FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

ወያኔ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም ::

1f2f5-248120_174211019409100_1213907092_n
Oktober 8/2013
ከገዛኽኝ አበበ

ሀገር ማለት የተለያዩ ብሄሮች ፣ የተለያዪ ጓሳዎች እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሎቸው ሰዎች መኖሪያ ናት :: እኛም ሀገራችን ብለን የምንጠራት ሀገራችን ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ያላት የተለያዩ ህዝቦች መኖሪያ ሀገር ስትሆን ሕዝቦቾም ለዘመናት በፍቅር፣ በመተሳሳብ ፣ በመከባባር እና በመተባባር አብሮ ሲኖር የነበሩ ህዝቦች እንደነበሩ ከታሪክ መረዳድ እንችላላን::ይችን ሀገራችንን ኢትዮጵያን በተለያዩ ጊዜና ዘመናትም የተለያዩ መንግስታቶች ለዘመናት በመፈራረቅ መርተዋታል መንግስታቶችም የኢትዮጵያን አንድነት እና ሎአላዊነትን ጠብቀው ህዝቡም ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ እና አስከብሮ እንዲኖር የበኩላቸውን አስተዋጹ አብርክተው አልፈዋል:: ጀግኖች አባቶቻችንም የኢትዮጵያ ሕዝብም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ ደማቸውን አፍስሰዋል፣ አጥንታቸውን ከስክሰዋል ፣ ህይወታቸውንም መሰዋት አድርገው አሳልፈው ሰተዋል :: ምክንያቱም ኢትዮጵያውነት ኩራት ኢትዮጵያውነት ፍቅር ኢትዮጵያውነት አንድነት መሆኑን ከመሪያቸው ተምረውታልና::

መሪው የኢህአዴግ ወያኔ መንግስትም ወደ ስልጣን ብቅ ካለበት ቀን ጀምሮ ሀገርን በመሸጥ ፣ በመገንጠል እና ሕዝብንም በዘር፣በብሔር፣ በጓሳ እና በቋንቋ በመከፋፈል ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት ርኩስ ተግባሩን እየገፋ ባለበት በእነዚህ አስርት አመታት ውስጥ ግን ኢትዮጵያውነት ኩራት መሆኑ ቀርቶ ውርደድ፣ ስደት መከራ እና ስቃይ መሆኑ እየጨመረ መጥቶል::

በእነዚህ አመታቶች ኢትዮጵያውነት የሀገር ስሜትና ወኔ ከህዝብ ዘንድ የጠፋበት እና ሕዝቡም እንደ ዜጋ መኖር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ::በእነዚህ አመታቶች ውስጥ ለሕዝቡና ለኢትዮጲያዊነት ግድ በሌለው በዚህ ሰይጣናዊ እና አረመናዊ አገዛዝ ስር ብዙዎች ታስረዋል፣ ተገለዋል፣ ወላዱች እንዳይወልዱ መካን ተደርገዋል ሕዝቦች ቄያቸውን መሬታቸውንና ሀብት ንብረታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለስደት እና ለመከራ ተዳርገዋል፣እናቶች ልጆቻቸው በግፍ ተገሎባቸዋል ይህ ነው የማይባል ብዙ ብዙ ግፍ በሕዝብ ላይ ተፈጽሞል :: ከእለት ወደ እለትም ሕዝባችን መኖር በማይችልበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል:: ዘሬ በየቤቱ በዚህ ጨቋኝ ስርዓት የማይማርር የለም:: የሕዝብም የመኖር ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ነው :: የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ለሕዝብ ምንም የጠቀመው ነገር የለም:: ይልቁንስ በሀገር ሀብት እና ንብረት በማን አለብኝነት እንደፈለጋቸው ሲፈነጥዙ ኖረዋል አሁንም እየኖሩ ይገኛሉ::

መንግስታት ሀገርን ሊያስተዳድሩ እና ሊመሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የሀገርን ሉአላዊነትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር ነበር በተቃራኔው ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝቦቾም ለዚህ ባለመታደል መብታቸውን እና ነጻነታቸውን ለመስከበር እንደ ሰው መኖር በሚችሉበት ሁኔታ በነጻነት ለመኖር በመፈለግ በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕዝቦች ሀገራቸውን በመልቀቅ ወደተለያዩ ሀገሮች ለስደት ይዳረጋሉ :: በብዛት ወደየ ሃረብ ሀገሩ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ለተለያየ እንግልት መከራ እና ስቃይ እንዲሁም ለሞት የሚዳረጉ ሲሆን በየቀኑ የብዙዎቹ ህይወት እንደዋዛ ያልፋል::

ነገር ግን ሕዝባችን በየቦታው እና በየአረብ ሀገሩ አሰቃቄ ድብደባ ግፍ እና ግድያ ሲፈጸምበት ሀገርን እየመራው ነው ሕዝብንም እያስተዳደርኩኝ ነው የሚለው የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት አንድም ቀን የዚህ ሕዝብ መከራ እና ችግር ግርፋት እና ሰቃይ ሞቱ ግድ ሲለው እና ለሕዝቡ አለኝታነቱ ሲቆም አይተን አናውቅም::ስለዚህ የኢህአዲግ መንግስት ለኢትዮጵያም ለኢትትዮጵያ ሕዝብም እስከ አሁንም ምንም የጠቀመው ነገር የለም አሁንም ወደፊትም አይጠቅምም :: ለሀገር እና ለሕዝብ ጥቅም ቆሚያለው የሚል መንግስት የሀገርን ሉአላዊነት ሲያስከብር የሕዝብን ደህንነት እና ጥቅም ሲያስከብር ብቻ ነው::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖር

posted by Daniel tesfaye

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: