልፎታል፡፡

ሽራፊ-መረጃ

የአቦይ ስብሃት ነጋ ቡድን በኢህአዴግ ውስጥ ተከስቶ ከነበረው ክፍፍል በአሸናፊነት መውጣቱ ከተረጋገጠ በኋላ አዲስ ወሬ እየተሰማ ነው፡፡ ይኸውም ‹ህወሓት የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን በመልቀቁ፣ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚያስረክቡትን ወንበር አቦይ ስብሃት መያዝ አለባቸው› የሚል ነው፤ ምንም እንኳ ሃሳቡ ተፈፃሚነት ባይኖረውም፣ ምንጮቼ አቦይ ራሳቸው በዘወርዋራ መንገድ ያሰራጩት ወሬ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ አዜብ መስፍንም ቦታውን የመያዝ ፍላጎት ያላት ይመስለኛል፡፡

ብዙ ሲባልለት የቆየው የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ከላይ ለማቅረብ በሞከርኩት መንገድ ግራና ቀኝ ሲዋልል፣ የመከፋፈል ተግዳሮትን ሲሻገርና እንደገና እየተመለሰ ሲሰባሰብ እዚህ ደርሷል፡፡ በዚህ ኮሮንኮቻማ ሂደት ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትሩ ሚና ‹እዚህ ግባ› የምንለው እንዳይመስለን ሆኗል፡፡ ኃይለማርያም መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን የፓርቲው ሊቀ-መንበርነትን የመሰለ ጠንካራ ፖለቲካዊ ስልጣን መያዙ ይህ ሰው የሚባለውን ያህል የዳር ተመልካች ሆኖስ ይቆያልን? ለሚለው ጥያቄ ቀጣይ ጊዜያቶች ብቻ መልስ ይኖራቸዋል፡፡ የጠቀስኳቸው የስርዓቱ ጉምቱ ሰዎች በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሱም ቢሆን፣ ይህን የኃይል መገዳደር እያደረጉ ያሉት በስልጣን ሞኖፖሊ ላይ ተቀምጠው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እናም ባቀረብኳቸው ሂደቶች እያለፉም ይሁን አይሁን ለስልጣናቸው የሚያሰጋ ጠንካራ የታቃውሞ ስብስብ አለመኖሩን ማመናቸው ይመስለኛል፣ የኃይል ትንቅንቁን ‹ግዜው አይደለም› ብለው ለማራዘም ሳይጠነቀቁ በግላጭ እርስ በእርስ የተፋለሙት፡፡

የሆነው ሆኖ የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈለግም፡፡

posted by Daniel tesfaye

Grand Andinet Rally Ends with Calls for Release of Political Prisoners {video}

UDJ
ADDIS ABABA – Tens of thousands of city residents marched through the streets of the Ethiopian capital on Sunday in an Andinet-organized rally for democracy and justice. Police were trying to block many people from joining the rally. Andinet rally organizers were taking cautious measures as undercover agents of the regime tried to pit police against demonstrators so that the rally would be disrupted. Activists chanted, among calls for the release of political prisoners, that the “police belong to the people,” in a clear message that the pro-democracy camp abhors violence as opposed to the regime, which has been in power since 1991 against the will of the Ethiopian people.

posted by Daniel tesfaye

Ethiopia opposition stage anti-government demo

 September 29, 2013

ADDIS ABABA (AFP) –  A leading Ethiopian opposition group gathered Sunday to protest against the country’s anti-terrorism legislation, the head of the group said.

“We want the government to abrogate the law and to release all political and prisoners of conscience immediately,” Negasso Gidada, the leader of the opposition Unity for Democratic Justice (UDJ), told AFP.

Several opposition members and journalists, including dissident blogger Eskinder Nega, have been jailed under the 2009 legislation.

The government accused the group of  ”glorifying” convicted criminals and said the threat of terrorism in Ethiopia needed to be taken seriously.

“These people are downplaying the danger that this country has been facing… its not a potential threat, it’s already there,” said government spokesman Redwan Hussein.

Negasso said he was briefly arrested ahead of the protests along with the single member of parliament from an opposition party, Girma Seifu, and 60 other people.

Redwan said he did “not know of anybody” who had been detained.

The demonstration is part of a three-month campaign launched by UDJ, which has held protests in several cities across the country.

Negasso estimated the crowd at 80,000 people, while Redwan said only a few hundred had gathered.

The group, led by five people dressed in prison uniforms, chanted slogans demanding freedom and the release of prisoners, including UDJ member Andualem Arage who is serving a life sentence after he was convicted under the law.

Rights groups have accused Ethiopia’s anti-terrorism legislation of being vague and used to stifle peaceful dissent.

Last year, two Swedish journalists jailed on terror-related offences were released after serving 13 months of their 11-year sentence.

posted by Daniel tesfaye

ሰበር ዜና፣ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

20130928_230706
20130928_175953
September 29, 2013
ዛሬ ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። ሙሉ ዘገባውን በቅርብ ይዘን እንቀርባለን ።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ከኖርዌይ
posted by Daniel tesfaye

No Human Rights = No Development

timthumb
September 26, 2013

Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network Submit Human Rights Report on Ethiopia to the United Nations

OAKLAND CA- In a report submitted to the UN Human Rights Council’s Universal Periodic Review (UPR) on September 15, 2013, the Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network outlined the human rights and international law violations perpetrated by the government of Ethiopia in the name of country’s development strategy.

Drawing clear links between recorded testimonies on the ground and breaches of specific international covenants and articles in Ethiopia’s constitution, the joint submission to the UN Human Rights Council also responds to Ethiopia’s draft National Human Rights Action Plan for 2013-2015. “Rather than working to build a development strategy grounded in human rights, the Ethiopian government is attempting to hoodwink its human rights record, leaving unmentioned its villagization program and the Anti-Terrorism Proclamation-both used by the government as significant justifications for forced resettlement, arbitrary detentions, and politically motivated arrests,” said Anuradha Mittal, Executive Director of the Oakland Institute.

As previous Oakland Institute reports have chronicled, the Ethiopian government’s efforts to clear land for large-scale foreign investment has entailed widespread violations of human, social, economic, and political rights. Violations of citizen’s rights to self-determination, housing, land for subsistence production, and free political association–enshrined in the Ethiopian constitution, the Rural Land Administration and Land Use Proclamation, and in United Nations international covenants–are carried out in the name of development.

The joint UPR submission suggests that the ruling party’s ability to implement country’s unpopular villagization program rests in its monopoly on force and dominance over the allocation of humanitarian assistance. “Authoritarian governance and the methods used in implementing development projects have combined to violate human rights to livelihood and culture for land-based peoples, especially in the peripheral regions,” said Joseph Schechla, Coordinator of the Housing and Land Rights Network. “Involuntary resettlement, a form of forced evictions, accompanies deprivation of the right to food, including the right to feed oneself, particularly for agropastoralists. On the other hand, the ability to control information and stifle dissent has enabled the ruling party to present a positive face to the international community, which has dubbed Ethiopia a nation in “renaissance”, he continued.

The joint submission presents undeniable evidence that should compel the international community to advocate for a human rights centered development strategy that would benefit all Ethiopians.

Download the joint Oakland Institute/HIC-HLRN submission

posted by Daniel tesfaye

የመንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ከወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች አመጽ ጀርባ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን አሉበት አለ

original_al_amoudi_wearing_eprdf_tshirt_may_2005
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፣ “ኢህአዴግን የፈተነ ወሳኝ ክስተት” በማለት የገለጸውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ አልሻባብ፣ አልቃይዳ ፣ ግንቦት ሰባት ፣ እና የኤርትራ መንግስት እንደሚደግፉት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሀን ቢገልጽም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ የደህንነት ሀይሎች ቱጃሩን ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንን ከእንቅስቃሴው ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቁም መረጃ ለመንግስት ባለስልጣናት ማቅረቡ ታውቋል።

በቅርቡ በወልድያ ከተማ የወልድያ ሙስሊም ተማሪዎች ባነሱት አመጽ መንገድ ዘግተው ወደ ላሊበላ ፤ ሰቆጣ ፣ ደሴ እና አዲስ አበባ የሚደረጉ የትራንስፖርት ጉዞዎች እንዲስተጓጎሉ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አመጹን አነሳስታችሁዋል የተባሉ 13 ታዳጊ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የደህነነት ሐይሎች አጣራነው ባሉት መረጃ አመጹን ሼክ አላሙዲን ከጀርባ ሆነው ደግፈውታል።

የኢህአዴግ አመራር እና የፌደራል ፖሊስ የጋራ የጸረ ሽብር ግብረ ሐይል በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ውይይት ካደረጉበት በኃላ ፣ በባለሀብቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ባይቻልም በወዳጆቻቸው በኩል ምክር አንዲሰጣቸው በአቶ በረከት ስምኦን የሚመራ አንድ ቡድን መዋቀሩን ለማወቅ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ሼክ አላሙዲን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከታክስ እና ከግንባታ ጋር በተያያዘ ከመንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። የደህንነት መስሪያ ቤት በባለሀብቱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መረጃ እንዳገኘ ቢገልጽም፣ መረጃውን እንዴት እንዳገኘው አልታወቀም። አንዳንድ ወገኖች ግን የሼክ አላሙዲን ከህግ በላይ መሆን ያሳሳበው መንግስት፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ባለሀብቱን ለመምታት የፈጠረው ዘዴ ሊሆን ይችላል ይላሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ ሼክ አላሙዲንን ወይም ወኪሎቻቸውን ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

ሼህ አሊ አላሙዲን ለኢህአዴግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይታወቃል።

posted by Daniel tesfaye

ዲያስፖራ ላሜ ቦራ (ወንድሙ መኰንን፣ ከታላቋ ብሪታኒያ)

76852408af0ad95f1379961584
September 26, 2013
ወንድሙ መኰንን፣ ከታላቋ ብሪታኒያ
ይኸ መጣጥፍ መጀመሪያ የተጻፈውና በኢትዮመዲያ፣ በኢካዲኤፍ፣ በአዲስ ቮይስ፣ በኢኤምኤፍ እና በጎልጎልጕል ድረ-ገጾች የተበተነው በእንግሊዝኛ ተደርሶ ነበር። በጣም ብዙ አስተያየት ሰጪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዬም ኢ-ሜይል ሳይቀር የተሰማቸውን አካፍለውኛል። ሁሉም ወደ አማርኛ እንደመልሰውና ብዙ ኢትዮጵያውያን ለማንበብ ዕድል እንዲያገኙ አጥብቀው ስለአሳሰቡኝ ጥይቄአቸውን ተቀብዬ ወደ አማርኛ መለስኩት።The Fake ‘Amharas’ – To milk “Lamie Bora

ከኢትዮጵያ የሚደርሱን ቀልዶች ለዛቸው ጨምሯል። ሰሞኑን፣ አንድ ከአገር ቤት የመጣ እንግዳ፣ የወያኔ ባለሥልጣናት፣ ዲያስፖራን “ላሜ ቦራ” እያሉ እንደሚሾፉብን አጫውቶን አዝናንቶናል። እውን እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ የተሰደድን ኢትዮጵያውያን ያለማቋረጥ የምንታለብ የካሽ ጥገቶች ነን?

መቼም በኔ ዕድሜ ትምህርት ቤት የሄዳችሁ ሁሉ፣ስለላሜ ቦራ የተተረከ የልጆች ጣፋጭም አሳዛኝም ታሪክ ሳታነቡ ወይም ሳይነበብላችሁ አልቀረም። የላሜ ቦራ ታሪክ እጅግ አንጀት የሚበላ ተረት ነው። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዲት ሁለት ሕጻናት የነበሯት እናት በጣም አሟት በአልጋዋ ላይ ሁና ትጣጣራለች። እሷ ስትሞት ባሏ ሌላ ሚስት ካገባ፣ የእንጀራ እናት በልጆቿ ላይ ለታደርስ የምችለውን ጭካኔ ስትገምተው ከራሷ መሞት በላይ አስጨነቃት። ከዚህም የተነሳ፣ ሰው አላምን ብላ (ሰው ምን ይታመናል? ዛሬ እዚህ ብታስቀምጠው ነገ ሌላ ቦታ ተንሸራትቶ ታገኘዋለህ) የምትወዳትን ላሜ ቦራ የተባለችውን ላሟን አልጋዋ ድረስ አስመጣቻት። “ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ” ብላ አዜማ እንደ ጨረሰች ሞተች። ሟቿ እናት እንደገመተችውም፣ የልጆቹ አባት፣ ብዙም ሳይቆይ ሌላ ሚስት አገባ። እንጀራ እናቲቱ ሕጻናቱ የሷ ልጆች ባለመሆናቸው በጣም ጨከነችባቸው። በረሀብ መንምነው እንዲሞቱ፣ ምግብም ትከለክላቸው ገባች። ልጆቹ ሲርባቸው፣ በቀጥታ ወደላሚቱ እየሄዱ፣ “ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የእማምዬን አደራ” ብለው ሲያዜሙላት፣ ላሜ ቦራ እግሮቿን ፍረክረክ አድርጋ ከጦቶቿ በቀጥታ ወተት እንዲጠቡ ታደርግ ነበር። ቀሪው ታሪክ ገብስ ነው። የሚገርመው ነገር፣ ላሜ ቦራ ያለመንጥፏ ነው። ክረመቱንም በጋውንም ዓመቱን ሙሉ ብትታለብ፣ ብትታለብ የማትነጥፍ የወትት ጅረት ናት ተብሎ ነው የሚገመተው!

ወያኔዎች፣ በሚያስገርም አኩኋን ታርኩን ዲያፖራው ላይ ደገሙልን። ታዲያ ታሪኩ በዲያስፖራው (ውጭ አገር ኗሪውን ኢትዮጵያዊ) ላይ መሆኑ አያንገበግብም? ያርገበግባል ኢንጂ። “ዲያስፖራ – ላሜ ቦራ” አሉን? ዕውነት አላቸው። ምን ያድርጉ! “አረሱት! አረሱት! የመተማን መሬት! የአርማጨውን መሬት፣ ያውም የኛ ዕጣ፣ እነሱ ምን ያርጉ ከኝ ሰው ሲታጣ!” ብሎ ደምድሞት የለ ዘፋኙ! ወያኔዎች፣ የወጭ ምንዛሬ በደረቀባቸው ቁጥር ጨርቄን ማቄን ሳይሉ፣ ባዶ ሻንጣቸውን አንጠልጥለው ወደ ዲያስፖራ – “ካሽ ጥገት”፣ ከተር ነዋ! ከዚህ ቢታለብ-ቢታለብ ከማይነጥፈውን ጥገት ዲያስፖራ በተለያየ ምክኒያት ተሰዶ በብዛት ከሚኖርበት የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች፣ እንደለነድንና ዋሽንግተን ካሉት ከቸች ነዋ! ለዚህ እንዲመቻች ደግሞ፣ ከዚህ በፊት እንዴት ተደርጎ ዲያስፖራው ሊጠመድ እንደሚችል፣ 52 ገጾች[1] በፈጀ ምርምር ጥናትና ዕቅድ ተነድፎ የወያኔ ኤምባሲዎች ሥልጠና አግኝተዋል። ላሜ ቦራን እያጠመዱ ይዞ ድርቅ እስክትል ድረስ እልብ ነዋ! ቅርብ ጊዜ ከተፈጥሩት ወጥመዶች መሀል፣ “የሕዳሴ ደደብ” (ይቅርታ፣ “ግድብ” ማለት ፈልጌ አዳልጦኝ ነው) ቦምብ፣ ውይ በሞቴ -ቦንድ ሽያጭ ነው። “አባይን ለደፈረ መንግስታችን ገንዘብ?” እንዴታ! ሌላው፣ የተለያዩ ለጥቅም የተደለሉ ላሜ ቦራዎችን እየሰበሰቡ፣ በየዘር ሀረጋቸው የሌማት – ይቅርታ ኦሆሆ ምን ነካኝ ዛሬ! – “ልማት” ማኅበር ማደራጀት ነው። ሌላው “ኢንበስተሮች” የሚል ሹመት ብጤ ስጥቶ፣ ላሜ ቦራዎቹ አድረገዋቸው አገር ቤት ንዋይ እንዲያፈሱ አግባብቶ ጠልፎ ማለብ ነው። ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ያማረች አሽክላ ፈጥረው መጥተውልናል። 40/60 የሚሉት በአቋራጭ የቤት ማግኛ ፎርሙላ ወይም ቀመር ነው። አንድ ሎንደን ውስጥ ቤተክርስቲያናችንን ካዘጉት ካህናት መሀል፣ ሰሞኑን በዚያ ፎርሙላ ተጠቃሚ ለምሆን ሌሎቹን ጓደኞቹን አስከትሎ ሲሂድ፣ ጥግብ ያሉት የወያኔ እልፍኝ አስከልካዮች፣ “አንተ የላሜ ቦራን መስፈርት አታሟላም” ብለው ሲከለክሉት ሰድቦአቸው እንደሂደ ሰምተን ስንስቅ ነበር። አይ መሪጌታ! ቅኔውናንና ዜማውን እንደ ጅረት ስታወርድለት ወዶህ የነበረ አምላክ አዝኖልህ፣ እስክትደርቅ ከመታለብ አተረፈህ! ይልቁንስ ነዴቱን ትተህ “ሐሌ ሉያ” በል!

ወያኔዎችን የሚያዋጣቸው ፍቱን ዘዴ ሁኖ የተገኘው አንዳንድ ጅላጆሎችን በብሔር ብሔረሰባቸው አደራጅቶ የልማት ማኅበር ማቋቋም ነው፡፡ ዘረኝነት ደግሞ አንዴ ከተጠናወተ የማይለቅ ውርዴ ነው። በዚህ መንገድ፣ “የአማራ የልማት ማህበር፣”፣ “የኦሮሞ የልማት ማህበር፣” “የሲዳማ የልማት ማህበር” ወዘተ እያሉ መድበዋቸው ወይ ያልቧቸዋል፣ ወይ አሰልጥነው ሌሎቹን ላሜ ቦራዎች ያሳልቧቸዋል። ከየብሔረሰቡ የተገኙ ጥቂት ሆድ አደሮች ካልሆኑ በስተቀር፣ ተደጋግመው ማህበራቱን የሞሉት እነዚያው የፈረደባቸው ጥቂት የማይባሉ ከትግራይ የተገኙ “የወርቅ” ዝርያ አባሎች ናቸው። የአማራ በዓል ላይ እነሱ ናቸው “እስክስ” የሚሉት! የኦሮሞው በዓል ላይም እነዚህው ናቸው “ሆ!” የሚሉት! የትግሬም በዓል ላይ እነሱው ናቸው “አጅዋ!” የሚሉት።

በዚህ ወር ላሜ ቦራን የማለቡ ተራ፣ ወያኔ ኤምባሲ ግቢ ተወልዶ ፍርፋሪ እየበላ ያደገው “የአማራ የልማት ማህበር” ነው። “በአማራው ማኅበር” ሥር የተደራጁት ዕውነተኛ አማሮች ሳይሆኑ በሙሉ ቁጭአማሮች ናቸው። የዘር ሐረጋቸውን እንደውያኔዎች ከቆጠርን፣ አማራ ሳይሆኑ የአማሩ ማለት ነው። እርግጥ አንዳንድ እንደያለው ከበደ ያሉ ወዶ ገቡች አይጠፉም። እነዚህ ማህበራት “የልማት” (የ”ጥፋት” ማህበራት ማላቱ ይቀላል፟)፣ ለማወናበድ እንዲመች ስማቸው ተቀየረ እንጂ፣ ወያኔ ለየአንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ በአገር ቤት ለለጠፋላቸው ዋና ዋናዎቹ የወያኔ አገልጋይ ተለጣፊ የፖሊቲካ ድርጅቶች “የድጋፍ ኮሚቴዎች” ናቸው። እንደ ኦሕዴድ፣ ብአዴን … ምናምኖች ማለቴ ነው።

እስቲ ከነዚህ በዘር ከተደራጁት አንዱን የአማራን ብሔረሰብ እንዲቀብርላቸው የፈጥሩትን ተለጣፊ የአማራ ድርግጅት ቀርብ ብለን እንይ! ይኸምውም “የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ብአዴን) ነው። ለአማራው ሕዝብ ለመቀጥቀጥ የተጠፈጠፈለት መዶሻ ነው። (አንጽሮዕተ ስሙ ሲደብር!) ይኸን ድርጅት ወያኔዎች ጠፍጠፈው የሠሩት፣ በትቅምት ወር ፲፱፻፸፪ ዓ› ም› (Nov. 1980) ኢሕአፓን በድንገት ደርሰውበት አባላቱን ከጨፈጨፏቸው በኋላ፣ ከሞት ካተረፏቸው ምርኮች ሰብስበው “ተክራርዉሀ” በተባለ ስፍራ ነበር። ድርጅቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ (ኢሕድን) ነበር። ዕውነትም፣ በጊዜው ኢሕአፓ አባላቱ ዘር ቆጥረው የተደራጁ ሳይሆኑ ከሁሉም ብሔረሶቦች የተወጣጡ ነበርና ምርኮኞች ቢሆኑም ስሙ ትክክለኛ ነበር። ወያኔ ግን “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም መስማት ስለማይፈልግ፣ በዘዴ “ብሔር አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ብአዴን) ብሎ እንደገና አጠመቀው። አርማም ቀርጾ ሰጠው። ታዲያ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ አመራሩን የያዙት ቁጩ አማሮች እንጂ አማራ በመብራትም ቢፈልግ አመራሩ ውስጥ አይገኝም። በመጀመሪያ ረድፍ የሚገኘው ቁጩ አማራ፣ አማራን በጣም የሚጠላ፣ አማርኛን መናገር የሚጠይፍ፣ ሻቦ ባንዳ፣ እናቱም አባቱም ከኤርትራ የፈለቁ፣ ጎንደር የተወለደ “በረከት ስምዖን”፣ ሕወነተኛ ስሙ ግን መብራቱ ገብረሕይወት የተባለው ነፍሰ ገዳይ ነው። ሒላዊ (ዕውነተኝ ስሙ “ፍቅሬ”) ዮሴፍ ወይ የእርትራ፣ አለበለዚያም የትግራይ ትግሬ እንጂ፣ አንዲት ጠብታ ደም በደም-ሥሩ ውስጥ የማትዘዋወር ቁጩ አማራ ነው። ታደሰ ጥንቅሹ (ዕውነተኛ ስሙ ታደስ ካሳ) ስሙን ቢያምር እንጂ፣ የትግራይ ትግሬ በመሆኑ፣ አማራነቱ በዲ ኤን ኤ ኤክስፐርትም ቢመረመር አይገኝበትም። ተፈራ ዋልዋ፣ ጊሚራ ነው። አማራና ጊሚራ ድምጹ ለጆሮ ቢመሳሰል እንጂ፣ አምሮም አያውቅም። ተፈራ ዋልዋ አማራ ነው የሚለኝ ሰው ካለ እራሱን የስነ አዕምሮ ሐኪም ጋ ሂዶ ይመርምር። ያስ ደግሞ፣ በአማራነት ሲያጭበረብረን የኖረ ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ? ስማቸውን እየቀየሩ እኮ ነው የሚያምታቱን። ለመሆኑ ጌታቸው ማሞ ዋቅኬኔ መሆኑን ስንታችሁ ናችሁ የምታውቁት? ስለዋኬኔ አማራነት እናንተው መርምራችሁ ድረሱበት። አዲሱ ለገሰ፣ ሰሙ ነው እንጂ አማራ፣ የሐረር ቆቱ ነው። አያሌው ጎበዜስ ቢሆን አማራ ነው? በአማራና በአገው መሀል ብዙም ልዩነት ባይታይም፣ ለሥልጣን የበቃው በአማራነቱ ሳይሆን ነገሩ ሌላ ነው። ቁጩ አማሮች በመሆናቸው አይደል፣ የአማራው መሬት ከጎንደር ተነጥቆ ለትግራይ፣ ከወሎ ተቆርጦ ለትግራይ ሲሰጥ፣ ጭጭ ብለው የተቀበሉት! እሱስ ይሁን ትግራይ የኛ ናት! የአማራው መሬት ተቦድሶ ለሱዳን ሲሰጥ የማያማቸው ቁጩ አማሮች በመሆናቸው አይደል! ቁጩ አማሮች ቢሆኑም አይደል፣ የዋልድባ መነኩሳት ሲደበደቡ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የተቀመጡት። ቁጩ አማሮች ቢሆኑ አይደል፣ አማሮች ከየክልሉ ቁምጥና እንደያዘው ከቄዬአቸው ተፈንቅለው ሲባረሩ፣ ከየክፍለ ዞኖች ከቤታቸው ተመንግለው ሲሰደዱ የማያማቸው? ቁጩ አምሮች በመሆናቸው እኮ ነው፣ የወያኔ መሠሪዎች አማሮች እንዳይወልዱ በኪኒን ስያመክኗቸው በዓይናቸው ብሌን እያዩ ትንፍሽ የማይሉት። ውጪ አገር በአማራ ልማት መልክ የተደራጁትም እንግዲህ የዚያው መልክ የተጠፈጠፉ ተቀጥሎች ናቸው! ሌሎችም ብሔረሰቦችን እነወክላለን የሚሉት፣ ቁጩ ኦሮሞዎች፣ ቁጩ ጉራጌዎች … በዚህ አኳኋን ነው የተፈጠሩት።

ወደ ላሜ ቦራችን ስንመለስ፣ ላሜ ቦራዎችን ለማለብ የተደራጁት፣ “የአማራ ልማት ማህበር – ዩኬ” (“Amhara’ Development Association – UK”) የተብለው ነው። እነማን እንደሆኑ ለማወቅ፣ ከፈለጋችሁ፣ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 2011 የገነዘብ ማሰባሰቢያ በዓላቸውን ሲያከብሩ የተቀዱትን ፊልም አብረን እንይ። http://www.youtube.com/watch?v=8fmeHCLPgpU።

መቼም ለንደን የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እዚያ ፊልሙ ላይ ከሚታዩት ማን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። ከተሳሳትኩ አርሙኝ። እንደ አለማየሁ (አሌክስ) ብርሀኑ ያሉ የለየላቸው ትግሬዎች ናቸው። አለበለዚያ ጃማይካኖች ናቸው (ጀማይካኖቹ ቁጩ አማሮ ሲሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነው)፣ እንግዲህ በጣት የሚቆጠሩ የሌሎች ብሔርሰቦች (ሞቅዲሾ ሶማሌዎች ሳይቀሩ) አባላትና ሆዳደር አማሮች ሊታዩ ይችላሉ። የለየለት ሆድ አደር አማራ፣ ያለው ከበደ በር ጠባቂ በመሆኑ አታዩትም። ታዲያ ያ ሆዱ የተቀፈደደው፣ እንግዶቹ በልተው፣ ጠጥተው ጠግበው ሲሄዱ ቀሪውን ፍርፋሪ እየበላ መሆን አለበት።

በዚህ ዓመት ሎንደን ውስጥ፣ ዲያስፖራ ላሜ ቦራን ለማለብ የታቀደው 28 September 2013 ነው። መግቢያው በነጻ ነው። ሁላችንም ተጋብዘናል። ምግብ መጠጥም በሽበሽ ነው። ለምን ሁላችንም ግልብጥ ብለን ሂደን አንጋበዝላቸውም? ታዲያ ኪሳችሁንና ሆዳችሁን ባዶ አድርጋችሁ ነው መሄድ! በመተት እንዳትታለቡ! ሌላ የረሳሁት! የቁጩ አማሮችን የገንዘብ ማሰባሰቢያ በዓል ማን እንዳስተዋውቅላቸው ታውቃላችሁ? http://www.tigraionline.com/’Amhara’-ada-event-uk.html! ሌሎችማ ድረ-ገጾች ምን ቁርጥ ቢያደርጋቸው ነው የቁጩ አማሮችን ዝግጅት የሚያስተዋውቁላቸው!

ቁጩ አማሮች መቼም ሕሊና የምትባል አልተፈጠረችባቸውም። ወያኔዎች የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሲደርቅባቸው ነው የሚፍልጓቸው። ቢሞቱ ይሻላቸዋል። የላሜ ቦራ አላቢዎች ናቸው። ቁጩ አምሮች ካልረዷቸው በስተቀር፣ የወያኔ አምባሳደሮችማ ሥራቸውን መሥራት አቅቶአቸው፣ ሰሞኑን ከየኤምባሲው እየተባረሩ ነው። ኢትዮጵያዊው በየከተማው ውርደት እያከናነባቸው፣ ባዶ ኮሮጆአቸውን እያሸከማቸው ወደመጡበት ስለመለሳቸው፣ ያላቸው ምርጫ፣ ቁጩ አማሮችን የሙጥኝ ይዘው ወራዳ ሥራቸውን እንደሠሩላቸው ማሠማራት ነው። ውሻ በር በድንብ እንዲጠብቅ ከተፈለገ፣ በየጊዜው ልፋጭ ይወረወርለታል።

አሁን በጥሩ ሁኔታ ወያኔዎች ላሜ ቦራን ለማለብ የፈበረኩት ዘዴ፣ ይኸ 40/60 የተባለው ቀመር ነው። ፎርሙላው የሚሠራው፣ እንዲህ ነው። ታላቢው ላሜ ቦራ ዲያስፖራ 40 ከመቶውን በውጭ ምንዛሪ ይከፍላል። 60 በመቶውን ወያኔ በብድር መልክ ይሸፍል። 100% በዶላር፣ በዩሮ፣ በፓወንድ (ሀርድ ከረንሲ) ለሚከፍል ቅድሚያ ይሰጣል። ለዚህ ተብሎ የተሠሩ ቤቶች አሉና፣ ዲያስፖራ ሆዬ በቀጥታ አዲስ አበባ ሂዶ መረከብ ነው ተብሎ ተሰብኳል። ለዚያ የሚጣደፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሞልተዋል። ምነው ቢባሉ፣ “እንዴ ለወያኔ ብቻ ማን አጋሪቱን ሰጣቸው፣ እኛም እመሀላቸው ገብተን ቦርቡረን ከውስጥ ገዝግዘን እንጣላቸው” የሚሉ ወንድሞች አጋጥመውኛል። ወያኔ ከግምታችን በላይ ተንኰለኛ ነው። አባላቱ ሲፈጠሩ እኮ ተንኰልን ከሆድ ተምረው ነው የሚወጡት። እነሱ ዕቅዳቸው ላሜ ቦራን አስጠግተው፣ ሙልጭ አድርገው በደርቁ ሊያልቡ እንጂ ሊታለቡ እንዳልሁነ ማወቅ ይኖርብናል። ሌባን ደህና ሰው ሊሰርቀው፣ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። ቤት አዲስ አበባ ይኖረኛል ብሎ ወያኔን መጠጋት፣ አንደኛ፣ አድራሻ ለመስጠት፣ ከዚያም ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ላለመውጣት፣ ከዚያም አሻራ ሰጥቶ የወያኔ ንብረት ለመሆን ነው። ወያኔ አልቦህ ሲጨርስ፣ እንደማስቲካ መጥቶ፣ “ኪራይ ሰብሳቢ” ብሎ ይተፋሀል። የኢትዮጵያ መሬት እንዳለ የወያኔ ንብረት መሆኑን ለአንዳችም ደቂቃ አንዳንስት። ወያኔ ሲፈልግ፣ “መሬቱ ለልማት ይፈለጋል፣ ሞርታርህንና ጡብህን ይዘህ ብትፍልግ አንጨቆረር ውረድ” ብሎ ያሾፋል። ነገሩ ከዚህ በፊት ስለደረሰ ነው እንዲህ የምላችሁ፣ ያጣ ወሬ ሁኖብኝ አይደለም። ሰዎች ሲሸወዱ አይቼ ነው። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽም አይክፋሽ ከመባል አምላክ ያድናችሁ።

ከወያኔ ጋራ ሕሊና ሳይሸጡ ቢዝነስ መሥራት አይቻልም። ሥርዓቱ የነቀዘ ሥርዓት ነው። በጥቅም ተስባችሁ ወደወያኔ ስትቀርቡ የሞቱትን እንኳን ባትስቡ፣ እስቲ እስር ቤት በግፍ የሚማቅቁትን እነ ርዕዮት ዓለሙን፣ አንዱዓለም አራጌን፣ እስክንድር ነጋን፣ ናትናኤል መኰንንን፣ ክንፈሚካኤል ደበበን፣ ዮሐንስ ተረፈን፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁናለምን፣ አንዱዓለም አያሌውን፣ በአሥርት ሺህ የሚቆጠሩትን የኦሮሞ ብሔርሰብ አባል እስረኞችንና፣ የእስልምና ሀማኖት መሪዎችን ስቃይና እንግልት አስቡ። ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በመሆናቸው ጥቃታቸው ይሰማን።

ዲያስፖራ ስደተኛ ወንድሞቼና እህቶቼ! አታስፎግሩን (በአራዳ አማርኛ)! እሺ ለታሠሩት፣ ለሚንገላቱ የሚራራ አንጀት ባይኖራችሁ፣ ላማንም ደንታ እንኳን ባያኖራችሁ ለራሳችሁ አስቡ። ገንዘባችሁን እየወሰዳችሁ አታስረክቡ። ወያኔ አምጣ-አምጣ እንጂ ሕንካ-ሕንካ የሚል አማርኛ መዝገበ ቃላቱ (ድክሺነሪው) ውስጥ የለም። ሰዶ ማሳደድ ካላማራችሁ፣ ገንዘባችሁን ሌላ ቦታ ብታስቀምጡ ደህና ገቢ ይኖራችኋል። አለበለዚያም፣ እናንተው በገንዘባችሁ እንደፈለጋችሁ የፈለጋችሁን ግዙበት፣ ብሉበት፣ ጠጡብት፣ ልበሱበት። ላሜ ቦራ መባል ይቅርባችሁ። ዛሬ አንዳንድ ላሜ ቦራዎች እንኳን ነቅተው የራሳቸውን ወተት ለራሳቸው መጠጣት ለምደዋል። እምቧ ከምትለዋ ላም ታንሳላችሁ? እስቲ የላሜ ቦራን ብልጠት በዝህች ፊልም ተመለክቱ!

posted by Daniel tesfaye

እንደ ቆራጥ ንስር ፓይለቶቹ…

26351fb59e29fb0a1375427042
September 26, 2013
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዋና የመነጋገሪያ አርዕስት የነበረው አራት የአየር ሃይል አብራሪዎችና አስልጣኝ መኮንኖች ከዘረኞቹና ከዘራፊዎቹ ጎራ ወጥተው ወደ ነፃነት ታጋዮች ጎራ የመቀላቀላቸው ጉዳይ ነበር። እነዚህ ቆራጥና አገር ወዳድ አብራረዎች የወሰዱት እርምጃ ወገንን የሚያኮራና ከፍተኛ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትልቅ ውሳኔ ነው።ይህ ውሳኔ ሰው ባጣች አገር፤ጀግና ባጣች አገር፤ለአገር ለወገን ተቆርቋሪ ባጣች አገር ውስጥ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በያለበት በተለያየ መንገድ ይህን የጀግና ውሳኔ የወሰኑ ልጆቹን እያደነቀም እያመሰገነም ይገኛል::

የግንቦት ሰባት ንቅናቄም ይህን የጀግና ውስኔ የወሰኑ ወንድሞቹን እንኳን ተወለዳችሁ፤ እንኳንም ተማራችሁ፤ እንኳንም ወደ ነፃነቱ ትግል ተቀላቀላችሁ እያለ ደስታውንና ለጀግኖቹ ያለዉን ከፍተኛ አክብሮት ይገልፃል። ውሳኔያችሁ ከፈርዖን ቤተ-መንግስት ምቾት ይልቅ ከህዝቤ ጋር መሰደደ ይሻለኛል ያለውን የታላቁን ሰው የሙሴን ውሳኔ ይመስላልና የወሰዳችሁትን ትክክለኛ እርምጃ ትውልድ ምን ግዜም አይረሳዉም።

የእነዚህ ቆራጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች፣ ሙያና ችሎታ ስጋዊ የሆነ ፍላጎታቸውን ለማርካት ከበቂ በላይ ነው።ከዘረኞቹና ከቃየላውያኑ ቡድኖች ጋር እየተሞዳሞዱ ለመኖርም የሚሳናቸው አልነበሩም።ሆኖም ግን ዘረኞቹ(ህወሃቶች) የሚፈፅሙትን ግፍ ተሸክመው ፤ብኩርናቸውን ሽጠው እና ከሰው ተራ ወርደው ለመኖር ሂሊናችው አልፈቀደላቸውም።ለሚበላና ለሚጠጣ ከንቱ ነገር ብለው ጥቂት ዘረኞችን ተሸክሞ ከመኖር ይልቅ የነፃነቱን መንገድ መርጠዋልና ጀግኖች ብለን ብናወድሳቸው ተገቢ ይሆናል። እንዲህ ዓይነቱን ውሳኔ የሚወስን ሃሞተ ኮስታራ ጀግና እንጂ ሌላ አይደለም።

አሁንም ለራሳችሁ ክብር ያላችሁና ተመሳሳይ እርምጃ ለመዉሰድ በዝግጅት ላይ የምትገኙ የአገር መከላከያ አባላት እንዳላችሁ እናውቃለን። ቅምጥሎቹ ጄኔራል ተብየዎች ከድሃ ወገኖቻችሁ ላይ የዘረፉትን ዘርፈው አገሪቷን ጥለው መሄድ ጀምረዋል። ቀሪዎችም የዘረፉትን የድሃ ንብረት ወደ ውጪ አገር እያሸሹ እንደሆነም ይታወቃል።በአጠቃላይ በእናንተ ምርኩዝነት አገራችንን እያፈራረሷት፤ህዝቧንም እያወረዷት ነው።የህዝቡም መከራና እሮሮ ተወርቶ የሚያልቅ አይደለም።እንዲህ አይነቱን ግፍና በደል እያዩ ከንፈር መምጠጥ እያበቃ ነው።እንግዲህ አሁን እኔ ብቻየን ምን አደርጋለሁ የሚባልበት ግዜ እያለፈ ነው።ጋሻ መከታ እና የኋላ ደጀን የሚሆኗችሁ ብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን በየቦታው አሉ።ብትወድቁ የሚያነሷችሁ፤ብትደሙ ደማችሁን የሚያብሱላችሁ፤ብትሰው መስዋእትነታችሁን ለትውልድ የሚዘክሩላችሁ ወገን አለላችሁ።አትፍሩ። ከዘረኞቹ መንደር ወጥታችሁ የነፃነቱን ትግል እንድትቀላቀሉ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

ህውሃት ማለት የዘራፊዎች እና የጨካኝ ነፍሰ ገዳዮች ስብስብ መሆኑን ያለምንም ጥርጥር ማመን አለባችሁ።ህወሃት ስንቱን አርዶ፤ስንቱን ገድሎ፤ስንቱን አጥፍቶ፤የስንቱን ኑሮ በትኖ፤ስንቱን ዘርፎ ባዶ እጁን አስቀርቶ በትረ ስልጣኑን እንደያዘ ምስክር የሚያስፈልገን አይደለም።

የህውሃት ዘረኝነትና ዝሪፊያ የቆጨህ እና ለራስህ ክብር ያለህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተነስተህ ትግሉን ተቀላቀል።እነዚህን ግፈኞች የሚፈፅሙትን በደል እያዩ ዝም ማለት ግፉን ከመደገፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።እናንተ ለራሳችሁ፤ ለወገናችሁና ለአገራቸችሁ ክብር ያላችሁ ዜጎች ዝም በማለታችሁ ህወሃቶች ዝምታችሁን እንደ በጎ ፈቃድ ቆጥረውት የግፍ ሰይፋቸውን ወደ ሰገባው ሊመልሱ ፈቃደኞች አልሆኑም።በማን አለበኝነታችውም ፀንተው ቆመዋል።እነዚህን ግፈኞች በቃ ለማለት ግዜው ደርሷልና የነፃነቱን ትግል ሳትዘገዩ አሁኑኑ ተቀላቀሉ።

እኛም ወደ ነፃነት ትግሉ እንድትቀላቀሉ ጥሪ ስናደርግላችሁ ለአገራችን ክብርና ለወገኖቻችን በሰላም መኖር ስንል ቆርጠን የተነሳን መሆናችንን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በምንም ሁኔታ በዘረኞች እጅ ተንቆና ተዋርዶ መኖርን አይቀበልም።እንዲህ ዓይነቱን ውርደት ተቀብሎ ለመኖር ሰው መሆናችን ይከለክለናል።እነዚህን ዘራፊዎች ተሸክመን ከመኖር ከነፃነታችን ጋር አያቶቻችን በተሰውበት ተራራ ላይ ቆመን መሰዋትን እንመርጣለን።አሁን ተነስተናልና የሚያቆመን የለም። እግዚአብሄርም መንገዳችንን ያከናውንልናል። ኑ ሀገርን ለማዳን የነጻነት ትግሉን ጎራ ተቀላቀሉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

posted by Daniel tesfaye

A must-watch ESAT Special on Ginbot 7 Meeting in Washington DC (Part 1)

     September 26, 2013           

 

 

Editor’s Note: On Sunday September 22, 2013, the Ginbot 7 leadership had a very revealing and open discussion in Washington DC meeting like it has never had before . As you know, the issue of working with Eritrea has been a bone in the throat for G7 as well as for its supporters around the world. Many have argued against using Eritrea as a spring board to wage an armed struggle against TPLF.
Opponents claim that Eritrea can not be trusted based on their experience with Isayas Afeworki so far and his public rhetoric as it relates to Ethiopia. They may have a point. But the problem is that they don’t practice the position they defend or argue for. They don’t provide an alternative and actually implement that alternative. For example, they don’t answer to the question of where to wage an armed struggle and show us the way by an example.  They don’t. For instance, what don’t they find a place within Ethiopia and wage an armed struggle? What do they go and practice what they preach instead of simply analyzing and arguing from the comfort of their homes in the West. What they do is simply disagree and sometimes with bitterness and even animosity against G7 position towards Eritrea.
Instead of making an honest and logical attempt to convince and win our support, those who oppose G7′s position in Eritrea use intimidation, name callings, insults, put downs and inuendos to impose their opinion on G7 and its supporters. But the irony is that these forces claim to believe and fight for democracy in Ethiopia and yet they impose their position on others. G7 has repeatedly expressed the right of any political entity to follow a path it believes in without imposing its policy or belief on any one else except asking their support.

G7 has often made clear that it does not oppose other political parties who pursue a political path different than its own. It is interesting whether we know how to win support with a clean logical argument backed by results in the ground instead of an endless ineundos and name callings. 
Those who opposes G7 are not all  in the same wave length. Pro-TPLF mercenaries like Awramba Times editor are going against G7 to accomplish their paid assignments. There is no surprise about them. They are part of the package. There is also a second group that questions and suspects a multi-national political force like G7 for fear of revenge by TPLF victims in the form of genocide or a lesser nationwide violence against the Tigrian population.
 These group has a legitmate fear. But opposing such a political force as G7 is not a solution to their fear. In fact, a force such as G7, if strengthened, may help stabilize the country by preventing a possible chaos and ethnic violence in Ethiopia when TPLF collapses.
And there is a third group. These are political organizations who are competing for power in Ethiopia after TPLF. They believe if they don’t cook the dish, it does not taste good. They want power at any cost and by any means necessary. They are ego-driven and uncompromising. Nothing satisfies them until they are in power to implement their belief. They oppose everything any opponent does. They deliberately or honestly believe that truth is on their side. Doing so is wounding their ego and it is relinquishing the possibility of power in Ethiopia.

There is one final group which I consider innocent but suspicious. Our story with Eritrea is full of suspicions and actual heart-breaking experience due to the war waged between Ethiopia and Eritrea for over 40 years now. They don’t trust anything related to Eritrea no matter who said what including God. These group has a legitmate concern but suspicion should not tie our hands and prevent us from doing what needs to be done. Our situation today is desperate. TPLF has done and still doing all it can to destroy our people and country. These suspicioius group should know that there are times in life when you have to do what you got to do to get out of a rock and hard place by swallowing our pride and controlling our suspicion.There is a saying in our country,” ቀን እስኪአልፍልህ የአባትህ ባርያ ይግዛህ” that we should follow. These group has no alternative except to give it a try while holding its suspicions. At this point, all of us have one universal enemy. And we have to focus on it. And that is TPLF. And it is wise to talk about our differences after we free Ethiopia from TPLF by any means necessary.

The G7 leadership has directly presented the question in a ‘take it or leave’ it manner to the audience and the Diaspora watching on ESAT.
Berhanu and Andi 5
Click the image above to watch the G7 meeting in DC on September 22, 2013
Ato Andargachew Tsige, secretary of G7, has explained in detail about the Eritrean question during the meeting. It may be hard to tell if every body is convinced. With all their suspicions remaining, there is no doubt many may be considering to give G7′s policy on Eritrea a chance, if it has any possibility of working, given the dire and critical circumstances Ethiopia has found itself at this time. 
There is no sure thing in life as well as in struggle. You take chances and you take risks. Not a blind risk but a pragmatic one based on the circumstances you found yourself boxed in. Not taking that risk, no matter how difficult, is committing a self-inflicted suicide. You put all your options on the table. And you pick the one with the least risk. And then you move on.
 And if not, the choice is to get stuck in some meaningless and fruitless activity and continue to waste time, money and even lives for nothing and finally give up and be forgotten. G7 seems to have made a decision to take the least risky option, according to Ato Andargachew Tsige, and is pursuing it with resolve. 
And for those of us with an apposing view, let us do what we believe in without imposing our position on G7 and its policy towards Eritrea. According to Ato Andargachew Tsige, G7 is not imposing its position on any person or political entity. He said they don’t oppose the positions other political organizations are taking when it comes to Eritrea or any other political position.
The take home message is that, we in the opposition camp, should all follow our individual political choices in our quest to remove TPLF from power without attacking each other. We all don’t have to come to the same conclusion. Let us just disagree without being disagreeable. There is no need to vehemently be involved in slash and burn campaign against a position we don’t agree on. First, it is not democratic. Second, it is nasty. We will sound like the dictators we claim to hate like Mensgistu and Meles. No one party or person has the monopoly on the truth of what works best to bring TPLF down. The only way to establish that truth is based on the results of a given policy on the ground. And let us all give a chance, with patience, to see what works with our suspicions still intact

posted by Daniel tesfaye

Post Navigation