FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

FREEDOM,DEMOCRACY.JUSTICE.AND UNITY FOR ALL ETHIOPIANS …by DANIEL TESFAYE

አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል ፭)

timthumb
August 22, 2013
ናደዉ፦ከዋሽንግተን ዲሲ
የወያኔ ጉጅሌዎችን ስዉር አጀንዳ ፅሁፍ ከዚህ ሆድ አደር ተላላኪ ታሪክ በኋላ ወደ ሌሎቹ እዘምታለሁ፤በማህበር ተጠርንፈዉ እስከሚመጡልኝ ወይም እስከሚመጡብኝ ድረስ ማጋለጤ በሰፊዉ ይቀጥላል፧ለጠላቴ አልተኛም እንደ በትናቸዉ/ፍርሻው ስንሻዉ የታች አርማጭሆ ልጅ መሆኔ ቀረ?!

ምርጫዉ ስንሻዉ ወይም ብዙዎች የዲሲና አካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚጠሩት በትናቸዉ/ፍርሻው ስንሻዉ ባለፈዉ እሁድ ደግሞ አዲስ የጥላቻና የጋጠወጥ ስድብ ከረጢቱን ዘረገፈዉ፣ አዎ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሚገኙት በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መሪ በፈርስቲ ኢጂራ ፕሬዘዳንት በሼክ ነጂብ ላይ፧ በወያኔ ጉጅሌ በጀት በሚተዳደረዉ ወናፍ መንደርተኛ ራዲዮኑ እሳቸዉን ብቻ ሳይሆን ባለቤታቸዉንና የሙስሊሙን ሕብረተሰብ የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴም ጭምር፥እንደወያኔ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ እሱም ሲሳደብ ዉሎ አደረ ፧ተወካያቸዉ መሆኑም አይደል?!መሽቶ ነጋ በቅዳሜ ማታና በእሁድ ቀን ፕሮግራሞቹ፤እኔም በዚህ ባንዳ ዙርያ በተከታታይ ለማወጣቸዉ ፅሁፎቼ ስል አለፍ አለፍ አድርጌ መቅረፀ ድምፄን ይዤ መከታተሌ አልቀረም፧ሚስቴና ልጆቼን ተደብቄ በሌሉበት መሆኑ ይታወቅልኝ !ምክንያት፥የዚህን ተሳዳቢ ሰዉዬ ቱማታ ላለመስማት ቤቱን ጥለንልህ እንዉጣ የሚለዉ ብስጭታቸዉ ስላሳሰበኝ ብቻ !!

ለእለቱ ለስድብ ኢላማነት የተመረጡትን እኝህን የሀይማኖት መሪ እንዲህ አለ፦ በአክብሮት ዘለፋዬን እርስዎም ባለቤትዎም የሀይማኖትዎም ተከታዮች በጥሞና ያዳምጡኝ ብሎ የራዲዮን ፕሮግራሙን ጀመረ፣የተለመደዉን የጥላቻ ስድብ ዉርጅብኝ በይሉኝታ ቢስና ፀያፍ ቃላቶቹ ለቀቀዉ አዎ እሱ ማንን ፈርቶ?!

ዛሬ ገና ለዚህ ተከታታይ ፅሁፌ ተገቢና ትክክለኛ ርእስ መስጠቴን አረጋገጥኩ። አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል። ያልኩትን፧ በትምህርተ ጥቅስ አስቀመጥኩት፤ ለምን እንዲህ አልክ ብትሉኝ መልሴ እንደሚከተለዉ ይሆናል፧! እኚህ ሰዉ ስለዚህ መሰሪ የደርግ ካድሬ ብዙ ምስጢር እንደሚያዉቁ ስለማዉቅ ብቻ ሳይሆን ዛሬ የሚያዉቁት ነገር ምናልባትም ላለፉት አስርተ አመታት ለዋሽንግተን ነዋሪ ኢትዮጵያዉያን ያልተናገሩትን የደራሽ ግብረሃይል ምስጢር የሚያጋልጡበት ወቅት አሁን በመሆኑ ነዉ። ሳይቸግረዉ የነካካቸዉ ይመስለኛል፧ያዉም የሞራል ህልዉናን በሚፈታተን መልኩ፥ለዚህ ወስላታ የመልስ ምት አያስፈልገዉ ብለዉ ነዉ ሃጂ?! ነገሩ እንዲህ ነዉ በክፍል አንድና ሁለት ላይ በግልፅ እንዳሠፈርኩት የዛሬ አስር አመት አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ በከፍተኛ ረሀብና ድርቅ በተጠቃችበትና አላፊነት የጎደለዉ የህወሀት ዘረኛ አምባገነን አገዛዝም ሁኔታዉን ለመደበቅ በሚድበሰበስበት በዚያን ወቅት የዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ሁኔታዉን ገሀድ ማዉጣታቸዉ እርግጥ ነዉ። በወገኖቻችን ላይ ደርሶ የነበረዉ አስከፊ ሁኔታ ወያኔን ከመታገል ጎን ለጎን ለተጎዱት ወገኖች በአፋጣኝ መድረስ ጊዜዉ ግድ ይል ነበር። በዚህም መሰረት በዳያስፓራ የሚገኙት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ትልቅ ድርሻ አበርክተዋል በዋሽንግተንና አካባቢዉም በተመሳሳይ መልኩ ከተጎጂ ወገኖቻቸዉ ጎን ለመቆም መንቀሳቀሳቸዉ አልቀረም። ይህንኑ የወገን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ሲባል በተቋቋመዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ግብረሃይል ዉስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ከሁለት መቶ ሽህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ የተሰበሰበዉንም ገንዘብ ደራሽ ግብረሃይል የሚል ስያሜ ለተሰጠዉ ኮሚቴ በአደራ በአደራ አስረከበና ዉጤቱን መጠባበቅ ጀመረ። በጊዜዉ ከኮሚቴዉ አባላት ዉስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የኢትዮጵያዊነት ራዲዮኑ ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ፤የሀገር ፍቅር ራዲዮኑ ባንዳዉ ንጉሴ ወልደማርያም፤የፈርስቲ ኢጅራዉ ፕሬዘዳንት ሃጂ ነጂብና ሲስተር እማዋይሽ ነበሩ። ተወካዮቹ በአካል ተገኝተዉ ለተጎጂ ወገኖቻችን አስፈላጊዉን ቁሳቁስ ገዝተዉ አንዲሰጡ የሕዝብ አደራ ተቀበሉ ፧አደራዉን ግን በሉት።

እንዲህ ሆነላችሁ የተከበራችሁ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ፧ የኮሚቴዉ ተወካዮች አዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በወያኔ ካድሬዎችና ሰላዮች ታጅበዉ ወደተዘጋጀላቸዉ ሸራተን ሆቴል አመሩ፧ ከተለያዩ ባለስልጣኖችም የምስጋናና የእንኳን ደህና መጣችሁ ስልኮች አቃጨሉላቸዉ የኰሚቴዉ መሪ የነበረዉ ሆድ አደር ተላላኪዉ ንጉሤ ወልደማርያም ከመመሪያ ጋር በእለቱ በሆቴል ክፍሉ ዉስጥ የወያኔ አባልነት ፎርም መሙላቱን የከብት ሕክምና ባለሙያዋ ባለቤቱ ታወራለች። በተያዘላቸዉ ምርጥ ክፍል አርፈዉ ለጥቂት ቀናት በከተመዉ ዉስጥ ከተዝናኑ በኋላ ፧ከየአቅጣጫዉ ከአገር ዉስጥም ሆነ ከዉጭ አገር በተጎጂዎች ስም በሚጎርፍለት ገንዘብ የሰከረዉ ወያኔ መልእክተኞቹን በቴሌቪዥን መስታወት ለጥቂት ደቂቃዎች ከሌሎች ለጋሾች ጋር ቀርበዉ ሁለት መቶ ሽህ የኢትዮጵያ ብር በጊዜዉ የወያኔ የአደጋ መከላከል ኰሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ስምኦን መቻሌ ያስረክቡና በሌላ የክህደት ፕሮግራም ለመገናኘት ተማምለዉ ይለያያሉ። ከመሐል አንድ እህታችን ብቻ በነገሩ ግራ በመጋባት ይህንን የህዝብ አደራ በልነትን ታወግዛለች ወደ አሜሪካ ስትመለስ ለማጋለጥም ለራሷ ቃል ትገባና ዋሽንግተን በገቡ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ ራዲዮኖች እየቀረበች ወገኖቼ የረሀብተኛዉ የእርዳታ ገንዘብ ተበላ እያለች መጮህዋን ትቀጥላለች ፧ቀሪ የኰሚቴ አባላትን ጨምሮ በአማላጅ ሁኔታዉ ይፋ እንዲወጣ ታስጠይቃለች ነገር ግን የሚሰማት ጠፋ ። አንድ እለት ብቻ ጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ ከሕብረተሰቡ ዛቻና ማስፈራርያ ሲበዛበት በራሱ ራዲዮ ላይ ወጥቶ ሃምሣ ሽህ ዶላር ብቻ መቅረቱንና ይህም ገንዘብ ወደፊት የሕዝብ ዉሳኔ ያገኛል ብሎ ለፈፈ፤ከዚያ ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት አመታትን አስቆጠሩ እነሆ ዛሬ አስርተ አመቱ ተቆጠረ ነገሩ የተረሳ ከሀዲ ቀማኞቹም ለይቶላቸዉ ወያኔ በፍርፋሪ ከጎኑ በግልፅና በስዉር አሰልፏቸዉ በሚመፀወቱት የራዲዮን የአየር ሰአት እንደገና ይሰድቡናል ያላግጡብናል፣ ገንዘቡንና ጊዜዉን የተበላዉ ነዋሪም አፈር ብላ ብሎ ተራግሞ ወደ ቤቱ ገባ ብዙዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች የነዚህን ከሀዲዎች ፀያፍ ተግባር ዛሬም ያስታዉሳሉ። ይህ የህዝብ ገንዘብ ነዉ ያለንበት አገር ደግሞ የህግ የበላይነት ይከበራል የተበላዉ በረሀብ ለተጎዱ ወገኖች የተዋጣ ገንዘብ ነዉ የፈለገዉ ያህል ጊዜ ቢቆይም ጉዳዩን በሕግ ፊት ማቅረብ ይቻላልና የህግ ባለሞያ ኢትዮጵያዉያንን ነገሩን እንዲመረምሩት በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ!

አሁንም በቅርቡ በዚያ በዘራፊዎቹ ንኡስ ኰሚቴ ዉስጥ የነበሩ አዛዉንትን አግኝቼ ሳነሳባቸዉ ነገሩ እንደዉስጥ እግር እሳት ያንገበግበኛል አሉ ወንጀለኞቹን እነ በትናቸዉ ስንሻዉን ዛሬም ምርር ብለዉ በፊቴ ተራገሙ በተጨማሪም እንዲህ አሉኝ በዚያን ወቅት ተጨንቄ ሃጂ ነጂብም ዘንድ ሄጄ እዉነቱን ለሕዝቡ ንገሩ ብዬ ብጠይቀዉ ዳግም አጠገቡ እንዳልደርስ አባረረኝ አሉና ሁኔታዉን ጊዜ እንዳመቻቸዉ የሚያዉቁትን ሁሉ በተገኘዉ ሚዲያ ገሃድ እንደሚያደርጉት ገለፁልኝና ተሰነባበትን።

በመጨረሻ ማሳሰብ የምወደዉ ሃጂ ነጅብ የሚያዉቁትን ይንገሩንና እርስዎም ከሕሊና ወቀሳ ይገላገሉ፣በብዙ ሀይማኖቶች ሲነገር የምንሰማዉ፦ ሌባና ሌባ ሲሰረቅ አይቶ እንዳላየ የሆነ ፧የሁለቱም ወንጀል አንድ ነዉ ይባል የለ?!እና እነዚህ ወሮበሎች ስለዘረፉት ገንዘብ የሚያውቁትን ይንገሩን እግረመንገድዎንም ከሃሜቱ ነፃ ይዉጡ እያልኩ ነዉ። ወቅቱም አሁን ነዉና!!!

የጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ ጉድ መቸም ቢጎለጎል አያልቅም እኔም አንዴ ጀምሬዋለሁና የማዉቃቸዉንና የሚደርሱኝን መረጃዎች በሙሉ እሄድባቸዋለሁ አዲስ አበባ አፍንጮ በር አካባቢ ለምትኖረዉ የድሮ ጓደኛዪ ምሥራቅ ስንሻዉ ከባለቤትዋ ከታጋይ ተክሌ አጋበዝ ጋር ሆና የወንድምዋን ጉድ እንድታየዉና ይህንን ፅሁፍ እንድትፈትሸዉ ሰሞኑን ሳልደዉልላት አልቀርም።

ይህን ማስታወሻ ስፅፍ ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትና አቶ ብርሃነ መዋ ትዝ አይሉኝ መሰላችሁ!?በነገራችን ላይ ሁለቱንም ወንድሞቼን እጅግ አድርጌ አከብራቸዋለሁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ቀላል የማይባል አስተዋፅዖ ማበርከታቸዉ እውነት ነው። ዛሬ ግን ወደ ፓለቲካዉ መድረክ ዳግም ላይመለሱ ከአንደበታቸዉ ብዙዎቻችን ሰማን። የሚገርማችሁ ደግሞ ሁለቱም በአንድ ወቅት በቅንጅት መፍረስ ማግስት መሆኑ ነዉ፧ ለዚህ ትልቁና ዋናዉ ተከሳሽ ጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ መሆኑ አይደንቅም። የቅንጅት አመራሮች በእስር ላይ በነበሩበት ግዜ እዚህ የነበሩት የቅንጅት የድጋፍ ኮሚቴ አባላት መከፋፈል ጀመሩ የኰሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት ሻለቃ ዮሴፍ በእስር ላይ ከሚገኙት የቅንጅት ፕሬዘዳንት ከኢንጅነር ሃይሉ ሻወል የኰሚቴ አባላቶች ሹም ሽር በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ ላኩ ተባለ አሰራሩ ማእከላዊነት ያልጠበቀ ነዉ ይሄ የንጉሣዊ ሹመት አይነት ነዉና አንቀበልም የሚል አካል ተፈጠረ የነብርሃነ መዋ ቡድን፧ ከስር ቤት ሾልኮ መጣ በተባለዉ የሹመት ዝርዝር ዉስጥ በዚያ የፓርቲ ስብስብ ዉስጥ ያልነበሩት የዶክተር ታየ ወልደሰማያት ስም የመሪነቱን ቦታ ይዞ ቀረበ ይህንን ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያራግቡት ሃላፊነቱን በበላይነት አንዲመራዉ ደጎስ ካለ የገንዘብ ጉርሻ ጋር ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ ተረከበ ረዳት ሆድአደር አፍራሾችም ተመደቡለት ረዳቶቹ ደግሞ ከኛ ወዲያ ትግል ላሳር የሚሉ የትግል ዘመናቸዉን ሻማ በማብራት ብቻ የሚደክሙ የዲሲ ፋኖዎችና በታኞች ተሳካላቸዉ በአጭር ጊዜ የአገሪቱን ሕዝብ አንድ አድርጎ ወያኔን ያርበደበደዉን ብዙ ዜጎች በጠራራ ፀሐይ ዉድና ተተኪ የማይገኝለትን ዉድ ሕይወታቸዉን የገበሩለትን የፓለቲካ ንቅናቄ ጠልፈዉ ጣሉት አሽመደመዱት። አዎ ምርጫዉ ስንሻዉ፧እነ ሻለቃ ዮሴፍንና ታዋቂዉን ስመ ጥር የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ማኖ አስነካቸዉ ሸወዳቸዉ በግርግርም ከፍተኛ ገንዘብ ተበላ ቅንጅትም ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከጨዋታ ዉጪ ሆነ ተበተነ የበትናቸዉ ስንሻዉ አለቆች ከበሮአቸዉን ደለቁ ከሕዝባዊዉ ማእበል ተጠራርጎ ከመጥፋት ዳኑ፧ ያን ሁሉ ወንጀል ፈፅመዉ ዛሬም እነምርጫዉ አሉ!አሁንም ኢንጅነር ሐይሉን እነ ብርሃነ መዋንም ጨምሮ ሁሉንም ባልተገራዉ ግልብ ንግግሩ ሙልጭ አድርጎ እያወረዳቸዉ ነዉ።ዛሬ በዚህ ባንዳ ምክንያት ብዙ ጠንካራ ሰዎችን አጥተናል አሁንም ዘለፋዉን ቀጥሏል።

መቸም በበትናቸዉ ስንሻዉ ዘለፋና ዝርፊያ ቆሽቱ ያልተቃጠለ አንጀቱ ያላረረ የለምና የዚህ ካድሬ ተጠቂዎች ለዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ብዙ መረጃዎች አደርሰዉታል፧ብዙዎቹ ይበሳጫሉ እንዲህ ያለ ኢትዮጵያዊ የለም ያስብላሉ ተግባራቶቹ ግን እዉነቶች ናቸዉ። እና አኔ እያልኩ ያለሁት ስም ለማጥፋት ለመጠፋፋት ሳይሆን አካሄድህ አስነዋሪ ነዉ ብሎ እሱነቱንና ወልጋዳ አካሄዱን ለራሱ እንደመስታወት አሳይቶ ወደወገኖቹ ለመመለስ ነዉ እንጂ ከተላላኪ ሆድ አደሮች ጋር ይሄን ያህል ግዜ ማባከን ባላስፈለገም ነበር ምናልባት ወደቀልቢያዉ ቢመለስ ብዬ እንጂ!!

ትናንት አንድ ወዳጄ አንድ አባት በዚህ አጉራ ዘለል ካድሬ የሆኑትን ልንገራችሁና የዛሬዉን ፅሁፊን ላብቃ በአንድ ወቅት ለከፈተዉ ቤተክርስትያን በደመወዝ እንዲያገለግሉት አንድ አባት ከምስጢራተ ቤተክርስትያንና ቅዱሳን መጽሐፍቶች ጋር ከአገር ቤት ያስመጣቸዋል በሚኖርበት አካባቢ ነዋሪዎች ቪላ ዉስጥ የምትገኝ አንድ ጠባብ ክፍል ይከራይላቸውና ይገባሉ ቄሱም በየወሩ ከሚሰጣቸዉ ደመወዝ ለቤቱ ኪራይ እየቀነሰ ቀሪዉን ሲሰጣቸዉ ይከርማል የሰዉየዉ ግልብ ባህርይ ባይመቻቸዉም ሌላ መጠጊያ ስለሌላቸዉ ረዘም ላለ ጊዜ እንደተቀመጡ እንባ እየተናነቃቸዉ ይናገራሉ አነጋገራቸዉ ሁኔታቸዉ በዚህ በመጦርያ እድሜያቸዉ ስደተኝነታቸዉና ሁኔታቸዉ እጅግ አሳዝኖኝ መንፈሴ እየተሸበረ ስላስቸገረኝ ንግግራቸዉን ቶሎ እንዲጨርሱ በመመኘት ከዚያ በኋላስ አልኳቸዉ ከዚያ በኋላማ ልጄ አሉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ መሬቱን በያዙት ረጅም ጃንጥላ ጫፍ እየቆረቆሩ ፦አንድ ቀን ትንሽ አመም አርጎኝ እቤት ዋልኩ ያለወትሮየ ቤት መዋሌን የተመለከቱት የቤቱ ባለቤቶች ሊጠይቁኝ መጡ እህል ዉሃም ሰጡኝና በደንብ ሳይሻለኝ እንዳልነሳ ሲመክሩኝ አይ እዚህ አገር ወጪዉ መች ያስተኛል አልኳቸዉ ሴትየዋም ሳቅ ብለዉ አይ አባ እርስዎ ደግሞ ምን ወጪ አለብዎት ለምግቡም ቢሆን አያስቡ አሉኝ እኔም ለሆዴ እንኳ ግድ የለኝም የቤት ኪራዩን ማን ይከፍልልኛል ስላቸዉ የምን የቤት ኪራይ ነዉ የሚያወሩት እኛ ሁኔታዎን አይተን ምርቃትዎ ይበቃናል ብለን ገንዘብ ተቀብለዉ አናዉቅም አሉኝ እኔም በየወሩ ከደመዜ ላይ እንደሚቆርጥብኝ ነገርኳቸዉና ከዚያን አለት ጀምሮ አይኑን አያሳየኝ ብዬ ለአምላኬ አልቅሼ ቀረሁ አሉኝ። አይገርምም ወገኖቼ?!

እነዚህን የመሳሰሉ አሳፋሪ ብዙ ተግባሮቹን ብዙ ትሰማላችሁ እዚህ አካባቢ ጎራ ብትሉ፤ከዚህ ነዉረኛ የወያኔ ተላላኪ የምንረዳው አንድ ነገር አለ ይኸዉም አምባገነኑና ጨካኑ የህወሀት ስርአት በዙርያው የሚኮለኩላቸዉ ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች ምንአይነት ከርሳሞችና ምግባረ ብልሹዎች እንደሆኑ ነዉ።

ክፍል ፮ ይቀጥላል

source,,,,http://ecadforum.com/Amharic/archives/9539/

posted by Daniel tesfaye

Advertisements

Single Post Navigation

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: