FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

ከእስክንድር ናፍቆት እስከ አንድነት ዘመነ … -ከነብዩ ሲራክ

1044303_169829796523576_1916727500_n

Mars 13,2015

አይዞህ ወንድም አለም …

…ምስላቸውን ተመልክቸ ፣ ታሪካቸውን ሰምቸ ስሜቴን ካናወጡት ጥቂት ምስሎች መካከል ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቅምጥል ከታዳጊ ናፍቆት በቅርቡ አባቱን ከታሳሪዎች መካከል ሲያፈላልግ የተነሳው የፖለቲከኛው ዘመነ ምህረት ልጅ አንድነት ዘመነ ተናጋሪ ምስልን ከሃገር ውስጥ ካየኋቸው ስሜት ኮርኳሪ ተናጋሪ ምስሎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። …

ከሃገር ወጣ ሲባል ደግሞ አስተማሪው በሞት የተነጠቀው ጥቁር ደቡበ አሜሪካዊ ማደጎ ዲያጎ አሳዳጊውን በሞት ተነጥቆ እንባ እያዘራ የሚያሳየው ምስልና ፍልስጥኤማውያኑ አባትና ልጅ አይዘነጉኝም!
ዲያጎ …

… ብራዚላዊ ወጣት ዲያጎ ከድህነትና አመጽ ነጻ ያወጡት የሙዚቃ አስማሪው በድንገት ተገድለው በቀብሩ ስነ ስርዓት ተገኝቶ ለሚወዳቸው የሙያና አባቱና ሰብአዊው ሰው ያለውን ክበር እንባውን እያዘራ ፍቅሩን ሲገልጽ የሚያሳየው ምስል ልብ በሃዘን ሰባሪ ነው …
መሀመድ አል ዱራህ …

ከሁሉም በቀዳሚነት ግን በእጎአ በ 200ዐ ዓም የሁለተኛው ፍልስጥኤማውታን አመጻ “ኢንቲፋዳ ” ወቅት ነበር ። በዚሀ ወቅት በሃገረ ፍልስጥኤም በአንድ የፍልስጥኤም አባትና ልጅ ምስል አሳዛኝ ትዕይንትና በጥይት የተደበደቡት አባትና ልጅ ህይዎቴንና እሳቤየን በብዙ መልኩ ቀይሮታል ። ..ድርጊቲ የተፈጸመው በማትረጋው ፍልስጥኤም ውስጥ ነው …በወቅቱ አመጻ ነውጥ ተነስቶ በነውጥ ሁከቱ መሀመድ አል ዱራ የተባለ አንድ ታዳጊ አባትቱን እየተከተለ በሽሽት እየሮጠ ከግርግሩ ሊያመልጥ ሲሞክር ይታያል። ብዙመ, ሳይቆይ አባትና ልጅ ከጥይቱ እርምታ ለማምለጥ በአንድ አጥር ተጠለሉ። ልጅ ከአባቱ ጀርባ ቢለጠፍም አባት የብላቴና ልጁን ህይዎት መታደግ ቀርቶ ራሱን ማዳን አልቻለም። በአጥሩ ታዛ አባት ተጎንብሶና ከጀርባው ተጣብቆ እጁን ከወደ ኋላው በመላክ በፍርሃቻ የሚርድ የሚሰፈሰፍ ልጁን ለመከላከል ሲሞክር በተንቀሳቃሽ ፊልሙ ይታያል .. ብዙም ሳይቆይ ግን አባትና ልጅ የአነጣጣሪው ወታደር የጥይት ራት ሆኑ ፣ በዚያ ፍልስጥኤማዊ አባትና በብላቴናው መሀመድ ላይ የሆነው ፈጽሞ አይረሳኝም ። በህይዎቴ ውስጥ ከባድ ለውጥ ካመጡት ምዕሎች ውስጥ መካከል ይህኛው ይጠቀሳል …
eskinderናፍቆት እስክንድር …

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በሸብርተኝነት ተከሰው ባሉበት ናፍቆት እስክንድር በወህኒ ተወለደ ፣ አደገ ። ብዙም ሳይቆይ “በይቅርታ ምህረት ” ከአመት በኋላ ተፈታ ። ጋዜጠኛ እስክንድር ኢትዮጵያየ ብሎ መጻፉን ቀጠለ ፣ ህሳቤ ፣ አመለካከት የሃገር ህልሙን ማሰር የማይችሉት እስክንድርን ሲያጠምዱና ሲይዙ ልጁ ናፍቆትን ከት/ቤት ሲመልስ እንደነበር ሰምተናል። በመንገድ ዳር አስቆመው እስክንድርን ልጁን ናፍቆትን መንጭቀው ሲለያዩዋቸው ናፍቆት ” ከአባቴ አትለዩኝ !” ብሎ ተንሰቅስቆ ያለቅስ እንደነበር የሚያሳይ ፎቶ ባናይም ድርጊቱን ሲሰሙት ዘልቆ ያማል። ዛሬ ናፍቆትና እናቱ ሃገራቸው እልተመቻቸውምና ተሰደዋል …

ከጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች …

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ቤተሰቦች በተለይም እህቷ እስከዳር አለሙ በህገ መንግስት የተደነገገ የእስረኛ መብቷ ተገፎ ውዷንና አብሮ አደግ እህቷን ከማየት መከልከላሏን ሰምቻለሁ ። ጋዜጠኛ ተመስገንን በህገ መንግስት የተደነገገ የእስረኛ መብቱ ተፈፎ ለ40 ቀናት በዘመደ አዝማድ ፣ በሃይማኖት አባትና በሃኪም እንዳይጠየቅ የተደረገበትን ሁኔታ ተመልክተን አዝነናል ። የተመስገን እናት እንባ ፣ ምግብ ሊያቀብል ሄዶ ድንደባ የደረሰበት ወንድም የመብት ገፈፋ ተጠቃሸ ነው ።
በመሰዊያው ላይ ያሉት …

የጸሃፍቱ ፣ፖለቲከኞቹና አማኞቹ ቤተሰቦች

ኑሯቸው ወህኒ ለማድረግ የተገደዱት ፖለቲከኛው የአብዷለም ፣ የሃብታሙና የየሽዋስ አሰፋ ፣ የእስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፣ ጸሃፊ ሃያሲው አብርሃም ደስታ ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና በስም ያልጠቀስኳቸው ሁሉም “ወንጀላችን በህገ መንግስቱ የተሰጠንን መብት ተጠቅመን ፣ እምነታችን ባራመድን ፣ ለሃገራችን ያለንን ህልም በመናገር በመጻፋችን ነው ” ሲሉ ፍትህን አጥብቀው ይጠይቃሉ። በሰላማዊው ተቃውሞ መስመር እንጅ ጦር ሰብቀው የማናውቃቸው በመሰዊያው ላይ ያሉት ወንደም እህቶች ሁሉ ቤተሰቦች ህመም ዘልቆ ቢያምም የመሰዊያው ያቃጠላቸው ልጆቻቸው እየደረሰ ያለው ያህል የሚያም ነገር የለም ፣ ሊሰሙት ሊያዩም ይከብዳል !

እናም ” አንድነት ዘመነ ነው !” ስሙ ያሉኝ ብላቴና የአባት ስስት ፣ ጭንቅ አሳምሮ የሚያሳየው ተናጋሪ ፎቶ ነፍሴን ጨምድዷት ለህመሜ ማስታገሻ ብዕር አንስቸ ስንኝ ስቋጥር ልቤ እየደማ ነበር ።
አይዞህ ወንድም አለም !:

የብላቴናው አባት ታሳሪ ማነው ?

ይህንን ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ምላሽ የሰጠኝ አንደ ወዳጀ ስለታሳሪው ሃገር ወዳድ ፖለቲከኛ እንዲህ ብሎኛል … “ዘመነ ምህረት በምርጫ ቦርድ የፈርሠው መኢአድ ሠሜን ቀጠና ሃላፊ እና በማክሠኝት 2ኛ ደረጃ ት.ቤት መምህር ነበር:: ምርጫ ቦርድ ድርጅቱን ለነ አበበው መሐሪ ሊሠጥ ጥቂት ቀናት ሢቀሩት ጎንደር ጥምቀት ላይ ችግር ልትፈጥሩ ነበር ተብለው የጥምቀት እለት በደህንነት ተይዞ ከዚያን ጊዜ ጃምሮ በማእከላዊ ይገኛል:: አሁን ላይ የሽብርተኛ ክሥ ተመሥርቶበት ቤተሠቦቹ ልጁን ይዘውት መጥተው ነው:: ልጁንያመጡት የዘመነ አባት አቶ ምህረት እና ባለቤቱ ናቸው:: ሌላው አሣዛኙ ነገር ግን ይህ ልጅ ከአሁን በሁዋላ ችግር ለይ መወደቁ.ነው ንክንያቱም የዘመነ ቤተሠቦች የሚተዳደሩት በዘመን ደመወዝ ነበር:: ለቤተሠቦቹ ገቢ ማሠባሠብ ካልተቻለ ሌላው ቀርቶ ይህ ህጻን ጎዳና ላይ ላለመውደቁ ዋሥትንና የለም። ዘመነ ቆራጥ ታጋይ መሆኑን ለማወቅ ልጁን ለምን አንድነት ብሎ እንደሠየመው ማወቅ ብቻ በቂ ነው:: ” ይላል ስለ መምህር ዘመነ ምህረትና ስለ ብላቴናው ልጁ አንድነት ዘመነ መረጃ ታቀበለኝ ወዳጀ …

ኢትዮጵያን ብለው የግንባር ስጋ የሚሆኑትና የሆኑት ወገኖች አስታወስኩና በደላቸው አልያዝህ ቢለኝ ከእነሱ አልፎ በወላጅ እናት አባት ፣ በእህት ወንድም በልጆች ፣ በዘመድ አዝማድና በጓደኞች የሚደርሰው ፈተና ዘለቆ ቢሰማኝ ” ዛሬዋ ኢትዮጵያችን እንዲህ ናት !” ነገ የመንጋቱን ተስፋ ላጽናና በሚል በውል ለማይሰማኝ ብላቴና አንድነት ጭንቅ መታሰቢያ ይዞህ ወንድም አለም ስል ይህችንም ወግ ግጥሟንም ቆጣጠርኩ …!
እስኪ ቸር ያሰማን !

መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓም

posted by Daniel tesfaye

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: