መልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
October 23.2014
‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር፡፡ ባለፈው ሳምንት የ‹‹ባንዲራ ቀን›› በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር፡፡
‹‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ጥሩ ሰው ሆኖ ከእስር ይወጣል፡፡ ተመስገን የህዝብ ልጅ ነው፡፡ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ፡፡ እስሩ ስለሀገሩ ያበረታዋል፤ ያጠነክረዋል፡፡ ብዙ ነገር እንዲረዳ ያደርገዋል፡፡ ሰዎች ይታሰሩ እያልኩ አይደለም፡፡ ይሄ አንዱ የሰላማዊ ትግል መስራት ውጤት ነው፡፡ በለውጥ እና በትግል መስመር ላይ ያሉ ኢትዮጵኖች መታሰራቸው ነገ ለውጥ ያመጣል፡፡››
እኔም ዛሬ ‹‹የሀገሪቱን ህዝቦች አንድነት እንዲፈርስ እና በሀገሪቱ ሕዝቦች መካከል ጸብና ቁርሾ እንዲፈጠር በማሰብ …›› የሚል ከባድ ክስ ብቀበልም የእስክንድርን መልዕክት ለማስተላለፍ አልተቆጠብኩም፡፡