FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል ፮)

timthumb
September 2, 2013
ናደዉ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ
በጨዋታችን መሐል አንድ አባት እንቅርትም ያገለግላል አሉ። የተናገሩት ምሳሌያዊ አነጋገር ስላልገባኝ አባባሉን እንዲያስረዱኝ መጠየቄ አልቀረም ፧እሳቸዉም ፈገግ ብለዉ ሰማህ ልጄ ፧በድሮ ግዜ የሆነ ነገር ነዉ ፦ባል ሚስቱ በጣም ታበሳጨዉና ስለት ይዞ መሬት ላይ ይጥላትና አንገትዋን ይቆጣትና ገደልኩ ብሎ አገር ጥሎ ይጠፋል፧የቆረጠዉ አንገትዋን ሳይሆን እንቅርቷን ኖሮ ሴትየዋ ከሞት ትድናለች። ይቺ ሴት እንቅርት ባይኖራት ኖሮ ሞተችም አልነበር ?!አሉና በመቀጠል አንተም የዚህን የወያኔ ግብረበላ ተላላኪ ሃጢያት ማስረጃዎች በማኖርህም አይደል ዛሬ ለማጋለጥ የረዳህ ብለዉ እኔንም ፈገግ አሰኙኝ ። የወያኔዉ ጉጅሌ ተላላኪ ምርጫዉ ስንሻዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ሁለት የተቃዋሚ ርድርጅት አመራር አባላትን እንደጀሀዳዊ ሃራካት የወያኔ ድራማ ከየስርቻዉ እየሰበሰበ ያጠራቀማቸዉን ንግግሮች ቆራርጦ በመቀጣጠል የሚያቀርባቸዉን የሚያቅሸልሹ አሉባልታዎችና የአኩራፊ ቃለምልልስና በጥላቻ የተደራረቱ ተራ ዘለፋዎቹን የተከታተለዉ ጓደኛዬ፧ይህ ሰዉ የወያኔ ጭፍን ተላላኪ መሆኑን እዉነት ነዉ። ወስላቶች።በነገራችን ላይ በራስ ዓሊ ጊዜ የደነቆረ በራስ ዓሊ ይምላል እንዲሉ ጋሻው ካሴ የሚባል ሞፈሩን አስቀምጦ አዲስ አበባ የገባ ፣ ወያኔ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ወቅት የአ.አ. ዩ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝደንት ስልነበርኩ “ታላቅ ታጋይ ነኝ ፤ አንቱ በሉኝ በሚል የከንቱዎች ፈሊጥ ያለአቅሙ ራሱን የቆለለ ግለሰብ በፍርሻው ስንሻው ሬድዮ ከቀረቡት አንዱ ነው። ይህ ግለሰብ፣ በኬንያ ተስዶ እያለ አብረውት ለተሰደዱት ተማሪዎች የሚላክውን ገንዝብ ብቻውን ሲያጠፋ የነበረ፣ ወስላታና ግብዝ ግለስብ ማንነት ኬንያ በስደት በስደት የነበርን እናውቃለን።

የሆነ ሆኖ በትናቸው ስንሻውም ሆነ እንደ ጋሻው ካሴ አይነት መሸ በከንቱዎች አሁን ወያኔ አየፈፀመ ካለው ጸረ ህዝብና ጸረ አገር ተግባራት አኳያ የአንድነት ሀይሉን ማስተባበር ሲገባ ፧ተቃዋሚ መሪዎች ላይ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ምን ይባላል ?! አለ ጓደኛዬ ለብዙ አመታት የሱ ራዲዮ ጣቢያ ደቀመዝሙር የነበረዉ፧ ዛሬ ግን እንደኢሠፓዋ ባለቤቴ ለሱም እሱነቱ ተገለፀለት በሚገባ አነበበዉ በትናቸዉን እዉነትም በትናቸዉ አለ ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ይዞ !!ዛሬ ይህ ከሃዲ ባንዳ ከጥቂት ቀላዋጮች ጋር ሆኖ አጥፍቶ ሊጠፋ ሲንገዳገድ ሊጥልበት ያሰበዉ ቦታ ላይ ሳይደርስ የያዘዉ ፈንጂ እጁ ላይ ፈነዳበት ። በወያኔ በሚመፀወተዉ የመንደር ራዲዮኑ ላይ እንደሚያላዝነዉ፥ ዳያስፖራ ዉስጥ እገሌ ተብሎ የሚጠቀስ የተደራጀ የተቃዋሚ ፖርቲ የለም አገር አሳልፎ ለጠላት የሚሸጥ ተቀጣሪ ብቻ ነዉ ። እኔ የማቋቍመዉን ፖርቲ ተቀላቀሉ ብሎ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከከፈተዉ ቤተክርስቲያን አባል ከሆኑ ከአንዲት ባልቴት ሰማሁ። በቅንጅት መሪዎች እስር ማግስት አቋቍሜአለሁ ብሎ ያወጀዉና ሰዉም አይንህን ላፈር ብሎ ስቆበት እሱም ትቶት የነበረዉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ንቅናቄ ብሎ ራሱ ብቻ በምናቡ የመሰረተዉን የኮሚኒስት ፓርቲ ከስምንት አመት በኋላ ከእንቅልፉ ሲነቃ ዛሬ ከጥቂት ተስፈንጣሪ ግለሰቦች ጋር የአዲስ ፓርቲ ምሥረታ ዘፈን ሊዘፍንልን ይዳዳል ይህ አጉራ ዘለል ካድሬ በቤተክርስቲያን ስም የሚያስገባዉ የሙዳየ ምፅዋት ገቢ ሲቀንስ በዚህ በኩል ሌላ የደም ገንዘብ ለመስራት ማሰቡ እዉነት ነዉ። ግን ይሳካለት ይሆን?! ወደፊት የምናየዉ ይሆናል፧የተላላኪዎችን ትያትር ማየት አይሰለቸን!!!

የትንቢተ ዳንኤል ምእራፍ ፮ ከቁጥር አሥራአንድ እስከ ሃያአራት፧መልእክቱ በአጭሩ እንዲህ ይላል ፦ ዳንኤል ለንጉስ ብልጣሶር የወርቅ ጣዖት አልሰግድም አለ፥ለእግዚአብሔር አምላኩ ብቻ ፀሎት በማድረሱም ምክንያት በቤተመንግሥቱ አካባቢ በሚገኙት ሆድ አደር ተላላኪዎች ተከሶ ንጉሡ ዘንድ ቀረበ ንጉሡም ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል አዘዘና ተጣለ ። እግዚአብሔር አምላክም የአንበሶችን አፍ ዘጋ ዳንኤልም በአንበሶች ሳይበላ ቀረ ንጉሡም የእግዚአብሔርን ተአምራት ተመለከተ አደነቀ የዳንኤልንም ከሳሾችና ሆድ አደር ተላላኪዎች አስጠርቶ በሱ ምትክ ቅጣቱ እንዲፈፀምባቸዉ አዘዘ ከነቤተሰቦቻቸዉም ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣሉ ፣ወደ ጉድጓዱ መጨረሻ እንኳ ሳይደርሱ አንበሶቹ ያዝዋቸዉ አጥንታቸዉንም ሁሉ ሰባበሩ ይላል ቅዱሱ መፅሐፍ።

አዎ!ነገም ለወያኔዉ አምባገነን አገዛዝ እድሜ ለማርዘም ለከርሳቸዉ ያደሩ የወያኔ ግብረበሎች ተመሳሳይ ሕዝባዊ ፍርድ ይጠብቃቸዋል ወደ አንበሶች ጉድጓድ ይጣላሉ ።ያ ቀን ሲመጣ ፧ለቅሶና ዋይታ መቆጨት ዋጋ አይኖራቸዉም ዛሬ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅሙት ወንጀል ነገ ትፋረዳቸዋለች፧ የነ ወጣት ሽብሬ ደም፧ የነ አሰፋ ማሩ ደም በቅንጅት ድጋፍ የተቃዉሞ ሰልፍ ምክንያት በጠራራ ፀሐይ የተጨፈጨፉት የመቶ ዘጠናሶስት ኢትዮጵያዉያኖች ደም በደኖ ገደል ከነሕይወታቸዉ የተወረወሩት ንፁሃን ደም በየመስጊዱ አንገታቸዉ እየተቀላ የሚገደሉት ሙስሊሞች ደም በዋልድባ ገዳም በጭካኔ የተጨፈጨፉት መናንያን ደም ጎጆዋቸዉ ዉስጥ ሆነዉ እሳት የተለኮሰባቸዉ ንፁሃን ደም እንዲሁ ሜዳ ላይ ዉሻ ልሶት አይቀርም ነገ ዋጋ ያስከፍላል ።በምድርም በሰማይም!!!

ይህንኑ እዉነት ትናንት ኢራቅ በሳዳም ሁሴን፣ሊቢያ በጋዳፊ፤ ግብፅ በሙባረክና በሌሎችም ጨፍጫፊ አምባገነን መሪዎችና ቤተሰቦቻቸዉ ተላላኪ ሆድአደሮቻቸዉ አይተናል አንበሳ ጉድጓድ ሲጣሉ ነገ የአገራችን ጨፍጫፊዎችና አስጨፍጫፊዎች ተረኞች ይሆናሉ። ተላላኪዎቻቸውም እንዲሁ ለመሆኑ ዛሬ በሁለቱም አምባገነን አገዛዝ እጆቻቸዉን በንፁሃን ዜጎች ላይ ያሳረፉት እነ በትናቸዉ ስንሻዉን ጨምሮ በአካለ ስጋ ዛሬ የምናያቸው ፅንፈኞች ካለፈዉ ስህተቶቻቸዉ ምን ተማሩ?!ነገስ በአሁኑ ወቅት እነሱ በሚሰሩት ወንጀል ቤተሰቦቻቸዉ አንበሳ ጉድጓድ መጣል አለባቸዉ?!ፈራጁ ንጉስ እዉነት ነዉ!የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ የኢትዮጵያ አምላክ ነው!!ለመሆኑ ልጆቻቸውስ በነሱ ወንጀል አንገታቸዉን ደፍተዉ ቀሪዉ ዘመናቸዉን የሰዉ አይን እየሸሹ በወላጆቻቸዉ ስም መጠራትን እያፈሩ እንዲኖሩ ለምን ይፈርዱባቸዋል??!!

ትናንት ቀይ ባሕርን አቋርጦ የመሪዎችን እጅ ለመሳም ለያዥ ለገናዥ አስቸግሮ የነበረዉ የዉስጥ እጅ እንደምንም ተሹለክልኮ በሳመ ማግስት ለወያኔ ፍርፋሪ የተንበረከከው እሱም ዜሮ ዜሮ የሆነዉ ሆድ አምላኪው አቀንቃኝ ሰለሞን ተካልኝ ከወያኔ ተላላኪነት ጡረታ መዉጣቱ በሰፊዉ በከተማችን እየተወራ ነዉ። ለሱ ተመድቦ የነበረዉ የራዲዮ የአየር ሰአት በጀትም በአዉራምባዉ ድሕረገፅ አምደኛ በታጋይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በኩል ለበትናቸዉ ስንሻዉ እንደሚዘዋወርለት በሰፊዉ በከተማችን ይወራል። በትናቸዉ ስንሻዉ ደግሞ ሰሞኑን አንጋፋዉንና የአርባ አመት ትግል እያካሄደ ዛሬም ድረስ አለ የሚባለዉን ኢሕአፓንና ግንቦት ሰባትን የማፍረስ እንቅስቃሴዉ በወያኔዎች ተወዶለታል፥ለዚህ ይመስላል ሰሞኑን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከነበረከት ስምኦን በታጋይ ዳዊት ከበደ በኩል የተቸረዉ። ሰለሞን ተካልኝም ዳያስፖራውን ይቅርታ ሊጠይቅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አንድ ለቤተሰቡ ቅርብ የሆነ ሰዉ ከወደ ቨርጂንያ ሹክ አለኝ። ምን ችግር አለ እንቀበለዋለን !ቂም መያዝ ድሮ ቀረ !ቂም መያዝ ያረጀ አካሄድ ነዉ ፧የፋራ ነዉ ይባልልኛል ። እንደተለመደዉ በራችን ወለል አድርገን እንቀበለዋለን ፧የጠፋዉ በግ ተገኘ ብለን ርችት እንተኩስለታለን ፧ሲሄዱ መሸኘት ፧ያጠፉትን አጥፍተዉ ሲመለሱ መቀበል ለምደን የለ?! ወያኔም እንደሸንኮራ ምጥጥ አድርጎ ይተፋቸዋል ትፋቱን እላያችን ላይ ጠራርገን እንቀበላቸዉና ትልልቅ ቦታ ይሠጣቸዋል ለዚህ በምሳሌነት ስም መጥቀስ ይቻል ነበር ግን ወቅቱ አይፈቅድልኝም ። ድል አድርጎ እንደተመለሰ ጀግና?!!የዳያስፓራውም ሚዲያዎች ይቀባበልዋቸዋል። ብዙዎቹ ባዶ እጃቸዉን ያለመረጃ ይመጣሉ ነገ አንደለመዱት ጓዳ ጎድጓዳችንን ፈትሸዉ ምስጢራቱን በዝብዘዉ ተመልሰው ይሄዳሉ ያሞኙናል ፧ገንዘብ ይሰሩብናል ልበል በአራዳ ቋንቋ!!!? የዳያስፖራ ፖለቲካ ይሄ መሆኑ ነዉ ወገኖቼ ኢትዮጵያዉያን ።ለዚህ ነዉ ይህ አጓጕል አካሄዳችን ልቤን አሳምሞኝ ፦፦እስቲ ቂማችን ጥቂት እንኳን እናቆየዉ የሚል ርእስ ለክፍል አንድ ፅሁፊ የሰጠሁት።

ዛሬ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልና ደጋፊ ነን የሚሉ አስተሳሰበ ደሀ ግለሰቦች የጋራ ጠላት የሆነዉን የወያኔ ኢሕአዲግን ፓርቲና ባለስልጣኖቻቸዉን ከማዉገዝና ከመታገል ይልቅ የተቃዋሚዉን ጎራ ስም ጥላሸት መቀባትና ማዉገዝ ይመቻቸዋል ጊዜያቸዉንም በዚህ አይነት ልፊያ ላይ ማዋል ያስደስታቸዋል ፥ መጠላለፍ ይወዳሉ ሰዉን ማዋረድና ሰድቦ ለተሳዳቢ መስጠት አነሱን ያገዘፋቸዉ አዋቂ ያስባላቸዉ ይመስላቸዋል አገሪቱን በሚችለዉ አቅሙ ለመታደግ የተነሳዉን ጎትቶ መጣል ከምንም በላይ ያስደስታቸዋል በቃ በነሱ ቤት ይሄ ትልቅ ትግል ነዉ። በዚህ አይነት እኩይና መሰሪ እንቅስቃሴያቸዉ ደግሞ ገንዘብ ይሰሩበታል መንደርተኛ ራዲዮን ከፍተዉ የከፋፋይና በታኝ ተግባራቸዉን ያራግቡበታል፧ለወያኔ ዱላ ያቀብሉታል በብዙ ገንዘብ ሊያገኝ የማይችለዉን መረጃ በአየር ላይ ቤቱ ድረስ ይልኩለታል፧ እንደነበትናቸዉ አይነት ማፈሪያዎች ሥራቸዉ ይኸዉ ነዉ፧በቃ!!

ሌላዉ እዚህ አገር ለሚደመጡ ራዲዮኖች መልእክት አለኝ የሚሰማ ጆሮ ያለዉ ይስማ መቸም አገራችን ዉስጥ ላለፉት አርባ አመታት ያላየነዉ የፖለቲካ ድርጅት የለም ብዙዎቹ ዛሬ የሉም። በህልዉና ዘመናቸዉም በዉስጣቸ የሃሳብ ልዩነቶችን አስተናግደዋል ። ያጠፋዉንም በድርጅቱ ዉስጠ ደንብ ዲሲፕሊን የእርምት እርምጃ ተወስዷል ።አንጃዎችም ተፈጥረዉ ተለያይተዋል ።በሥርአት በመከባበር የተፈፀመ ጨዋ ተግባር ፧ጨዋ ዘመን አይተናል። ዛሬስ ?!በተለይ በዳያስፓራዉ የፈረደበት የመዋጮ ራዲዮ ተከፍቶ በአንድ ወቅት ለአንድ አላማ ተሰልፈዉ የሕይወት መስዋእትነት ለመክፈል ቃልኪዳን ገብተዉ የተሰለፉ ወገኖች ጓዶቻቸዉንም ለዚህ አላማ አሰልፈዉ ፧ያጡ የወጣትነት ዘመናቸዉን ለዚህ ሕዝባዊ ትልቅ አላማ መስዋእት ያደረጉ ሁሉ ፧ዛሬ አዎ ዛሬ ፧በራዲዮ ላይ ወጥቶ መገላለጥና መዘራጠጥ ሃላፊነት የጎደለዉ ተግባር ይመስለኛል።ለዚያዉም የህቡእ ድርጅት የተዋቀረ ድርጅት የጠንካራ ፓርቲዎች ሞዴል ይባል የነበረ እጅግ መዉረድ ነዉ ወገኖቼ!!ለዚህ ፓርቲ ዉድና ተተኪ የማይገኝለትን ሕይወታቸዉን መስዋእትነት የከፈሉትን ዜጐች መርሳት ነዉ ። ለጠላት መሳለቂያነት መዋል!? ሀላፊነት የጎደላቸዉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ደግሞ እሰጥ አገባዉን ይወዱታል የሬዲዮናቸዉን አድማጭ ይናፍቃሏ!! ገንዘብም አይደል!? እነሱ ምን ጎደለባቸዉ የየዋሃን ገንዘብ አይደል?! ወገኖቼ ቆም ብላችሁ ሁኔታዉን በዚህ መስታወት ተመልከቱት ፥ብዙዎቻችን ዛሬ ከዚህ ፖርቲ ጋር ባንኖርም ኢሕአፓ የልጅነት ትዝታችን ነዉ።

ወንድም እሕቶቻችን እናት አባቶቻችን ገብረንበታል። ብዙዎቻችን አሁንም ድረስ ህሊናችን ቆስሎአል አካለ ጐደሎም የሆንለት ጥቂቶች አይደለንምና እና እባካችሁ!? ማራገቡን ተዉት ክቡራን አራጋቢዎች!አዛኝ ቅቤ አንጓች አትሁኑ የጥላቻና የብቀላ ስራ ይመስልባችኋል።

ይቀጥላል ክፍል፯

አስተያየት ወይም መረጃ ካለዎት በዚህ አድራሻዬ ይላኩልኝ። kifeleta11@gmail.com

source,,,http://ecadforum.com/Amharic/archives/9634/
posted by Daniel tesfaye

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: