FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል 7)

timthumb

September 8, 2013
ናደዉ ከዋሽንግተን ዲሲ
ሣይንስና ቴክኒዮሎጂ በደረሱበት ደረጃ አንፃር በልዩ ልዩ የሞያ መስክ ስልጠና ተወስዶ አገርንና ወገንን መርዳት የተለመደ ተግባር ነዉ ።በዚህም ምክንያት የልምድ ሰራተኞች ቦታቸዉን በዘመናዊዉ መስክ ለሰለጠኑት ባለሞያዎች መልቀቅ ግድ ይላል። በአንዳንድ ባላደጉ አገሮች የሰለጠነ የሰዉ ሀይል እጥረት ምክንያት በልምድ ባለሞያዎች ቦታዎች እንዲሸፈኑ ይደረጋል፧ዛሬም። ታዲያ ይህ አካሄድ ሕብረተሰቡን እንደጥንቱ ሁሉ ዛሬም እየጎዳዉ ነዉ። የልምድ አዋላጆችን ጨምሮ ግርዛትና ሌሎችን በየደረጃዉ መጥቀስ ይቻላል፥እና ለማለት የተፈለገዉ ችግር ካልሆነ በስተቀር በአሁኑ ወቅት አጉል ነዉ አንዳንድ ግዜም በሕግ ያስቀጣል፣በተለይም ደግሞ በአደጉ አገሮች ይህ ሁኔታ ሲፈፀም ወንጀሉን ከባድ ያደርገዋል። ይህን እዉነት ካልኩ በኋላ ወደጋራ ጉዳያችን ላምራ ወደኛዉ ወደዳያስፖራዉ ፈተና ልበለዉ ችግር። በተለይ ወደ ኢትዮጵያዊዉ ዳያስፖራ ስንመለከት ብዙዎቻችን ወደዚህ አመጣጣችን መንገዱ ብዙ ነዉ አናኗራችን የዕዉቀት ደረጃችንና ልምዳችን ለየቅል ነዉ። በዚያ ላይ የባእድ አገሩ የንሮ ዉጣዉረድ ሲታከልበት ሕይወትን ዉስብስብ ያደርገዋል። አንዳንዶች ሁኔታዉን መቋቋም ባለመቻላቸዉ ራሳቸዉን ሲያጠፉ እናያለን አለያም የአደገኛ ሱስ ተጠቂ ሆነዉ ይቀራሉ:: አንዳንድ ብልጣብልጥ ወስላቶች ደግሞ በአፍቅሮተ ነዋይ ይጠመዱና ወገኖቻቸዉን ሲበድሉ ይስተዋላል። ካለሞያቸዉ ገብተዉ ሲዳክሩ ደግሞ አደጋዉን የከፋ ያደርገዋል እንደልምድ አዋላጆቹ ስህተት የሰዉ ህይወት ያበላሻሉ ፧

የሰዉ ህሊናን ይሰልባሉ፧የዳያስፖራውን አንድነት ፈተና ዉስጥ ይከቱታል የሙያዉ ስነምግባር ethics ስለሌላቸዉ ለሙያዉ ክብር ያሳጡታል ባለሙያዎችንም አንገት ያስደፋሉ ። በተለይ በሚዲያዉ አለም ሲሰነቀሩ አደጋዉ የትየለሌ ነዉ። ባለፉት 6 ተከታታይ ፅሁፎቼ ላይ በስም የጠቀስኩት የወያኔ ተላላኪ ምርጫዉ ስንሻዉን አይነት ስርአተአልበኛ ግለሰቦች ለሞያዉ ክብር ስለሌላቸዉ አደገኝነታቸዉ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ሕብረተሰቡ ማንነታቸዉን አስኪረዳ ድረስ ብዙ ጥፋት ያደርሳሉ። ይሉኝታም አልፈጠረባቸዉምና ገንዘብ እስካስገኘላቸዉ ድረስ ሁሉንም ያደርጋሉ። አንድ ጠንካራ የወያኔ ተቃዋሚማ ካገኙ ስም ለማጉደፍ በነሱ ቋንቋ ጥላሸት ለመቀባት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፧አለቆቻቸዉ ምነዉ አንቀላፋችሁ?!ስለሚሏቸዉ የተቃዋሚ ተቃዋሚዎችን አሉባልታ ለዚህ እኩይ ከፋፋይ ተልእኮዋቸዉ ይጠቀሙበታል።

አንዳንድ ከተቃዋሚ ድርጅቶች በግል ባሕርያቸዉና cheep popularity ርካሽ ተወዳጅነት ናፋቂ ግለሰቦችን ይጠቀሙባቸዋል።ለዚህ አይነቱ በሽታ ግንባር ቀደም ምሳሌ የሆነዉ ይኸዉ የወያኔ ግብረበላ ም/መ/አለቃ በትናቸዉ ስንሻዉ ነዉ። የዚህ ተላላኪ እንቅፋትነትና ከፋፋይ እኩይ ተልእኰዉ ይቀጥላል የራሱ ራዲዮ ዝግጅት አማካሪዎች አንዳንድ ጥቆማዎችን በቁጥር 6 ላይ በተዉኩት የ e-mail አድራሻዪ ልከዉልኛል። ጥቂቶቹን ርእሰ ጉዳዮች በጥቂቱ እነሆ ፧ በተያዘለት ቀጠሮ በሚቀጥሉት ፕሮግራሞቹ የሚያቅራራዉ በቅርቡ እዚህ ዳያስፓራ በተቋቋመዉ በሽግግር ምክር ቤት ዙርያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ስለዚህ ሕዝባዊ ድርጅት አመሰራረት፧ መስራችና ሰብሳቢ ስለነበረዉ ስለ ዶ/ር ፍሰሐ እሸቱ ጠቅላላ ሁኔታና ከበትናቸዉ ስንሻዉ ጋር ስለተፈጠረዉ አዲስ ወዳጅነት እንዲሁም በጋራ ስላቋቋሙት NGO ንግድ ግንኙነትና በዚህ ሰበብ ሊሰራ ስለታቀደዉ ገንዘብ በቂ መረጃ በእጁ ስለገባ ጊዜዉ ሲደርስ በዚሁ ድህረ ገፅ ለአንባቢ ይፋ ያደርገዋል።

በመግቢያየ ላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በልምድ አዋላጅ ስህተት ብዙ ህይወት ያጠፋል የልምድ ጋዜጠኛም እንዲሁ፧ በተለይ የጥፋት መልእክተኝነት ሲታከልበት የሚያደርሰዉ አደጋ ከባድ ነዉ።ህሊና ያቆስላል፧ እርግጥ ነዉ እዚህ ዳያስፖራ ደግሞ ቀላል ነዉ የልምድ ጋዜጠኛ መሆን ፧በቃ የአየር ሰአት መግዛት ከተቻለ ሁሉም ይቻላል፧ አየር ላይ ሆኖ እንደፈለጉት መሆን አየር ሰአት ገዢዉ የልምድ ጋዜጠኛ የፈለገዉን ይክባል የፈለገዉን ያዋርዳል፤አየር ላይ ወጥቶ ትፋቱን ይለቀዋል ፧ የፈረደበት ዳያስፖራ መዋጮ ፈንድ ሬዚንግ ምናምን ይባላል ይሰጣል። እግሩ እስኪንቀጠቀጥ ወገቡ እስኪጎብጥ ደክሞ ካገኘዉ ገንዘብ ቆርሶ ይመፀዉታል መልሶ መፅዋቾቹን ይሰድባቸዋል ወይም ከፋፋይ አንድነት በታኝ ቱማታዉን ያስደምጣቸዋል፧ጓደኞቹም በተመሳሳይ ይህንኑ አስነዋሪ ስነምግባር እንደሞዴል ይጠቀሙበታል። የልምድ አዋላጆቹ እንጥል ቆራጮቹ እነ ሰለሞን ተካልኝ ፧እነ ዮሴፍ ግዛቸዉ ፧ንጉሴ ወ/ማርያም ፧ወንድወስን ፧ ሌሎችም አዳዲስ ተቀፍቅፈዋል የደም ገንዘብ ቀላዋጮች፧ በተለይማ በትናቸዉ ስንሻዉ በዚህ ሞያዊ የልምድ አዋላጅ አይነት ጋዜጠኛነት ርካሽ ተግባሩን ተክኖበታል፧ቀልዶበታል ፧ዶልቶበታል ፧በሚያገኘዉ የቅልዉጥ ገንዘብ ሕንፃ ገንብቶበታል፧ስንቱን የአንድነት ታጋይ ከጨዋታ ዉጭ አድርጎበታል ።ይህ ተላላኪ ትናንት በኰሎኔል ጎሹ ወልዴ ይመራ የነበረዉን መድህን ፓርቲን ፧የኢንጅነር ሀይሉንና የዶክተር ታየ ወ/ማያትን ቅንጅት ፧ቀጠለና ኢሕአፓንና የሽግግር ምክር ቤትን ፧ እንዳበደ ዉሻ አየነከሰና እየለከፈ ይገኛል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የወያኔን ኢምባሲ መሽሩፍ ሊቀበል ገባ ወጣ ሲል ከርቀት በባለሞያዎች ፎቶ ካሜራ ተቀረፀ ፧ምስሉ በኢሜይል አድራሻዬ ከች አለ ቤሮየ ድረስ ፧ወደፊት ጊዜዉ ሲደርስ በእጄ ከገቡት ጠንከር ያሉ ማስረጃዎች ጋር ይፋ ይሆናሉ። እንደትግል ጓዶቹ እንደነ ልደቱ አያሌዉ፧የአዉራምባዉ ዳዊት ከበደ፧ንጉሴ ወልደማርያም፧ ሰለሞን ተካልኝ፧ዮሴፍ ግዛቸዉ፧ጫማ ስመዉ ዉለታ ፈርመዉ አገር በመሸጥ የደም ገንዘብ ከአዲስ አበባዉ ዋናዉ ቱጃር ይመፀወታል አይዞህ ለከርስህ አታስብ በኔ ይሁንብህ ይባላል ፧! እና ምን ቸገረዉ ቀፈቱ ከሞላ አገሪቱ ብትንትኗ ቢወጣ ።ከመጣዉ ጋር ሁሉ አዲስ ዘፈን መዝፈን ይችልበታል ከደርግ፧ አሁን ደግሞ ከወያኔ ነገ ደግሞ ከሚመጣዉ ጋር ሁሉ፧ማፈሪያ ተላላኪ። ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ነዉ! መባሉ እዉነት ነዉ ይህን ሕዝባዊ ተቋም የወያኔ ሆድ አደር ተላላኪዎች ፈትሸዉታል ፕሮፌሽናል ያልሆኑ የግል ዝና ናፋቂ ጮርቃ የልምድ አዋላጅ አይነት ጋዜጠኞችም ሰልለዉታል ግን አልሆነላቸዉም:: የአዉራምባዉ የትግራይ ጉጅሌ ዳዊት ከበደና እነ እንትና ጥፉ ተብለዉ ጭራቸዉን ቆልፈዉ ወጥተዋል፧ሲተፉ ደግሞ በመንደር ራዲዮኖችና ድህረገፆች ላይ እየወጡ ሲያላዝኑ ይታያሉ የተከበራችሁ ኢሳቶች ይህ ተቋም የኢትዮጵያ ሕዝብ ልሳን ነዉና ለሆድ አደር የወያኔ ተላላኪዎችና የልምድ አዋላጅ አይነት ጋዜጠኞች በራችሁን ገርበብ አርጉት እንዲያዉም ዝጉባቸዉ!!አራት ነጥብ። ክፍል8 ይቀጥላል ናደዉ ዋሽንግተን ዲሲ የተከበራችሁ አምባቢዎቼ ስለላካችሁልኝ

መረጃዎች እጅግ አመሰግናለሁ!

kifleleta11@gmail.com

posted by Daniel tesfaye

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: