FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

የወገን ያለህ! (Facebook)

September 9, 2013

ግርማ አየለ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አካባቢ ነው፡፡ ከሰላም ቴክኒክና ሙያ ኮልጅ እንዲሁም ከተግባረ ዕድ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በጀነራል ሜካኒክስ በዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ ሲንቴክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር (SINTEC ETHIOPIA PLC) በተባለው ድርጅት ውስጥ በቋሚ ሰራተኛነት ለአንድ ዓመት ከአስራ አንድ ወር ያህል በቴክኒሻንነት አገልግሏል፡፡Girma Ayela

ግርማ ዛሬ ላለበት አሳዛኝ ህይወቱ መነሻ የሆነችውን ቀን ወደ ኋላ በማስታወስ ሲናገር አይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡ ጥቅምት 2 ቀን 2003 ዓ.ምን ‘በወጣትነት ጉልበቴ ሰርቼ እራሴንም ቤተሰቦቼንም እለውጣለሁ የሚለው ህልሜ የጨለመበት ቀን ነው’ ብሎ ይገልጸዋል፡፡

በሲንቴክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ውስጥ በቴክኒሻንነት ሲያገለግል የቆየው ግርማ አየለ እና ሌሎች ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ከሙያቸው ውጪ የሆነ አንድ የስራ ግዴታ ተጣለባቸው፡፡ ‘የማላውቀውንና ልምዱም የሌለኝን ስራ አልሰራም የሚል ምላሽ በወቅቱ ብሰጥም ተቀባይነት አላገኘሁም’ የሚለው ግርማ የእንጀራ ነገር ነውና ስራው ወደሚከናወንበት ቦታ ከባልደረቦቹ ጋር አመራ፡፡ እንዲያከናውኑት የታዘዙት ስራ ደግሞ ድርጅቱ ከሸገር ሬድዮ ጣቢያ ጋር በተዋዋለው መሰረት የጣቢያውን ማሰራጫ ታወር መትከል ነበር፡፡

ግርማና ሁለቱ የስራ ባልደረቦቹ አዲስ አበባ ድልበር ተብሎ በሚጠራውና በጎጃም በር መውጫ በኩል በሚገኘው የመትከያ ቦታ ተገኝተው ስራውን ጀመሩ፡፡ አሁን ግርማና ሁለቱ የስራ ባልደረቦቹ የተከላ ስራው እየተከናወነ ባለው ታወር ከመሬት 65 ሜትር ከፍ ብለው እየሰሩ ነው፡፡ ድንገት የተሸከማቸው ብረት ተሰበረ፡፡ ሶስቱም እየተምዘገዘጉ ወርደው ከመሬት ተላተሙ፡፡ አንደኛው ወዲያውኑ ህይወቱ አለፈች፡፡ ሁለተኛው ሆስፒታል ቢደርስም የደረሰበት ጉዳት ህይወቱን ከአንድ ሳምንት በላይ የሚያስቀጥላት አልነበረምና አለፈ፡፡ በተዓምር የተረፈው ግርማ ብቻ ነበር፡፡

ግርማ ‘ለአደጋው መከሰት የብረቱ የጥራት ችግርና የሽቦ መወጠሪያዎቹ ማጠር ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው’ ይላል፡፡ አያይዞም ‘ለመከራከሪያነት እንዳይሆነን እንኳ እቃውን የት እንዳደረሱት አላውቅም’ ሲል ይገልጻል፡፡ ዛሬ ግርማ በኮሪያን ሆስፒታል ውስጥ ከ2 ዓመት ከ10 ወራት በላይ በተኛበት አልጋ ላይ አሁንም ይገኛል፡፡ የተደረገለት ህክምናም የአካል ጉዳቱን ሊጠግንለት ቀርቶ እስከ ዛሬ ድረስም ቁስሉ አልዳነለትም፡፡ ህግ የሚለውን አላውቅም፡፡

በህጉ በኩልም የሄደባቸውንም ሆነ የተሰጠውን ውሳኔ በዝርዝር አላውቅም፡፡ ይህንንም በዝርዝር የማወቅ ፍላጎቱም የለኝም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የወገን ጉዳት የኔም ጉዳት ነው የሚሉ፤ የሰብዓዊነት ስሜት ያላቸው የህግ ባለሙያዎች ቢያነጋግሩት ደስ ይለኛል፡፡ ደግሞም ነግ በኔ የሚለውን የሀገራችንን ብሂል ማስታወስ የሚገባ ይመስለኛል፡፡ ልጠይቀው በተኛበት ክፍል ውስጥ በተገኘሁበት ወቅት ግን እዚህ ሆስፒታል ከገባ በኋላ የሆነውን ሁሉ እንዲህ አጫውቶኛል፡፡

‘‘አደጋው እንደደረሰ ከጥቁር አንበሳ ሪፈር ተብሎ ቀጥታ ወደ ኮሪያን ሆስፒታል መጣን፡፡ እዚህም ስብራት ብቻ ስለሆነ ችግር የለውምና የነርቭ ችግር ካለ እናያለን ብለው ለአምስት ቀናት ያህል ያለ ምንም እርዳታ ቆየን፡፡ ከአምስት ቀን በኋላ ኤምአርአይ እንድነሳ ተደርጎ የነርቭ ችግር እንዳለ ታወቀ፡፡ ስብራቱን ግን የሰሩልኝ በአስራ ስምንተኛው ቀን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ አስራ አራት ጊዜ ኦፕሬሽን ተደርጌአለሁ፡፡ ሰውነቴ ክፉኛ ቆሳሰለ፡፡

እስከዚህ ጊዜ ድረስ ማለትም ለአመት ከሰባት ወር ያህል ድርጅቱ የህክምና ወጪውን ይከፍል ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ አቅም የለኝም ብሎ ለሆስፒታሉ ማመልከቻ አስገባ፡፡ ቀጣይ ህክምና እንደሚያስፈልገኝ ለድርጅቱ ቢገለጽለትም እስካሁን በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ ተገቢ የሆነ ህክምና አልተደረገለትም የሚል መከራከሪያ ነጥብ አቀረበ፡፡ እንጊዲያውስ ሆስፒታል ልትቀይሩልኝ ይገባል ብዬ ብጠይቅም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ህግም አያስገድደንም የሚል ምላሽም ሰጡኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ኮሪያን ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት የሰጠሁበት ሂሳብ ይከፈለኝ በማለት ወደ ክስ ሄደ፡፡ እስከ አሁንም ሁለቱ ድርጅቶች በክስ ሂደት ውስጥ ናቸው፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነርሶች ቁስሌን ይጠርጉልኛል እንጂ ምንም የህክምና እርዳታ እየተደረገልኝ አይደለም፡፡ ፊዚዮቴራፒ ያስፈልገኛል፣ የዶክተር ክትትልም ያስፈልገኛል፤ ሁለቱንም ከልክለውኛል፡፡ ሆኖም ግን ነርሶቹ በግል ለሚያሳዩኝ ፍቅርና ትህትና ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ የኢንሹራንስ ካሳዬን ብጠይቅም ሆስፒታሉን ለቀህ ካልወጣህ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እንደ ተሸከርካሪ ወንበርና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን አሟሉልኝ ብልም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ አማራጭ ስለሌለኝ እስከ ዛሬ እዚሁ አለሁ፡፡

አሁን ከወገቤ በታች መንቀሳቀስ አልችልም፡፡ ምንም ህክምና ስለማይደረግልኝ ቁስሌ ይሸታል፡፡ ፈሳሹ እየጨመረ ሄዷል፡፡ ህክምና ማግኘት እንዳለብኝ ሆስፒታሉ ያምናል፡፡ ነገር ግን ገንዘብ ካልተከፈለኝ አላክምም ነው ያለው፡፡ ከገንዘብ በፊት ግን ምንጊዜም ቢሆን የሰው ህይወት መቅደም ያለበት ይመስለኛል፡፡

ኮርያን ሆስፒታል ክርስቲያናዊ የህክምና ማዕከል እንደመሆኑ መጠንና ከቆመለት ሰብዓዊና ሞራላዊ የበጎ አድራጎት ስራ አንጻር ተገቢውን ህክምናና ትብብር ሊያደርግልኝ ይገባ ነበር፡፡ ይሁንና ሆስፒታሉ ራሱ ሙያዊ ስህተት ፈጽሞብኛል፡፡ በኦፕሬሽን ወቅት ለፈሳሽ ማውጫ በሚል ምክንያት ውስጥ የቀረው ጓንት ጓንት ለ11 ቀናት ያህል ስለቆየ ስጋዬን አበሰበሰው፡፡ ቁስሌ እስከዛሬ ሊድን ያልቻለበት ምክንያትም ይሄ ነው፡፡

ዛሬ በዚህ እድሜዬ በበላሁበት አልጋ ላይ ስጸዳዳ የወጣትነት ህልሜ እንዲህ መና ሲቀር ሳይ ከባድ የሞራል ድቀት ይሰማኛል፡፡ እንደ ዜጋ የሚረዳኝ ሰው እፈልጋለሁ፡፡ የደረሰብኝን ሁሉ ህዝብ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ፡፡ በራሴ ልታከም የምችልበት አቅምም የለኝም፡፡ አባቴ ጡረተኛ ነው፤ እናቴ በህይወት የለችም፡፡ የሚረዳኝ የለም፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች ሲካሰሱ እኔ ግን በመሃል ቤት እየማቀቅኩ ነውና የወገን ያለህ እላለሁ፡፡ <a href="http://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/Amharic

posted by Daniel tesfaye

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: